ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Government. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 03-07-17, 06:40 pm


Karma: 90
Posts: 286/879
Since: 02-29-16

Last post: 34 days
Last view: 34 days
የገበያ ርሃብ እና የደሞዝ ጭማሪው

የሀገራችን አባባል ነው፡፡ አንዱ ፤ እናቴ ጎጆ ልወጣ እፈልጋለሁ ይላታል፡፡ እረ ልጀ የጎጆ ቀዳዳው እኮ ብዙ ነው ትለዋለች፡፡ ልጅም የለም እናቴ በሳር እደፍነዋለሁ ብሎ አለ፡፡ ጎጆ በሳር ተደፍኖ የኑሮ ብርዱን ፤ የመስማማት ንፋሱን ፤ የመተማመን ወጮፉን ፤ የመነጋገር ቁሩን ፤ የመሸከም አቅም የለውም፡፡

129 በመቶ እስከ 50 በመቶ የፈለገው ጭማሪ ቢኖር ፤ የማይጨመር ገቢያ ፤ የሚረጋጋ ሸቀጥ ማግኝት ከባድ ነው፡፡ የገበያ እርሃብ ደግሞ የከፋ ነው-- እያለ አለመግዛት መቻል ፤ እያዩት አለማግኝት ፤ ቦርሳ ሙሉ ብር ይዞ ፤ ባዶ ዘምቢል ጋር መመለስ፤ በራስ ለመያዝ ካነሰች ቋጠሮ ጋር መመለስ ፤ መመለሸያ የሌለው የግሺፈት መንገድ እየመሰለኝ ከለመድኩት ድህነት (በልቶ ማደር) ጋር እንደተፋቀርን ብንኖር ይሻል ይሆን ፤ ሌላ ህይዎት ላለመልድ ባይነካኩን እያልኩ ነው፡፡ ደሞዝ ጭማሪው ደስታ ሳይሆን ስጋት ነው ለኔ ፤ ጭማሪ ባለን ነገር ላይ አዲስ ለውጥ የሚያመጣ ሲሆን እንጅ ፤ ያለውን ጠራርጎ የሚውስድ ሲሆን የገበያ ፈረሰኛ ወይም ውሃ ሙላት ነው፡፡ ውሃ ሙላት ድግሞ ነፍስ ይቀማል፡፡ ንብረት ያወድማል፡፡ የኑሮ ውድነት መንስኤ እንዳይሆን የሚያስረዳኝ ምሁር ፤ ሚገልፅልኝ አጣሁ ፡፡ብቻ ወገኔ የሚነግረኝ፤ ‹‹ሳላገኝሁ እያጣሁ ነው›› የሚለውን ነው፡፡
የኑሮ ውድነት፤ የተለያዩ የፖለቲካ ርዕዮተዓለም ተከታዮችን፣ የመንግሥት (የአውራው ፓርቲ) አባላትንና ደጋፊዎችን፣ ተቃዋሚዎችን እና “መሀል ሠፋሪዎችን፣” በአጠቃላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በአንድ የሚያሰልፍ ፖለቲካዊ ችግርም ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም፡፡ የአቶ መለስን ርዕይ ዳር እናደርሳለን ስንል፣ “ድህነት ዋነኛው ጠላታችን ነው” ያሉትን እየረሳን አይደለም፡፡
ስለዚህ ዘመን የኑሮ ውድነት ለማወቅ መቼስ የግዴታ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ (ኢኮኖሚስት) መሆን አይጠይቅም። እኔ እንደምገምተው በአቅራቢያችን ወደሚገኝ ሱቅ ሄደን ትላንት የገዛነውን ዕቃ ዛሬ ደግመን ብንጠይቅ የዚያን ጊዜ አንድ ኢኮኖሚስት መጽሐፍ አገላብጦ ከሚያገኘው “ፅንሰ ሃሳብ” በላይ “ተግባራዊ” ዕውቀት ማግኘት የሚቻል ይመስለኛል። እንዲያውም በየታከሲው ውስጥ የሚጋገረው እና የሚቦካው እሱ ነው።
የኑሮ ውድነት፣ የመግዛት አቅም መዳከም፣ የአቅርቦት መመናመን፣ የጥራት መጓደል፣ ስርዓተ አልበኝነት የነገሰበት የግብይይት ስርዓት አጅበውት እንዳይመጡ ባልሰገ ለኔ ቂልነት ነው፡፡ መንግስትም በሚዲያ ቀርቦ ከጭማሪው ውጭ የነገረኝ ቃል የለም፡፡ የሀገሬ ሚዲያዎች አጀንዳ መቅረፅ ቸገራቸው እንዴ ፡፡
ለማንኛውም በብዙ ገንዘብ ምሃል ከሚራብ ገበያ ይሰውራችሁ፡፡ ገበያ ሲራብ እና አንጀት ሲታጠፍ ማጠፊያው ከባድ ነው፡፡
በአየለ አዲስ
Pages: 1