ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Cooking & Recipes . | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 03-17-17, 09:45 pm

Karma: 100
Posts: 70/94
Since: 08-19-16

Last post: 81 days
Last view: 18 days
የሚያስፈልጉ ነገሮች
----------------

1. ፍርኖ ዱቄት
2. ጨው
3. ዘይት
4. የተነጠረ ለጋ ቅቤ
5. ሊጥ መዳጫ
6. መጥበሻ
7. ማቡኪያ እቃ
8. ከበሰለ በኋላ እንዳይደርቅ የምናስቀምጥበት ላስቲክ

አሰራሩ
------

ማቡኪያችሁ ዕቃ ውስጥ አስፈላጊውን ፍርኖ ዱቄትና ጨው ጨምራችሁ እንደ ዳቦ ቅሎ ልጥ አድርጋችሁ በወፍራሙ በጣም እሹት ሊጡ ለእጅ የበለጠ መለስለሱን ስታውቁ ቅቤ ጨምራችሁ እስከሚዋሃድ አሁንም እሹት ቅቤ በጣም ሳያንስም በጣም ሳይበዛም መሆን አለበት

በዚህ መልኩ ያዘጋጃችሁትን ሊጥ በምግብ ላስቲክ ውስጥ ሸፍናችሁ አስቀምጡት

ቀጥሎም የሊጡን መዳጫና ቅቤ አቅርባችሁ አንድ መጥበሻ ሊጋግረው የሚችለውን ሊጥ ቆንጥሩ በእጃችሁ አንደያዛችሁ ቅቤ ቆንጠር አድርጉና ሊጡ መሃል ውስጥ ክተቱ ከዛም ሊጡን ቅቤው ወደ አለበት ክትት ክትት እያደረጋችሁ እሹት ከዛ መክተፊያው መሃል ላይ አስቀምጣችሁ በመዳጫው ዳጡትና ሊጡን በክቡና በስሱ አስፉት መጠኑ የምትወስኑት እንደ መጥበሻው ስፋትና ጥበት ነው

በመቀጠል መጥበሻውን እሳት ላይ ጥዳችሁ በማስማት ፈጢራውን በተከታታይ ጋግሩና ጨርሱ
ስትጨርሱ በምግብ ላስቲክ ውስጥ እንዳይደርቅና ንፋስ እንዳይገባበት አርጋችሁ ሸፍኑና እንደአስፈላጊነቱ ለምግብነት መጠቀም ትችላላችሁ
Posted on 02-12-18, 02:24 am

Karma: 100
Posts: 1/2
Since: 02-12-18

Last post: 277 days
Last view: 277 days
Posted by ማማዬ