ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Religion. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 03-16-17, 05:08 pm (rev. 2 by Ye Arada Lij on 03-16-17, 05:10 pm)


Karma: 90
Posts: 310/879
Since: 02-29-16

Last post: 69 days
Last view: 69 days
በቤተክርስቲያናችን ስርአት መሰረት 7 ጊዜ እንፀልያለን የእነሱም ትርጉም

1⃣ ጠዋት 12 አንድ ክርስቲያን እግዚአብሔርን አምላክን በፀሎት የሚያመሰግንበት ምክንያት (ሚስጥር)

1 እግዚአብሔር አምላክ ሌሊቱንና ጨለማውን አሳልፎ ብርሀን እንድናይ ስላበቃን በዚህ ሰአት እግዚአብሔር አምላካችንን እንድናመሰግን ታዝዝዋል አንድም በዚህ ሰአት ጌታችን ለክስ ከጲላጦ ፊት ቆሞ የተወቀሰበት ሰአት ስለሆነ አንድም በዚ ሰአት አባታችን አዳም ያልተፈቀደለትን እፅ በልቶ ከገነት የተባረረበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድ ክርስቲያን ይህን ሁሉ እያሰበ ወደ አምላኩ እንዲፀልይ ታዝዋል

2⃣ ሰልቱ ሰአት ከጠዋቱ 3 ሰአት አንድ ክርስቲያን እንዲፀልይ የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር)

1 በዚህ ሰአት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብስራተ ገብርኤልን የሰማችበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድም በዚህ ሰአት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን የፀነሰችበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድም ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የተገረፈበት ሰአት ስለሆነ ዮሐ 19 ፥1 ሐዋ ስራ 2፥15 እያንዳንዱ ክርስቲያን ይሔንን የመሳሰሉ ሁሉ እያሰበ እግዚአብሔር አምላኩን እንዲያመሰግን ታዝዋል

3⃣ 6:00 አንድ ክርስቱያን እኩለ ቀን (ከ ቀኑ 6ሰአት) ሲሆን እንዲፀልይ የታዘዘበት ምክንያት ወይም (ሚስጥር )

1 ጌታችን በቀራኔዎ አደባባይ በመስቀል ተሰቅሎበታልና አንድም ልብሱን ተገፎበታል አንድም ሳዶር አላዶር ዳናት ሮዳስ በተባሉ ችንካሮች ተቸንክሮበታል አንድ ክርስቲያን ይህን ሁሉ እያሰበ በዚህ ሰአት እንዲፀልይ ታዞበታል

9⃣ ተስአተ ከ ቀኑ 9:00 ሰአት ሲሆን አንድ ክርስቲያን የሚፀልይበት ምክንያት (ሚስጥር)

1 አይሁዶች ጌታችን መድሀኒታችን ኢየ�ሱስ ክርስቶስን መራራ ሐሞት አጠጥተውበታል አንድም ቅድስት ነፍሱን ከ ክቡር ስጋው የለየበት ሰአት ነውና አንድም በመስቀል እንዳለ 7ቱን አፅርሀ መስቀል የተናገረበት ማር 15፥34 ማቴ 27፥50 አንድ በዚህ ሰአት ይህንን እያሰበ እንዲፀልይ ታዝዋል

5⃣ የሰርክ ሰአት ከቀኑ 11፡00 ሰአት አንድ ክር�ቲያን እንዲፀልይበት የታዘዘበት ምክንያት ወይም (ሚስጥር)

1 ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ወደ ከርሰ መቃብር የወረደበት ሰአት ስለሆነ አንድም ቀኑን በሰላም አሳልፎ ወደ ምሽት በሰላም ያደረሰን አምላክ ምስጋ ስለሚገባው ነው ይህንን የመሳሰሉ ሁሉ ሕዝበ ክርስቲያን እንዲያስቡ ታዘዋል

6➡ ከምሽቱ 3 ሰአት በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን እንዲያመሰግን የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር)

1 በዚህ ሰአት እራሱ ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስርአተ ፀሎት አሳይቶበታል አንድም በዚህ ሰአት ጌታችንን አይሁድ በይሁዳ ጠቁዋሚነት ተረበርበው የያዙበት ሰአት ስለሆነ ነው አንድም በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን ከመተኛቱ በፊት በሰላም ያዋለንንና ያስመሸንን አምላክ አመስግኖ መተኛት አለበት ይህን ሁሉ እያሰበ እንዲፀልይ ታዝዋል

7⃣ መንፈቀ ሌሊት ከሌሊቱ 6ሰአት በዚህ ሰአት አንድ ክርስቲያን እግዚአብሔር አምላኩን እንዲያመሰግንበት የታዘዘበት ምክንያት (ሚስጥር)

1 በዚህ ሰአት ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዶበታልና ነው አንድም ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙስና መቃብርን ድል አድርጎበታልና(ተነስቶበታል) በመዝሙረ ዳዊት አመሰግንህ ዘንድ በመንፈቀ ሌሊት እነሳለው ባለው መሰረት ጳውሎስ ሲላስ በእስር ቤት ሆነው ወደ እግዚአብሔር የፀለዩበት ስለሆነ ነው አንድም የሰው ልጅ የሚመጣበት ጊዜ ማታ ይሁን መንፈቀ ሌሊት ይሁን ዶሮ ሲጮህም ይሁን ሲነጋም ቢሆን አይታወቅምና ባለው አምላካዊ ቀል መሰረት በመንፈቀ ሌሊት አንድ ክርስቲያን እንዲፀልይ ታዝዋል

Pages: 1