ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Cooking & Recipes . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 11-21-16, 12:35 pm


Karma: 100
Posts: 44/95
Since: 08-19-16

Last post: 197 days
Last view: 197 days
የበሶ ዱቄት አዘጋጃጀት
------------------
የሚያስፈልጉ ነገሮች
----------------
1. ፍሬው ወፍራም የሆነ ነጭ ገብስ
2. ለመቀለያ የሚሆን ብረት ምጣት
3. መፈተጊያ ሙቀጫ ወይም ወፍጮ
4. ማድረቂያ የሚሆን ስስ ምንጣፍ
5. ጉድጓዳ ዕቃ
6. ለብ ያለ ውሃ
7. ወንፊት
8. ሰፌድ
9. ዱቄቱን ማስቀመጫ ባለ ክዳን ዕቃ

አዘጋጀጀት
--------
ገብሱ በሰፌድ ተበጥሮ ተለቅሞ ከቆሻሻ ንፁህ ይሁን ገብስ አጓድጓዳ ዕቃ ውስጥ ለብ ያለ ውሃ ጨምሮ ገብሱን አንድ ላይ ከ 10 ደቂቃ ማራስ
ውሃው በወንፊት እየተጨለለበ በሙቀጫ መፈተግ ሲያልቅ ለማድረቅ በሚመች ስራ ዕቃ ለዘዝ ብሎ እስከሚደርቅበትን አድርጎ ፀሐይ ላይ ማስጣት ወዲያው ለዛዝ እንዳአለ ከንብብ ቆሎ ቀረት ያለው አበሳሰል በመጠቀም ቆልቶ መጨረስ፡፡
ቀጭ ብሎ የቀረውን ገለባና የአበሳሰል ችግር ማለት የተሰባረና የአረረ ገብስ ከአለ በሰፌድ ተበጥሮ መወገድ አለበት ይህ ካልሆነ የበሶው ዱቄት ጣዕምና ከለር ሊበላሽ ይችላል፡፡
ስለዚህ ንፁህ ቆንጆ ሆኖ መዘጋጀት አለበት በተጨማሪም አንደገና በድጋሚ ሳይበሽ ለምግብነት የሚቀርብ ነው፡፡
በዚህ መልክ የተዘጋጀውን የበሶ ቆሎ ማንኛውም ጥሬ እህል ባልተፈጨበት ንፁህ ወፍጮ መፈጨት አለበት ካልሆነ ከራሱ ቆንጥሮ አስፈጭቶ ወፍጮውን በማሟሸት ማስፈጨት ይቻላል ዱቄቱ በጣም መላም ወይም መድቀቅ አለበት፡፡
ይህን ዱቄት በደረቅና በንጹህ ዕቃ ውስጥ በመክተት ከድኖ ማስቀመጥና እንደአስፈላጊነቱ መጠቀም ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡ ካስፈለገ በጣም በማያስታውቅ ሁኔታ የኮረሪማ ቅመም ፍሬና ጨው ጨምሮ ማስፈጨት ይቻላል፡፡

Posted on 11-01-17, 07:53 am


Karma: 100
Posts: 4/5
Since: 12-15-16

Last post: 771 days
Last view: 770 days
ምን ቅመም ይጨመርበታል
Pages: 1