ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Family. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 01-16-17, 01:19 pm


Karma: 90
Posts: 181/879
Since: 02-29-16

Last post: 69 days
Last view: 69 days
ለ17 አመት ሙሉ የተጠፋፉትን አባትና ልጅን ያገናኘችው ታክሲ!

በትላንትናው ዕለት ይህች የምትመለከቷት ታክሲ ከቦሌ ድልድይ 12 መንገደኞችን አሳፍራ ወደ ቃሊቲ መናሃሪያ እየተጎዘች ነው ::አብዛኛው መንገደኛ መዲናችን አዲስ አበባን ለቆ ወደ ክፍለ ሃገር የሚጎዝ ነው::
ሁሉም መንገደኛ አጠገቡ ካለው ሰው ጋር እየተጨዋወተ ጉዞችንን ቀጥለናል አንድ እድሜው በግምት 45 አመት የሆነው ጎልማሳ አጠገቡ ከቆመው ወጣት ረዳት ጋር ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ፀጉሩ ድረስ በአግራሞት እየተመለከተው እየተጨዋወቱ ነው::
ጎልማሳው የረዳቱ ፀጉርና መልኩን በአትኩሮት ሲመለከተው ቁጭ እራሱን ይመስላል:: ጎልማሳው አሁን ጥያቄዎችን መጠየቅ ጀመረ"
ስምህ ማን ይባላል"?
ረዳቱ፥ ቢኒያም እባላለሁ::
ቢኒያም ማን? ደግሞ ጠየቀ
ቢኒያም ስዩም::
መለሰ ረዳቱ በዚህ ሰዓት ጎልማሳው ደነገጠ
ለመሆኑ የየት ሃገር ልጅ ነህ?
ረዳቱ በዚህ ሰዓት መልስ አልሰጠም ምነው ደጋግመህ ጠየከኝ ፓሊስ ነህ እንዴ? ሲል ጠየቀው::
አይ አይደለሁም ለማወቅ ፈልጌ ነው :: መለሰ ጎልማሳው
የተወለድኩት ደብረዘይት ነው ነገር ግን ከ10 አመቴ ጀምሮ የምኖረው እዚሁ አዲስ አበባ ነው ::
ለምን ከደብረ ዘይት ወጣህ? አሁንስ እዚህ አዲስ አበባ ከማን ጋር ነው የምትኖረው?
"ደብረዘይት እያለሁ አባቴ ገና በአምስት አመቴ ነው እናቴን ጥሎት ወደ ውትድርና ዓለም የገባው በዚህን ሰዓት እናቴ ምንም ነገር ስለሌላት ሰው ቤት እየሰራች እኔን ማሳደግ ጀመረች ልክ አስር አመቴ ሲሆን እኔን ወደ አዲስ አበባ እህቷ ጋር ጥላኝ አንዱን አግብታ ወደ አሰበ ተፈሪ ሄደች እኔም ከዛን ጊዜ ጀምሮ አክስቴ ቤት ነው የምኖረው" ሲል መለሰ::
የእናትህ ስም ማን ትባላለች?
መቅደስ ሽፈራው ትባላለች : :በዚህን ሰዓት ጎልማሳው ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ በታክሲ ውስጥ ያለው ተሳፋሪዎች ደነገጡ የታክሲ አሽከርካሪው መኪናውን ዳር ይዞ አቆመው ምንድነው የተፈጠረው? በማለት ሹፌሩ ጠየቀ
ጎልማሳው እያለቀሰ " ስዩም ተፈራ እባላለሁ የዛሬ 22 አመት ገደማ መቅደስ ሽፈራው የምትባል የፍቅር ጎደኛዬ ነበረችኝ ከእሷ አንድ ልጅ ወልጄ ኑሮ ስለከበደኝ ህፃኑ የ5 አመት ልጅ እያለ 1990 ዓ.ም የውትድርና ዓለምን ተቀላቀልኩኝ ከ8 አመት በሆላ ወደ ደብረ ዘይት ስመለስ ሚስቴም አግብታ ሃገር ለቃ ልጄን ይዛ ወደ ሌላ ሃገር እንደሄደች ሰማሁኝ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ሚስቴንና ልጄን እየፈለኩኝ ባዝኛለሁ ::
ይሃው በአጋጣሚ ከረዳቱ ጋር ስናወራ ሁሉንም ነገር ጠይቄው የሚነግረኝ ነገር ሁሉ የኔ ልጅ መሆኑን ነው ከዚህም በተጨማሪ እንደምትመለከቱት ፀጉሩም የፊቱም ገፅታ እኔን ነው የሚመስለው ስለዚህ ከ17 አመት በሆላ እዚህ ታክሲ ውስጥ ልጄን አገኘሁት ለዚህ ነው የማለቅሰው" በማለት ከረዳቱ ልጃቸው ጋር እየተለቃቀሱ ተቃቃፉ ተሳፋሪዎቹም በጭብጨባ አጀቦቸው::
ለ17 አመት የተጠፋፉት አባትና ልጅ ታሪክ ይሄን ይመስላል:: ፍቃደኝነታቸውን ጠይቀን ፎቶቸውንና ቪዲዮቸውን ለእናንተ የምናቀርብ ይሆናል መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ::
Pages: 1