ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Marriage & Divorce . | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 11-24-16, 01:32 pm


Karma: 100
Posts: 55/94
Since: 08-19-16

Last post: 269 days
Last view: 75 days
ጋብቻን ለመመስረት ልናውቅ የሚገባቸው ጎጂ እና ጠቃሚ ነገሮች
ጎጂ ናቸው የምንላቸው ነገሮች
1. በቁንጅና
2. በገንዘብ (ሀብት)
3. በአለባበስ
4. በአነጋገር (ጥሩ አንደበት)
ጠቃሚ ናቸው የምንላቸው ነገሮች
1. ቁንጅና
2. የቤተሰብ ሁኔታ
3. እኩያነት
4. ጥሩ ስነ ምግባር
ጎጂ ተግባራት እንዴት ጎጂ ተባሉ
- ጋብቻን በመልክ ቁንጅና ብቻ ከመረጥን ለኑሮአችን ወረንጦ የሆነች ከሆነ የወደድነው ቁንጅናዋን ብዬ የሚያምረን ሳይሆን በጣም የሚያስጠላን ሆኖ ይገኛል፡፡
- ሀብታም ነው/ነች ብለን ከመረጥን ሁሉ ነገር እንደነበር ካልሆነ መለኪያችን ተበላሽ ጭቅጭቅ ያመጣል የጭቅጭቅ ውጤቱ ግልጽ ነው
በአለባበስ ፡ የተፈቀረ የተፈቀረች ትዳሩ ሲጀምር የኑሮ ውጣ ውረድ የአለባበስ ሁኔታን ያበላሸዋል ስለዚህ በእይታ መጠላላትን ያመጣል
በጥሩ አንደበት እንደበቷ የተፈቃቀሩ ተጋቢዎች ልብስ እርቃናችንን እንደሚሸፍንል ሁሉ አንደበታችንም የእኛነታችንን ይሸፍንልናል ውስጣችን መጥፎ ባህሪ ያለንን ከሆንን በአንድ ጣሪያ ስር ስንኖር ጎልቶ ይወጣና ለትዳር ጠንቅ ይሆናል፡፡
ለጋብቻ ጠቃሚ ናቸው የምንላቸው
- ቁንጅና ለሁሉም ሰው ለሁሉም ቆንጆ አይደለም ለጋብቻ ለሚመርጣትና ለምትመርጠው እርስ በእርሳቸው ቆንጆዎች ናቸው ቁንጅናን የሚያጠናክሩ ነገሮች አብረው ሲኖሩ ነው ማለት ነው
እርሱም፡ ጥሩ ምግባር ካላቸው እናት አባት መውለድና አብሮ ማደግ ይህም ትልቅ ቁንጅና ነው ምክንያቱም የቤተሰብ ጥሩ ምግባር ይወረሳል
እኩያነት በሥነ ልቦና በተፈጥሮ የምናገኘው ባህሪ ከአካባቢ ከወረስነው ባህሪ ከት/ቤ ከወስድነው ባህሪ ወዘተ የወረስነውን ባህሪ አደባላልቆ ተዋውጦ መኖር መቻል ይህም ቁንጅና እና ባህሪ እኩያን ነው፡፡
- ስነ ምግባር በተጋቢዎች መሀል እጅግ በጣም ጥሩ የሆኑ ሥራዎች ሁሉ ሁለቱም በእኩል ደረጃ መሰረት አለባቸው ይህ በትክክል በተግባር እየተተረጎመ ሲኖር ይህ እስከመጨረሻው መዝለቅ እንዲችል ተጋበዊቹ ሊያደርጉትና ሲኖሩ ከዚህ የበለጠ ስነ ምግባር ቁንጅና ምን አለ አምባቢዎ ከመጣጥፉ መረዳት እንደተቻለው ጥሩ ባልና ጥሩ ሚስትን ለማግኘት በችኮላ ቆንጅናት ቆንጆ ነው ወዘተ .. በሚል ለተጋቢዎችም ሆነ ለሚወለዱት ልጆች መጥፎ እልል እንዳያጋጥም እግዚአብሔር ይዞ ማስተዋልና በእርጋታ መወሰን ውጤታማ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ብዙ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩባት ሀገር ነች
ብሔረሰቦቿ እያንዳንዳቸው የራሳቸው የሆነ አኗኗር ባህል አላቸው
እነርሱም ፡ ሀ የጋብቻ
ለ/ የአለባበስ
ሐ/ የአክብሮት
መ/ የአመጋገብ ስርአት
ሠ/ እንግዳ አቀባበል
ረ/ አብሮ የመብላት
ሰ/ የመደጋገፍ
ሸ/ የመመካከር .. የመሳሰሉ
ለሱ እጅግ በጣም ጥሩ ባህሎች አላቸው በጣም የሚገርም የድሮ የጋብቻ አመራረጥ ነው፡
ብዙ ብሐየረሰቦች ሴት ልጅ ለጋብቻ መጀመሪያ ሊጠይቁ በራሳቸው ወግና ስርአት ነው፡፡
ዛሬ ላወራችሁ የፈለኩት አብዛኛው የአማራው ክልል ወንድ ልጅ ትዳር መያዝ አሁን እችላለሁ ተዘሃጀቻለሁ ብሎ አይደለም ሁለቱም ተጋበዎች ስለትዳር (ስለ ጋብቻ ) የሚያውቁት የለም
የሁለቱም ትዳር መራጮች ወላጆች ናቸው ፡፡
አይገርምም ይህ ለምን ሆነ ?
