ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Marriage & Divorce . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 01-14-17, 03:43 pm


Karma: 100
Posts: 190/444
Since: 07-20-15

Last post: 67 days
Last view: 67 days
ባልና ሚስት ከተጋቡ አራት አመታት ተቆጥረዋል ግን ልጆችን
መውለድ አልቻሉም ነበርና ወደ ሀኪም ቤት ችግሩን ለማወቅ
ይሄዳሉ አስፈላጊውንምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው
ተነግሯቸው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ፣ የምርመራውን ውጤት
ለመስማት ባል ወደ ሃኪም ቤት ቀድሞ ያመራል ዶክተሩ ጋር
ሲገባ የተነገረው ውጤት እጅጉን አሳዛኝ ነበር ባለቤቱ መውለድ
አትችልም መሃን ናት ባል የሰማውን ዋጥ በማድረግ እግዜርን
ያመሰግናል ፣ ለዶክተሩም እንዲህ ይለዋል
(ባለቤቴን ይዜ እመጣለው ግን ስትመጣ መውለድ
እንደማትችል አትንገራት ይልቁንስ እኔ መውለድ እንደማልችል
አሳውቃት) በማለት ለምኖ ያሳምነዋል።
ዶክተሩም ባል ያለውን እሺ ባማለት ለሚስት ባለቤትዋ
መውለድ እንደማይችል እና ተስፋቹ አንድ እግዜርን ብቻ
መማፀን ነው ሲል ከምክር ጋር ውጤቱን ያሳውቃታል ፡ ብዙም
አልቆየ ይህ ወሬ በባልና ሚስት ቤተሰቦች ዘንድ ይሰራጫል፣
በዚህ መልኩ ለአምስት አመታት ያህል ከኖሩ በኋላ ሚስት
ለባል ከዛሬ ጀምሮ ከሱ ጋር መኖር እንደማትችል እና ዘር
ፍሬዋን ልጆችዋን ወልዳ ማየት እንደምትፈልግ ትነግረዋለች
፣ባል በጣም ሀዘን እየተሰማው ይህ የእግዜር ውሳኔ ነው እባክሽ
በእግዜር ላይ ያለሽ ተስፋ የጠነከረ ይሁን በማለት ነገሩን
ለማርገብ ይሞክራል እሷም ጥሩ ይህንን አመት እታገሳለው ከዛ
በኌላ ግን ከኔ ጋር ትቆያለች ብለህ እንዳታስብ ትለዋለች።


እሱም በእግዜር ተስፋውን አስጠግቶ ይስማማል በዛው አመት
ሚስት በኩላሊት በሽታ ትጠቃለች ሀኪሞችም ግዴታ ኩላሊቷ
መቀየር እንዳለበትና ካልሆነ ነገሮች ሊከብዱ እንደሚችሉ
ይነግሯታል፡ ሚስትም ይህንን ስትሰማ ወቀሳዋን በባል ላይ
አጠናክራ ቀጠለች ሰበቡ አንተው ነህ ፍታኝ ኑሮዬን ልኑርበት
ስልህ እምቢ ብለህ ብዙ ወቀሰችው በዚህ ወቅት ባል ባለቤቱን
አስፈቅዶ ኩላሊት በፍቃደኝነት ለባለቤቱ የሚሰጥ ሰው
ለማፈላለግ ከሀገር ውጭ እንደሚሳፈር ይነግራት እና ተሰናብቶ
ከሆስፒታል ይወጣል ብዙም አልቆየ ከሳምንት ቦኌላ ይደውላል
፣ ኩላሊት የሚሰጥ ሰው አግኝቻለው አብሽሪ በማለት
ያበስራታል።
አንድ የአረብ ሀገረ ተወላጅ ወጣትም ያለችበት ሆስፒታል ድረስ
መጥቶ ኩላሊቱን ሊሰጣት ፍቃደኛ የሆነው እሱ መሆኑን
ይነግራታል፡ ቤተሰብ ሁሉ ተደሰተ ምስጋነው ዘነበበት ለነገሩ
ኩላሊቱን የሚሰጠው በእርግጥ ባል እንጂ ይህ ወጣት
አልነበረም ሚስት እና ቤተሰብ እንዳያውቁ የተጠቀመው ዘዴ
ነበር ፡ባልም አስፈላጊውን የቀዶ ጥገና ከተደረገለት በኌላ
ኩላሊቱን ለሚስት ይሰጥና የኩላሊት ዝውውሩ በተሳካ መልኩ
ይጠናቀቃል፡፡
ብዙም አልቆዪ ሚስት የመጀመርያ ልጅዋን መፀነስዋን
ታውቃለች!!!
በ ዘጠነኛው ወር የመጀመረያው ልጅ ተወለደ ቤተሰብ ሁሉ
በደስታ ተዋጠ ፥ ይህንን ሁሉ በቀን ውሎው መዝገብ ላይ ግን
ከማስፈር ባል አልተዘናጋም ነበር በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ አንድ
ቀን በቤት ውስጥ ካለ ጠረጴዛ ላይ ይህንን መዘገቡን ረስቶ
ጥሎት ከቤት ይወጣል ሚስትም አንስታ ማንበብ ትጀምራለች
ያኔ ነበር እውነታው ሁሉ የተብራራላት በለቅሶ ተዋጠች ወዲያው
ባል ጋር ደውላ ተንሰቅስቃ እውነታውን እንዳወቀች አስረዳችው
እሱም እያለቀሰ ምን ያህል እንደሚወዳት ነገራት፡፡
ታሪኩን ፀሀፊው ባልም ሚስቱ ለሱ ካላት ክብር እና ከፍተኛ
ወዴታ የተነሳ ከዛ ቀን ጀምሮ ቀና ብላ በሙሉ አይኗ ደፍራ
እንዳላየችው በመግለፅ ለባለፉት አስር አመታት ብቻውን ያለቅስ
እንደነበር እና እምባውን ይጠርግለት የነበረ ሰው እንዳልነበረ
እና ዛሬ ባለቤቱ ስታለቅስ አይዞች በማለት እምባዋን
እንደሚያብስላት ይናገራል።
ለወዳጅዎ ሼር በማድረግ ያካፍሉ
ተጨማሪ ቁም ነገር አዘል ጽፎችን ከፈለጉ ፔጃችንን ላይክ
ያድርጉ
Pages: 1