ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Cars. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 09-29-16, 11:57 pm


Karma: 90
Posts: 126/879
Since: 02-29-16

Last post: 6 days
Last view: 6 days
ስለ ባለ ማርሽ መኪኖች ጥያቄ አለኝ፣ እየነዳን ቁልቁለት ስንወርድ ማርሹን ወደ 0 መቀየር ይቻላል ቁልቁለት ስለሆነ ማለት ነው እንደገናም ቁልቁለት ስንወርድ እና ዳገት ስንወጣ መጠቀም ያለብን ማርሽ አለ ወይስ በማንኛውም መጠቀም እንችላለን
ከቻላችሁ እባካችሁ መልሱት
Posted on 09-30-16, 06:47 pm


Karma: 100
Posts: 62/610
Since: 08-27-16

Last post: 21 days
Last view: 9 days
የመኪና፡ማርሽ፡ሁለት፡ዓይነት፡ናቸው።
1ኛ፡የአንተ፡ፎቶው፡ላይ፡ያለው፡ሲሆን፡ማኑዋል፡ትራንስሚሺን፡ይባላል።ማርሽ፡ለመቀየር፡ሁልጊዜ፡ፍርሲዮኑን፡መርገጥ፡አለብህ።
ከዳገት፡ላይ፡የፍርሲዮኑና፡የቤንዝኑን፡አመጣጥነህ፡ካልረገጥህ፡መኪናው፡ወደኋላ፡ይሄድብህል። 3የእግር፡መርገጫ፡አለው።
እነርሱም፡የቤንዚን፡የፍሬን፡የፍርሲዮን፡ናቸው። ባትሪው፡ሞቶብህ፡ማስነሳት፡ካልቻልክ፡ከዳገት፡ላይ፡በስተቀር፡አያስገፋህ፡
ማስነሳት፡ትችላለህ። በኔ፡ግምት፡85በመቶ፡የአሜሪካ፡ሕዝብ፡መንዳቱን፡አያውቅበትም።ብዙ፡ጊዜ፡ፍርሲዮኑ፡ይቃጠላል።0 ብለህ፡
ያልከው፡ኒውትራል፡ይባላል፡ሲገፉልህ፡ኒውትራል፡ላይ፡አድርገህ፡ነው፡የምታስነሳው። በተረፈ፡ለጥቂት፡ጊዜ፡ቆም፡ለማድረግ፡ከአስፈለገ፡
ኒውትራል፡ላይ፡አድርገህ፡ፍሬን፡የዘህ፡ትቆማለህ።ከቆምክበት፡ለመሄድ፡መጀመሪያ፡1ኛ፡ማርሽ፡ከዚያም፡2ኛ፡ቶርክ፡ያላቸው፡ማርሽ፡
ሲሆኑ፡ለመብረሪያ፡ለእስፒድ፡ደግሞ፡3ኛ፡እና፡4ኛ፡5ኛ፡ትጠቀማለህ። በጣም፡ቁልቁለት፡ከሆነ፡2ኛ፡ማርሽ፡ወይም፡1ኛ፡መጠቀም፡
አለብህ፡እንደፍሬን፡ያገለግላል። ለቶርክ፡ዳገት፡ስትወጣ፡ከካምቢዮ፡ውስጥ፡ትንሿ፡ጊር፡ለምሳሌ፡10ጊዜ፡ስትዞር፡ትልቁ፡አንዴ፡ይዞራል፡
ማለት፡ነው።ለሩጫ፡ደግሞ፡መርሹን፡ስትቀይር፡ትልቁ፡ጊር፡አንዴ፡ሲዞር፡ትንሿ፡አስር፡ጊዜ፡ትዞራለች፡ማለት፡ነው። በተቻለህ፡መጠን፡
በ 0 ወይም፡ኒውትራል፡ባትነዳ፡ይመረጣል።

2ኛ፡አውቶማቲክ፡ነው።ህፃን፡ልጅ፡ይነዳዋል፡ብዙም፡ጣጣ፡የለበትም።2 የግር፡መርገጫ፡ብቻ፡ነው፡ያለው።
ይሄ፡ጽሁፍ፡እንደረዳህ፡ተስፋ፡አለኝ።

Posted on 10-01-16, 03:41 am


Karma: 90
Posts: 127/879
Since: 02-29-16

Last post: 6 days
Last view: 6 days
በጣም አመሰግናለሁ 12yeempfasillg! እድገነዘብ ረድቶኛል
Posted on 10-01-16, 10:20 am


Karma: 100
Posts: 64/610
Since: 08-27-16

Last post: 21 days
Last view: 9 days
የአራዳ፡ልጅ፡
አብሮ፡ይስጠን።
Pages: 1