ወላጆች
1. የጥንቶቹ ወላጆች የራሳቸው የጋብቻ ሁኔታ ልጅህ ለልጄ በሚል የጋብቻ አጠያየቅ የተጋቡ ስለሆነ ልጆቻቸውንም እነርሱ ባለፉበት ጎዳና ሳይቀንሱ ሳይጨምሩ እንዲጓዙ ያደርጋሉ
2. የሀብት ጥገኝነትን ፍለጋ
3. የወላድ ዘርን ፍላጋ
በዚህ ምክንያት ወንዱም ከሴቷ ቢሻልም የባሰ በሴቷ ላይ የሚደረገው ከእናቷ ማህፀን ውስጥ እያለች ልጃችሁ ሴት ከሆነች ለወንድ ልጄ ዳሩልኝ ተብሎ ሽማግሌ ይላካም የሴት እናት አባትም ሁለቱ ቤተሰቦች ከተፈላለጉ ጋብቻውን ያጸድቁታል
ልጅቷ ወንድ ይሁን ሴት ትዝን ትጠብቃለች ሴት ከሆነች እስከ 7 አመት እናት አባቷ ቤት ታድጋለች ሰባት አነት እናት አባቷ ጋር ማደጓ በህግ የተደነገገ አይደለም ከፍ ዝቅ ሊል ይችላል፡፡
እንደ ቤተሰቦቻቸው መልካም ፍላጎት ነው፡፡
ጋብቻው በ 7 አመቷ ከተፈጸመ በዚህ እድሜዋ ከእናት አባቷ ቤት ወጥታ ከባሏ ቤተሰቦች ጋር መኖር ትጀምራለች
ለምን ከቧላ ጋር አትኖርም ?
በተጋቢዎቹ ፋንታ ጋብቻውን የፈፀሙት ቤተሰቦች ያለ እድሜ ጋብቻ መሆኑን አውቀው ለማካካሸ በአሁኑ እድሜዋ ከቧላ ጋር በተኛች ብለው ከ 2-3 ዓመት ድረስ ጥብቅ በሚል ስያሜ ከልጁ እናት ጋር እንድትተኛና እንድትኖር ይደረጋል፡፡
ይህ የተጨመረው እድሜ (አመት) እድሜዋን ለጋብቻ በቂ ያደርገዋል ማለት ነው ?
ይህን ይገርማል ብለን ብናልፈው ይሻላል
በዚህ እድሜ ልጅ ከወላጆቹ ተለይቶ አስቡት
1. የቤተሰብ ፍቅሯ
2. መብቷ
3. እውቀቷ
4. ወኔዋ
5. የኃላፊነት ችሎታዋ
6. የልጆቿ እጣ ፋንታ
7. የአካላ መበላሸት ወዘተ…
ከባሏ ቤተሰብ ጋር ስትኖር እንኳን ባሏ መሆኑን ሳታውቅ ቀርቶ እዛ ቤት ለምን እንደምትኖር አታውቅም ከቆይታ የራሳቸው ቤተሰቦች ይመስሏታል እሱንም ወንድም ጋሼ እያለች ትኖራለች ወንዱ ግን ስለሚያውቅ የተወሰነውን የዓመት ገደብ መቆየት ስለሚያቅተው መቆየት የሚችለውን ያህል ቆይቶ ገደቡን ለማፍረስ ይገደዳል ፡፡
ስለዚህ ከቤተሰቡ ደብቆ ይደፍራታል በዛን ጊዜ ስለሚያማት ምን ጉድ ነው ብላ ታለቅሳለች ትደነግጣለች ፍቅር ምን ማለት እንደሆነ ባለማታው ወዲያውኑ የጥላቻ መንፈስ ያድርግባታል ጥላ ትወጣለች ቤተሰብ እንድትኖር ይገፋፋታል የማትፈልግ ግን ከቤተሰቦቿ ተለይታ ርቃ ወደቡት የትዳር ፍቅሯም ይጠፋል ፡፡
ይህ አሁን አለ ወይ ?
አሁን ሙሉ በሙሉ ቀርቷል ለማለት ትክክለኛ መረጃ የለኝም ግን በአለኝ መጠነኛ እይታ በአብዛኛው ቀርቷል ማለት እችላለሁ፡፡
ታዲያ አይገርም !!!Pages: 1