ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Religion. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 03-19-17, 09:51 pm (rev. 1 by Tg on 03-19-17, 10:04 pm)


Karma: 100
Posts: 238/444
Since: 07-20-15

Last post: 73 days
Last view: 73 days
ልብ ብለዉ ያንብቡት3 ዛፎች ነበሩ ። 2ቱ የቆሙ ሲሆኑ አንዱ ግን
ወድቋል። ከእለታት አንድ ቀን እኚህ ዛፎች
የህይወት ህልማቸውን ይነጋገሩ ጀመር ።
አንደኛው ዛፍ " እኔ ሳጥን ሆኜ የአለም ውድ
እቃዎች እንዲቀመጡብኝ ጥልቅ ምኞቴ ነው " አለ፣
ሁለተኛውም ቀበል አድርጎ " እኔ መርከብ ሆኜ
የአለም ነገስታት እንዲጓጓዙብኝ እንዲፈንጩብኝ
እፈልጋለው" አለ ፣ ሶስተኛው ደግሞ " እኔ
መድሀኒት ሆኜ ብዙዎችን ማዳን ከቻልኩ ከዛ በላይ
ምንም ኣልፈልግም" አለ ።
ሶስቱም ህልማቸውን አውርተው ሲጨርሱ ዛፍ ቆራጮች
መጡ፡ የወደቀውን ይዘውት ሄዱ ።
እሱም ሳጥን መሆን የህይወት ፍላጎቱ ቢሆንም
ጠርበው የከብቶች መመገቢያ አድርገው ሰሩት።
ሁለተኛውንም መጥተው ቆረጡት ለጀልባነትም
አዋሉት፡ መርከብ የመሆን ምኞቱም ባክኖ ቀረ።
ሁለቱም ዛፎች ተናደዱ ህልማቸው የተጨናገፈም
መሰላቸው። ሶስተኛው ዛፍም ለምንም አገልግሎት
ባለመዋሉ እጅጉኑ አስከፋው።
ከአመታት በኋላ ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ አለም መጣ።
እነሆ በ ቤተልሄም ቦታ ስላልነበር በከብቶች በረት
ተወለደ። እናቱ ማርያምም በከብቶች መመገቢያ
ውስጥ ጠቅልላ አስቀመጠችዉ። የአለም ውድ ነገሮች
ማስቀመጫ መሆን የፈለገው ዛፍም የውዶች
ውድ የእንቁዎች አንቁ የሆነው ክርስቶስ
ተቀመጠበት።
ጌታም ሊያስተምር ሲሄድ በታንኳ ተጓዘ ፡ ያም
ታንኳ ያ የአለም ነገስታት እንዲጓዝብኝ እፈልጋለው
ያለው ነበር፡ የነገስታት ንጉስም ተጓጓዘበት። ጌታችን
እንዲሰቀል ሲፈረድበት የቀረውን ዛፍ
ቆርጠው አመጡ በሱም ሰቀሉት። ለብዙዎች
መድሀኒት መሆን የፈለገው ዛፍ መስቀል ሆኖ አለም
ሁሉ ዳነበት።
ሶስቱም ዛፎች ህልማቸው የተጨናገፈ ሲመስላቸው
ፈጣሪ ግን ካሰቡት በላይ አደረገላቸው። ወዳጆቼ ለእኛም
ከራሳችን በላይ የሚያስብልን
አምላክ አለን። ስለዚህ ህልማችን የተጨናገፈ
ቢመስለን አምላክ አብዝቶ ሊሰጠን ስለሆነ ሁሌም በ
ትዕግስት እንጠብቀው።
መጪው አዲስ ዘመን ሁላችንም የተፈጠርንበትን
አላማ አውቀን ፈጣሪ አምላካችንን የምናስደስትበት ብሩህ
አመት እንዲሆን የልብ ምኞቴ ነዉ፡፡

ለጓደኞቻችሁ share share በማድረግ አድርሱ
Posted on 03-20-17, 12:29 pm


Karma: 100
Posts: 146/610
Since: 08-27-16

Last post: 84 days
Last view: 2 days
Pages: 1