ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Marriage & Divorce . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 11-21-16, 12:53 pm


Karma: 100
Posts: 54/94
Since: 08-19-16

Last post: 269 days
Last view: 75 days
ጋብቻን እስከ መጨረሻ ለማሳመር
---------------------------
ተጋቢዎች ሊተገብሩአቸው የሚገባ ሥርዐቶች
-----------------------------------
ጋብቻ ማለት በጣም ትልቅ የሆነ የስራ ፕሮጀክት ነው፡፡
በውስጡ ብዙ ጥሩ ጥሩ የሆኑ የኑሮ ጣፋጭ መንገዶች እየኖርን የምንጓዝበት ጎዳና ነው፡፡
በተጓዳኝ ካልሆነ ግን መራርና ጉርብጥ ጎዳና ነው፡፡
ማንኛውም ሰው መጀመሪያ ጓደኝነትን ሲጀምር ተዋዶና ተፋቅሮ ነው፡፡
በዚህ ሁኔታ የታገቡ ፍቅረኛሞች ወይ እስከመጨረሻው አብረው ይኖራሉ ወይም የማይኖሩ አሉ ኑሮ ሲጀምር በትዳር አለም ውስጥ ብዙ የሚተገብሩ ስራዎች ስለአሉ በዛ ምክንያቶች መግባባትም እንዲገኙ ስለ መግባባትም ይፈጠራል፡፡
አለመግባባት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ከሄደ አብሮ የመኖሩ ጉዳይ ቀስ በቀስ ሆድ በነገር እየሻከረ ይሄዳል መጨረሻው መለያየት ይሆናል፡፡
ይህ እንግዲህ ይህ ከባድ ያደርገዋል እንዴት ?
ተጋቢዎች ባለመግባባት ምክንያት በአአምሮና በአካል ላይ የሚደርሰው ጉዳት ሲታይ የተወለዱ ልጆች ከአሉ በጋራ የተያዘ ንብረት ከአለ በፍቅርና በጉጉት የተጀመረው ትዳር በእሬት ተለውሶ ሲፈርስ በቀላሉ የሚረሳ አይሆንም ልጆች ማደግ ያላባቸው ከእናት ከአባት ጋር ነው ይህ ሳይሆን ሲቀር ለልጆም ለወላጆችም በሕይወታችን ሙሉ ብዙ ደስታ አይሰጥም ጥቁር ነጥብ ጥሎ ያልፋል፡፡
ጋብቻ ያፈረሱ እንደገና ለማግባት ሲፈልጉ ልጆች በእንጀራ እናት ወይም በእንጀራ አባት ሊያድጉ ነው አዲስ የተጋቡት እንጀራ እናት ወይም እንጀራ አባት ያልወለዱትን ልጆች ሲያሳድጉ ሲመጡ እንጀራ እናት ወይም እንጀራ አባት ልጆች ሲወለዱ በቤተሰቡ ውስጥ በእናትና በአባት የሚለያዩ በእናት በአባት አንድ የሆኑ ልጆች የሚለያዩ በእናት በአባት አንድ የሆቡ ልጆች ተቀላቅለው ሊያድጉ ነው ማለት ነው ይህ መጀመሪያ ተጋብተው የተፋቱትን የኑሮ ሁኔታ ከባድ እና ምስቅልቅል ያደርገዋል የልጆቹንም እኗኗር የቤተሰቡንም ኑሮ ምስቅልቅልና አስቸጋሪ ሆኖ ያልፋል
ከላይ በጥቂቱ ይህንን ያህል ከተመለከትን ይህን እና ይህን የመሳሳሉ ሁኔታዎች በእኛ ላይ እንዳይከሰት ከመጀመሪያው በጥንቃቄ የጥሩ ትዳር ጓደኛን መጓዝ ነው፡፡
ታዲያ ማንም ሰው ይህ መጥፎ ሁኔታ እንዲያጋጥመው የሚፈልግ ሰው የለም
ስለዚህ ምን ቢደረግ ይሻላል!!
ይህንን ጠቃሚ ነው ብዬ ስጽፍ ውጤታማ የሚሆነው ከዚህ በታች የተዘረዘሩተን ጠቃሚ ነጥቦች በማስተዋልና ሰበእርጋታ በማንበብ አፈጻጸማቸውን በትክክል በጋራ ሲተረጎም ነው፡፡
ይህ ለተጋቢዎች ለልጆች፣ ለቤተሰብ፣ ለጓደኛ፣ ለህብረተሰብ እንዲሁም ለሀገር ይበጃል፡፡ ምክንያቱም ጥሩ ቤተሰብ ጥሩ ቤተሰብን ያዘጋጃል መከተልና መተግበር ያለብንን የስርአቶች ዝርዝር ከዚህ በታች እገልጻቸዋለሁ ፡፡
1. መከባበር 11. ታማኝነት
2. መተዛዘን 12. መረዳዳት
3. መተሳሰብ 13. በተሰብን በጋራ ማየት
4. ግልጽነት 14. ማህበራዊ ኑሮን በጋራ ማየት
5. መደማመጥ 15. ስለ ልጆች አስተዳደግ በጋራ መስራት
6. መማማር 16. ንብረትን በጋራ መጠቀም
7. መወያየት 17. ቂም አለመያዝ
8. መታገስ 18. ነገሮችን ሁሉ በትዕግስት ማራመድ መናገር ወዘተ … ናቸው
9. መቻቻል
10. መረታት
ሌላው ማት ማንኛውም ሰው በእኔ እምነት በተፈጥሮ የሚያገኘው በራሱ ጥሩም የሆነ መጥፎ ባህሪ አለ ብዬ አምናለሁ ተሳስቼ ከሆነ አንባቢዎቼ ታርሙኛላችሁ፡፡
ስለዚህ ለኑሮ የሚያስቸግር ትእግስት የሚያሳጣ መሸነፍንና የሰው ሃሳብ መቀበልን ወዘተ.. ያለመቻል ባህሪ ካለብን በተቻለ መጠን ለመተው መታገስንና መተው መቻል አለብን፡፡

Pages: 1