ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Cooking & Recipes . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 02-25-17, 11:48 pm (rev. 2 by  ማማዬ on 04-28-17, 01:04 am)


Karma: 100
Posts: 61/95
Since: 08-19-16

Last post: 197 days
Last view: 197 days
የሚያስፈልጉ ነገሮች
----------------

1 በፈላ ውሃ ተልጦና ታጥቦ ደቆ የተከተፈ የበግ ወይም የፍየል ጨጓራ
2 ደቆ የተከተፈ ጉበት
3 ደቆ የተከተፈ ኩላሊት
4 ደቆ የተከተፈ የጎድን ስጋ
5 ደቆ የተከተፈ ላት
6 ደቆ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
7 ፍሬዉ ወጥቶ ደቆ የተከተፈ ቃሪያ
8 ደቆ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት
9 ተቀምሞ የተፈጨ ሚጥሚጣ
10 የተነጠረ ለጋ ቅቤ
11 የተፈጨ ቁንዶ በርበሬ
12 የተፈጨ ኮረሪማ
13 የሎሚ ጭማቂ ወይም ኮምጣጤ
14 ጨው
15 ዘይት
16 ቀዝቃዛ ውሃ
17 ማቀላቀያ እቃ

አሠራር
------
ጨጏራዉን ብቻ በማስቀረት በላዩ ላይ ያሉ አላስፈላጊ ነገሮች ሁሉ ታጥበዉ በቢለዋና በእጅ በመጠቀም ማስወገድና ማጠብ ጨጏራዉን ጎመድ ጎመድ አድርጎ ማስቀመጥ

ጉበቱንም ሀሞቱን ከላዩ ላይ ቆርጦ መጣል እና ጉበቱን ዙሪያውን በቢለዋ ቀስ ብሎ መታ መታ በማድረግ የቨፈነዉን ስስ ሽፋን ልጦ መጨረስ ከውስጡ ያለውን ሥራ ሥር ከጉበቱ ለይቶ ጉበቱን ብቻውን ማስቀመጥ

ኩላሊቱንም ሥጋውን የሸፈነውን ስስ ሞራ ነገር እና ከመሀሉ ያለውን ሥራ ሥር ለይቶ በማውጣት የኩላሊቶቹን ሥጋ ብቻ ማስቀመጥ

የሽንጥ ሥጋውንና ላቱን ድቅቅ አድርጎ ከትፎ ለየብቻ ማስቀመጥ

በርከት ያለ ውሃ በብረት ድስት በማፍላት ተራ በተራ የጨጏራውን ጉማጅ ጫፉን በእጅ ወይም በመቆንጠጫ እንዳያቃጥል በመያዝ እፈላው ውሃ ውስጥ ለሰከንድ ወጣ ገባ እየተደረገ በፍጥነት እመክተፊያ ላይ በማድረግ እያገላበጡ ለበጉ ምግቡን ይፈጭለት የነበረውን ክፍል ነጭም ይምሰል ጥቁር ልጦ መጨረስ ውሃው እየፈላ ጨጏራዉን ለብዙ ሰኮንዶች ብናቆየው ይገነትርና አይላጥልንም ስለዚህ በጥንቃቄ በፍጥነት ተልጦና ታጥቦ እንደ እንጀራ በመጠቅለል በጣም በቀጫጭኑ መቁረጥ የተቆራረጡትንም ቀጫጭን ጨጏራዎች ሰብስቦ በትንንሹ አድቅቆ ከትፎ ለብቻው ማስቀመጥ

ጨጏራው ሲከተፍ ጠንካራ ስለሆነ እንደ መፍትሔ ውሃ በብረት ድስት እሳት ላይ በመጣድ ትንሽ ጨውና ታጥቦ ተልጦ የተዘጋጀውን ጨጏራ በጣም እዳይበስል ገንተር በማድረግ ከውሃው ለይቶ በማውጣት ሲቀዘቅዝ መክተፍ አከታተፉን ቀላል ያደርገዋል

በዚህ መልኩ አመቻችተን ያስቀመጥናቸውን የሥጋ ዓይነቶች ሁሉንም ድቅቅ አድርጎ ከትፎ ለየብቻ ማስቀመጥ ለየብቻ ማስቀመጥ ያስፈለገበት ምክንያት አበሳሰላቸው የየቅል ወይም እኩል ስለማይበስሉ ነው

አበሳሰል
------

ለብ ለብ
-------
ከጨጏራው በስተቀር ሁሉንም ለብ ለብ አድርጎ አንድ ላይ ጎድጎድ ባለ ዕቃ ማስቀመጥ የተከተፈውን ቀይና ነጭ ሽንኩርቱን አንድ ላይ እዳይጠቁር አድርጎ በትንሽ ዘይት ማቁላላ ሽንኩርቱ ትንሽ ጨምደድ ሲል የተከተፈውን ጨጏራ በመጨመር ያለውሃ መጥበስ ሲበቃዉ ለብ ለብ ተደርገው የተቀመጡትን የዱለት ሥጋዎች ጭምቅ አድርጎ በውስጣቸው ያለውን ፈሳሽ በማስወገድ ከተጠበሰው ጨጏራ ጋር ማቀላቀል ሚጥሚጣ ፣ለጋ የተነጠረ ቅቤ፣ ቁንዶ በርበሬ፣ ትንሽ ኮረሪማና ጨው ጨምሮ ማውጣትና ለምግብነት ማቅረብ ይቻላል

ሌላው አሰራር
-----------

አስፈላጊው ነገሮች ተመሳሳይ ሆነው የተከተፉትን የዱለት ሥጋዎች ሁሉ ውሃ እዳይወልዱ በጋለ መጥበሻ ወይም ብረት ምጣድ ላይ ሁሉንም አንድ ላይ ጨምሮ ቶሎ ቶሎ በማማሰል ቅመሞችንና ማጣፈጫዎችን ወዲያው ጨምሮ በማዋሃድ ውሃ ሳይወልድ ፈጥኖ በማውጣት በትኩሱ ለምግብነት ማቅረብ

ለዱለት ማሳሰቢያ
--------------

- ጨጏራ ሳይላጥ መስራት ይቻላል
- የፈለገ አንጀት መጨመር ይችላል

Pages: 1