ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 3 guests | 2 bots
Pages: 1
Posted on 02-20-17, 05:51 pm (rev. 1 by Melat on 02-20-17, 05:52 pm)


Karma: 100
Posts: 182/426
Since: 07-12-15

Last post: 6 days
Last view: 6 days
የዘመኑ አፍቃሪ

እኔ አፍቅሬሻለሁ…
እንደ አሜሪካ አፈር
እንደ ሳምሰንግ ሰቨን
እኔ አፍቅሬሻለሁ…
እንደ አርሴናል ክለብ
እንደ ሜሲ ጥበብ
እኔ አፍቅሬሻለሁ…
እንደ እንግሊዝ ፓውንድ

እንደ ናይኪ ብራንድ
እኔ አፍቅሬሻለሁ….
እንደ ቱርክ ሲኒማ
እንደ ቃና ቻናል
ብዬ መናዘዜ
አልገባሽም አይደል!
…እሺ ምን ላ’ርግልሽ?
ከዝሆን ድድ ላይ
ቀንጣጤ ሸርፌ፣
ከጥር፡ኝ ብብት
ዝባዷን ጨልፌ
ከነብር ገላ ላይ
ቆዳውን ገፍፌ
ከብሄራዊ ባንክ
ወርቅ፣ እንቁ ዘርፌ
ከአራት ኪሎ ግቢ
ሹሞቹን አፍኜ
ልላክልሽ ይሆን
ኮማንድ-ፖስቱን ጭኜ?
(ቂ ቂ ቂ ቂ ቂ ቂ)
ተይ እኮ ንግስቴ
ተይ እኮ የኔ ውድ፣
ፍቅር ከአልጋ ዘሎ
መቃብር እስኪወርድ
እኔ አንቺን ሳፈቅር
እኔ አንችን ስወድድ
ጀብዱን ተይውና…
እንደ ቃና ቻናል
እንደ እንግሊዝ ባውንድ፡፡
Pages: 1