ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Cooking & Recipes . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-25-16, 06:52 pm (rev. 3 by  ማማዬ on 06-14-17, 05:50 pm)


Karma: 100
Posts: 13/94
Since: 08-19-16

Last post: 240 days
Last view: 47 days
መከለሻ ቅመም ማለት ምን ማለት ነው?
- መከለሻ ማለት ቅመም ነው ቀይ ወጥ ሲሰራ ሊወጣ ሲል የሚጨመር ቅመም ነው

መከለሻ ለማዘጋጀት የምንጠቀምባቸው ቅመሞች ስም ዝርዝር
--------------------------------------------------
1. የፈረንጅ ኮረሪማ (ገውዝ)
2. ጥምዝ
3. ቀረፋ
4. ቅርንፉድ
5. ቁንዶ በርበሬ
6. ከሙን ናቸው

አሰራሩ
------
- ከላይ ከ1 እድከ 6 የተገለጹትን ቅመሞች በመጀመሪያ ከቆሻሻ አፀዳድቶና አድርቆ ማዘጋጀት
- ደርቀውና ፀድተው የተቀመጡትን ቅመሞች በሙቀጫም ሆነ መፍጨት በሚችል ማሽን ድቅቅ አድርጎ ፈጭቶ ወይም ወቅጦ መጨረስ
- የደቀቀውን ቅመም በደረቅና በንጱህ እቃ ማስቀመጥ ሲፈለግ ቀይ ወጥ በስሎና በቅቶት ከእሳት ላይ ሊወጣ ሲል የሚበቃውን መከለሻ ጨምሮ ለትንሽ ጊዜ ተክተክ በማድረግ ወጡን ማውጣትና መጠቀም ይቻላል

- ውድ ተከታዮቻችን ማሻሸያ፣ማስተካከያ፣እንዲሁም ሀሳብና የምትጠይቁት ጥያቄ ካለ ከስር መጻፍ ትችላላችሁ

ከላይ ከ1 እድከ 6 የተገለጹትን ቅመሞች
Posted on 08-30-16, 07:26 pm


Karma: 100
Posts: 5/610
Since: 08-27-16

Last post: 52 days
Last view: 1 day
ሠላም፡አዳነ፡ለጥያቄዬ፡በቶሎ፡መልስ፡ስለሰጠኸኝ፡እግዚአብሔር፡ይስጥልኝ። አትፍረድብኝና፡ከውድ፡ሃገሬ፡ከወጣሁኝ፡ብዙ፡ብዙ፡ዘመናትን፡አሳልፌአለሁ። ድሮ፡በልጅነቴ፡ወንድ፡ልጅ፡ከወጥ፡ቤት፡አይገባም፡በል፡ውጣ፡እየሉ፡ያባርሩኝ፡ነበር።
በሰጠኸኝ፡ዝርዝር፡ለመስራት፡እሞክራለሁ። የጥምዝ፡ቅመም፡ምንድን፡ነው?
Posted on 08-30-16, 08:16 pm


Karma: 100
Posts: 18/94
Since: 08-19-16

Last post: 240 days
Last view: 47 days
ይሄ ነው
Posted on 02-28-17, 01:47 pm


Karma: 100
Posts: 2/5
Since: 12-15-16

Last post: 538 days
Last view: 537 days
የስልጆ አሰራር እንዴት ነው
Posted on 03-05-17, 09:28 pm


Karma: 100
Posts: 63/94
Since: 08-19-16

Last post: 240 days
Last view: 47 days
Terefwa ስልጆ Youtube ላይ ተሰርቱዋል ግን በጽሁፍ ከፈለግሽው በቅርብ ጊዜ ይፃፋል
Posted on 05-09-17, 12:23 pm


Karma: 100
Posts: 1/1
Since: 05-09-17

Last post: 714 days
Last view: 714 days
ጤና ይስጥልኝ ማሚ ጥብስ ስሰራ በጣም ይደርቅብኛል ወይም ይከነችርብኛል በዛ ምክንያት ጥብስ ከሰራሁ በጣም ቆየሁ ምክንያቱ ምን ይሆን ማሚ ተባበሪኝ አመሰግናለሁ ደግሞ በጣም ነው ምወድሽ።
Posted on 05-15-17, 04:17 am


Karma: 100
Posts: 79/94
Since: 08-19-16

Last post: 240 days
Last view: 47 days
የኢትዮጵያ ስጋ ከሆነ ስጋውን ከጠበሽ በኋላ ውሃ ጠብ አርገሽ አላሊው ወይም በሌላ መንገድ መጨረሻ ላይ ቲማቲምና ሽንኩርት ጨምረሽ ሳይበስሉ አውጪያቸው ይሄ ሁሉ የሚሆነው ስጋው ውሀውን አስኪመጥ ከጠበሽ በኋላ ነው የአሜሪካ ከሆነ ስጋው ውሃ ሲወልድ ውሃውን አጠንፍፈሽ ስጋውን ብቻ ጥበሺው ከዛ መልሰሽ ያጠነፈፍሺውን መረቅ ጨምረሽ አላሊው
Pages: 1