ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Marriage & Divorce . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 03-14-17, 07:08 am (rev. 1 by Melat on 03-14-17, 03:33 pm)


Karma: 100
Posts: 192/426
Since: 07-12-15

Last post: 269 days
Last view: 269 days
የፍቅር ቀን
ይህ ዜና ለአለም ሁሉ ይሰማ!
አንዳንዴ ክፉዜናዎች ብቻ ጮክ ብለው ስለተወሩ ጥሩ ዜናዎች ተደብቀው ይቀራሉ፡፡ በተለይ አሁን ባለንበት ሁኔታ ክፉ ዜናዎች በደቂቃ ውስጥ ለአለም ሲደርሱ እንታዘባለን ጥሩ ዜናዎች ግን ከቤት አልፈው ጎረቤት እንኳን መሰማት ሳይችሉ ይቀራሉ፡፡ ይህ መልካም ዜና ግን ለአለም ይደርስ ዘንድ ብዙዎች ፅፈውላታል እኔም እፅፍላታለሁ፡፡ በወዳጄ ሳምሶን ጥቆማ ነበር የዚህችን ሴት ታሪክ የሰማሁት በእውነትም በንግግሯ ተደስቼ በተግባሯ አመስግኛታለሁ፡፡ እንግዲህ ‹‹ውይ ሴት የለም ዘንድሮ›› ‹‹ፍቅር ምድር ላይ አለ እንዴ›› የምትሉ ይህ ማረጋገጫ ይደርሳችሁ ዘንድ ፃፍኩላችሁ፡፡

......ይህች ሴት በጣም የምትወደውና የምታፈቅረው የምትሳሳለት ጆን ፔር አዳምስ የተባለ ባል ነበራት፡፡ ጆን ታዋቂ የፈረንሳይ የእግር ኳስ ተጫዋች ነበር፡፡ በ1982 ዓ.ም ላይ አሞኛል ብሎ ሆስፒታል ይገባል ታዲያ ህክምና ላይ በተፈጠረ ስህተት ምክንያት ራሱን ስቶ ኮማ ውስጥ ይገባል፡፡ ታዲያ ይህች የተባረከች ሚስት ከአይኑ ውጪ ሙሉ አካሉ የማይንቀሳቀስ ባሏን በትጋት ታስታምመዋለች ታፀዳዳዋለች ታጥበዋለች ሁሉንም ነገር የምታደርገው እሷ ናት እሱ ከአይኑ ውጪ የሚንቀሳቀስ ነገር የለውም አያወራም ቀን በቅን ታስታምመዋለች፡፡ ታዲያ ይህንን ያደረገችው ለአንድ ቀን አይደለም ለሁለት ቀንም አይደለም ለ33 አመታት ያለመታከት ነው እንጂ፡፡ ዛሬም ድረስ በይድናል ተስፋ በሏን የህይወቷን እውነት ትንከባከበዋለች፡፡አሁን አልጋ ላይ እንዳለ እድሜው 67 አመት ደርሷል፡፡ ስለ ባሏ በአንድ ጋዜጠኛ ተጠይቃ ‹‹ባሌ ላይ የህክምና ስህተት የሰሩትን ዶክተሮች ከስሻቸው የተወሰነ እስርና የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸው ወደስራቸው ተመለሱ ባሌ ግን ወደህይቱ አልተመለሰም እኔ ለባሌ በተቻለኝ መጠን ሁሉ ነገር እንደቀድሞው እንዲመለስ እጥርለታለሁ ሁሌም አጥበዋለሁ ልብስ እቀይርለታለሁ ጠዋት አልብሼ አብልቼው ቴሌቪዥን ከፍቼለት ወደስራ እሄዳለሁ›› አለች፡፡ ጋዜጠኛው እጅግ ተደንቆ እንዲህ ሲል ጠየቃት ‹‹ግን ለ33 አመታት ለውጥ ያላሳየን ሰው መንከባከብ አይከብድም?›› ሚስትም እንዲህ ስትል መለሰች ‹‹ለምን ይከብዳል ባሌ እኮ ነው ፡ ግን 33 ዓመት ሞላው እንዴ? ከተኛ ስንት አመት እንደሆነው አስቤ አላውቅም ካንተ ነው የሰማሁት›› ጋዜጠኛው ቀጠለ ‹‹ታናግሪዋለሽ የሚሰማስ ይመስልሻል›› ‹‹አዎ ይመስለኛል ሁሌም ፊቱ ቁጭ ብዬ አወራለታለሁ እቃ ስረሳ አይኑን ያርገበግብልኛል በዚህ ይገባኛል›› አለች፡፡ተመልከቱ ታዲያ እውን ሴት የለም? ታዲያ ፍቅር የለም? ላይክም ካደረግን ይህንን ነው ሼርም ካደረግን ይህን ዜና ነው ይህ የመልካም ፍቅርን ዜና አለማችን ተጠምታለች ለአለማችን እንዲህ አይነት ጥሩ መልካም የፍቅር ዜናዎች ያስፈልጓታል ቀን በቀን ችግርና መከራ እየተቀባበልን እያራገብን በሚወጣው የጥፋት ንፋስ ኑሯችን ቁልቁል እየሄደ ነው፡፡ ይህን የዚህች ሴት እና የዚህች አይነቶችን ጥሩና መልካም ዜና እየተቀባበልን አለምን በመልካም ስራ ዜና እናራግባት ያኔ የፍቅር ንፋስ በመውደድ ከፍታ ያኖረናልና፡፡!!
መልካም አዳር !
ሼር !
Pages: 1