ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Cooking & Recipes . | 2 guests
Pages: 1
Posted on 09-11-16, 02:28 pm (rev. 2 by  ማማዬ on 08-26-18, 05:27 pm)


Karma: 100
Posts: 24/94
Since: 08-19-16

Last post: 240 days
Last view: 47 days
ባህላዊ የቅቤ አነጣጥ ዘዴ በኢትዮጵያ
--------------------------------
- ቅቤውን ከወተቱ ወይም ከእርጎው የምንለይበት እንቅስቃሴ ቅቤ መናጥ ይባላል

የሚያስፈልጉ ነገሮች
----------------
ሀ. ወተት
ለ. አነስ ያለ እንስራ
ሐ. ለእንስራው ክዳን ድፍን ቅል
መ. ከእንስራው አንገት ትንሽ ወረድ ብሎ የተበሳ ቀዳዳ
ሠ. ለተበሳው ቀዳዳ ክዳን ወይም መወተፊያ
ረ. ቀጥና የተቀደደች ንፁህ ጨርቅ
ሰ. ወይራ
ሸ. ረጅም ቀጭን እንጨት

አሰራሩ
-----
- እንስራውን መግዛትና በእሳት እየተቃጠለ ዙሪያውን ይለበለባል ሲበቃው እጥብ አድርጎ በወይራ በደንብ እስከሚያልበው ይታጠናል ከዛም ከአንገቱ በታች በወስፌ ይበሳል በውሃ አንድ ጊዜ ይለቀለቅና ይደፋል
- በመቀጠል እንስራው እንዳያፈስ ጥልቅ ብሎ በደንብ የሚከድን ድፍን ቅል ተለክቶ መዘጋጀት አለበት ምናልባት እንደዛም ተከድኖ እንዳያፈስ የተዘጋጀውን ቀጭን ጨርቅ በእንስራው አፍና በቅሉ መሀከል ያለውን ቦታ ጥቅጥቅ ይደረጋል
- ከዚህ በኋላ ወተቱ በየቀኑ እየታለበ ይጠራቀማል በቆይታ ከ፪ ቀን ጀምሮ እየረጋ ይመጣል እርጎው ከእንስራው ግማሽ ትንሽ ከፍ ሲል በእንስራው ቀዳዳም እርጎው በዛ እንዳይፈስ መወተፊያ ይሰራለታል

ከዚህ በኋላ
----------
- እንስራው በቅሉና በጨርቁ ይከደናል
- ቀዳዳው ይወተፋል
- የሚንጠው ሰው በሚመች ዱካ ወይም ምደብ ላይ ይቀመጣል
- እንስራው ለስላሳ ማቶት ላይ ይቀመጣል ከዛ የሚንጠው ሰው እንስራውን ማቶቱ ላይ በማስቀመጥ የእንስራውን አንገት ወይም ማንገቻውን በመያዝ ቅቤው እስከሚወጣ ድረስ ወደታች ወደላይ እየተደረገ ይናጣል
- ቅቤው ሊወጣ ሲደርስ ድምፁ ቀጠን ይላል በዛን ጊዜ የተደፈነችውን ቀዳዳ በመክፈት በረጅም ቀጭን እንጨት ወደ ውስጥ በማስገባት ቅቤ ለማግኘት መሞከር ከደረሰ ቅቤው አብሮ ይወጣል ካልደረሰ አይወጣም ስለዚህ ቅቤው ጥቅልል ብሎ እስከሚወጣ ድረስ መናጥ አለበት
- ከዛ ሲበቃው ቅቤው አንድ ቦታ ተሰብስቦ ይገኛል እንስራውን ከፍቶ ማውጣትና በንፁህ ውሃ እጥብ አድርጎ መጠቀም ነው
- የቀረው አጓት ለአይብ ይሆናል እንደ እርጎም ሊጠጣ ይችላል
- በዚህ መልኩ እኛ ከአንድ ሊትር እርጎ ጀምሮ በማያፈስ ዕቃ በመጠቀም በእጃችን ንጠን ቅቤ ማግኘት እንችላለን
- በጁስ መፍጫ ማሽንም ውሃ ጣል አድርገን በመፍጨት ቅቤ እናገኛለን- ውድ ተከታዮቻችን ማሻሸያ፣ማስተካከያ፣እንዲሁም ሀሳብና የምትጠይቁት ጥያቄ ካለ ከስር መጻፍ ትችላላችሁ

Posted on 11-01-17, 08:31 am


Karma: 100
Posts: 5/5
Since: 12-15-16

Last post: 538 days
Last view: 537 days
አነጣጥና አነጣጠር ይለያል
Posted on 11-04-17, 10:09 pm


Karma: 100
Posts: 91/94
Since: 08-19-16

Last post: 240 days
Last view: 47 days
እሺ አስተካክዬዋለሁ
Pages: 1