ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Law Enforcement & Police . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 03-06-17, 07:01 pm


Karma: 100
Posts: 189/426
Since: 07-12-15

Last post: 6 days
Last view: 6 days
‹‹ልጄን ነጠቀኝ! … አበባዬን ነጠቀኝ!›› / A 17 years old girl cost her life tragically
• የሴቶች ጥቃት በሃና ላለንጎ አላቆመም!
የካቲት 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ (ከሜክስኮ አደባባይ ወደ ዲ አፍሪክ ሆቴል) አቅራቢያ - ብሔራዊ የአልኮሆልና አረቄ ፋብሪካ በር ላይ አሳዛኝ የወንጀል ድርጊት ተፈፅሟል፡፡
በጠራራ ፀሐይ ‹‹አፈቅርሻለሁ!›› በሚል ወጣት የ17 ዓመቷ ተማሪ ኑሃሚን ጥላሁን በስለት ተወግታ መሞቷን ፖሊስ አረጋግጧል፡፡ ተጠርጣሪ ወንጀለኛውንም አስሮ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን ወንጀል ምርመራ ግድያ ክፍል አስታውቋል፡፡
ሟቿ - የቦሌ ኮሙኒቲ የሕዝብ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪ ነበረች፡፡ ከትምህርት ቤት ስተመለስ፣ ቦርሳዋን እንዳነገተች - እንደወጣች ቀርታለች፡፡
ኑሃሚንን ሕዝብ ተባብሮ ባልቻ ሆስፒታል አድርሷት የነበረ ቢሆንም በሕክምና ጥረት ሕይወቷን ለማትረፍ የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ በዚህን ጊዜ በሆስፒታል ግቢ የፈሰሰው ሕዝብ በዋይታ - በእንባ ሲራጭ ማምሸታቸውን ያነጋገርኳቸው የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
የወንጀሉ ድርጊት የከተማችን መነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል፡፡ #Talk of the town
***
ሜሪ ታደሰን #Merry Tadesse ተከትለን ዲ አፍሪካ ሆቴል ፊለ ፊት በምትገኘው መንገድ ተያይዘን ሀዘንተኞቹ ቤት ውስጥ ገባን፡፡ጎረቤት አነጋገርኩ፤ ‹‹እንደምትመለከተው እናትና ልጅ በቀበሌ ጠባብ ቤት ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡ … ነገን ተስፋ አድርገው እጃቸውን ለጠመዘዘው ድህነት፣ ችግር ሳይበገሩ በሰላምና ፍቅር ተሳስበው፣ ድምፃቸው ሳይሰማ ይኖሩ ነበር፡፡ ልጅቷ ደግሞ በባህርይዋ ዝምተኛ ነበረች፡፡ ከግቢው ልጆች ጋር እንኳ ተቀላቅላ የምትጫወት ልጅ አልነበረችም››
የትምህርት ቤት ጓደኞቿ ደግሞ ‹‹አንድ ዓመት ሙሉ ይከታተላት ነበር፡፡ በጣም ሲያስቸግራት እንደነበረ እናውቃለን››
***
እናቷ ወይዘሮ ወይንሸት ወዳጅ ሀዘን በሰበረው ድምፅ፤ ‹‹ … ልጄን ነጠቀኝ! … አበባዬን ነጠቀኝ! … እህቴን፤ ጓደኛዬን ነጠቀኝ! … እህህህ … አቧቷ በአንድ ዓመት ከስድስት ወራት እድሜ ላይ በሞት ተለይቷታል፡፡ ተለይቶናል፡፡ … ብቻዬን፤ እናትም አባትም ሆኜ በችግር አሰደግኋት፡፡ … የሀገር ልብስ ተደፍቼ እየሠራሁ፡፡ … የነገ ተስፋዬ በእርሷ ነበር፡፡ የምለፋው፣ የምደክመው የእርሷን ሕይወት ለማደላደል ነበር … እህህ … ወላድ ይፍረደኝ … የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ … ልጄን ነጠቀኝ! … አበባዬን ነጠቀኝ …
እረ ልጄን መልሱልኝ!
እረ አበባዬን መልሱልኝ! …
***
የእጅ ስልካቸውን ቁጥር ተቀብለን እያለቀስን ከግቢው ወጣን፡፡
***
ወዳጆቼ ሆይ! …ሀዘኑ የሁላችንም ነው፡፡ የሴቶችን ጥቃት የምንቃወም ሁሉ ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግ መልዕክታችንን እናድርስ፡፡
Pages: 1