ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣ ኑ እና የምትሉትን በሉ!
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
0 users browsing Cooking & Recipes . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-21-16, 12:35 am (rev. 9 by  ማማዬ on 08-28-16, 04:42 pm)


Karma: 100
Posts: 3/94
Since: 08-19-16

Last post: 149 days
Last view: 39 days
የእንጀራ አና የዳቦ እርሾ አሰራር
------------------------

1. እርሾ መለት ምን ማለት ነው
- እርሾ መለት መነሻ መጀመሪያ ማለት ነው
2. እርሾ የምናገኝበት መንገድ ፪ ነው
እነርሱም:- ሀ. በፋብሪካ
ለ. በቤት ውስጥ የሚሰሩ ናቸው
3. በፋብሪካ የሚሰሩ እርሾዎች
ሀ. ለተለያዩ ዳቦዎች
ለ. ለኬኮች
ሐ. ለፓስቲዎች ወዘተ እንገለገልባቸዋለን

- በቤት ውስጥ የሚሰሩ እርሾዎችን ግን ለሁሉም መጠቀም እንችላለን ሆኖም ግን የጤፍ እንጀራችንን ለመጋገር ጣዕሙ የጤፍ እርሾ ስለሚመቸን ካላጣን በስተቀር ምንም ጊዜ በጤፍ እርሾ ማቡካትን እንመርጣለን

- ዳቦም ስንጋግር በጣም ጥቂት የዳቦ እርሾና የጤፍ እርሾ ጥላይ ጨምረን ነው የምንጋግረው ይህ በዚህ እንዳለ አሰራሩን እናያለን

አሰራሩ
-----
- ለዳቦና ለእንጀራ የምንጠቀምበትን ዱቄት ሁሉ በተናጠል በመጠቀም እርሾ መፍጠር እንችላለን
ለምሳሌ:- 1/4 ኪሎ የጤፍ ዱቄት በጣም ለሰስ ባለ ውሃ ላላ አድርጎ ማቡካት ክ3 ቀን ጀምሮ ኩፍታውን በመጠበቅ ኩፍ ሲል እንደ እርሾ መጠቀም ትችላላችሁ::

- በተሰጠው ምሳሌ መሰረት ከማንኛውም የዱቄት አይነት እርሾ መስራት ትችላላችሁ

ማሳሰቢያ:- ሀ. ሁሉም ዱቄቶች በእኩል ቀን ኩፍ ሊሉ አይችሉም
ለ. የእርሾ ጣዕም አመራረጥ እንደተመጋቢው ነው

- ውድ ተከታዮቻችን ማሻሸያ፣ማስተካከያ፣እንዲሁም ሀሳብና የምትጠይቁት ጥያቄ ካለ ከስር መጻፍ ትችላላችሁየጤፍ እርሾ

የጤፍ እርሾ

.
.
.
.
Posted on 10-23-16, 09:50 pm


Karma: 100
Posts: 1/1
Since: 10-23-16

Last post: 821 days
Last view: 821 days
ማሚ እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥልን ማሚ የ5 ቀን ጥቅል አቡክቼ መጀመሪያ ቆንጆ ሆኖልኝ ደስ ብሎኝ በሚቀጥለው ግዜ እንቢ አላኝ አብሲት ሲበዛብኝ ወይም ቢቀጥንብኝ ምን ባደርግ ጥሩ ነው ሌላ እንቢ ሲላችሁ ፍሩጅ እስገቡትና ጋግሩ ብለውን ነበር ለስንት ደቂቃ እመሰግናለሁ
Posted on 10-24-16, 02:33 am


Karma: 100
Posts: 41/94
Since: 08-19-16

Last post: 149 days
Last view: 39 days
አመሰግናለሁ ለምርቃቱ, አብሲት ሲበዛ የጤፍ ብቻ እንጀራ ከሆነ በአንድ የእጅ እፍኝ ጤፍ ዱቄት ማጎብጎብ የጤፍና ገብስ እንጀራ ከሆነ በአንድ የእጅ እፍኝ ገብስ ዱቄት ማጎብጎብ ከቀጠነ አስቀምጪውና ሲያጠል አጥሊይው ፍሪጅ ውስጥ ከአንድ እስከ ሁለት ሰዓት በቂው ነው እንደተጨማሪ ማሳሰቢያ ቡኮውን ስታቦኪው ቀዝቃዛ ቦታ አስቀምጪው
Posted on 08-02-17, 09:47 am


Karma: 100
Posts: 1/1
Since: 08-02-17

Last post: 538 days
Last view: 538 days
Emamaye, Egziabher ystilin sile timirtwo. Enjera eyaschegeregn tiyake alegn. Absit ketechemere behuala ( ye tef bicha Amsit ken buko erswo bastemarun meseret) be magistu litu wuha yakeral enji erswo gar endemitayew kurifrif bilo aybokam. Sigager ayin yelelew sintiktik yale yihonal. yihew lit baking powder tal sidereg aynu egig yamare yihonal. Enjerwa gin dirik yale yihonal. Min yimekrugnal?

Esgziabher Yisilin.
Posted on 08-04-17, 12:01 am (rev. 1 by  ማማዬ on 08-04-17, 12:05 am)


Karma: 100
Posts: 87/94
Since: 08-19-16

Last post: 149 days
Last view: 39 days
ስለ ምስጋናሽ አመሰግናለሁ በንጋታው ውሃ የሚያቀርብሽ ሊጡ እራሱ በደንብ ስላልቦካ ነው ቪደዮ ላይ እንዳየሽው ከ 4-6 ቀን እንዳየሩ ሙቀት ሊጡ መቡካት አለበት እንዲሁም እርሾ በርከት አርገሽ ጨምረሽ አብኪው ከዛ ነው አብሲት የምትጨምሪው, ቤኪንግ ፓውደር ባትጠቀሚ ይመከራል እሱ ነው ሚያደርቀው
Posted on 09-27-17, 03:20 am


Karma: 100
Posts: 1/1
Since: 09-27-17

Last post: 482 days
Last view: 482 days
እማማዬ በጣም በጣም ውድድድድድ ነው የማረግሽ የስደት የሙያ እናቴ ያንቺን ቪዲዮ ማየት ከጀመርኩባት ጊዜ ኣንስቶ የማልችለው ሙያ የለም እልሻለሁ እድሜና ጤና ይስጥልኝ ኣዳነ ላንተም እግዚአብሔር ይስጥልኝ መልክቴን ኣድርስልኝ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ ኣደረሳችሁ
Posted on 09-28-17, 05:53 am


Karma: 100
Posts: 89/94
Since: 08-19-16

Last post: 149 days
Last view: 39 days
እንኳን አብሮ አደረሰን Abby እኔም አመሰግናለሁ ስለ ጥሩ አስተያየትሽ
Posted on 02-12-18, 02:39 am


Karma: 100
Posts: 2/2
Since: 02-12-18

Last post: 344 days
Last view: 344 days
Posted by ማማዬ
የእንጀራ አና የዳቦ እርሾ አሰራር
------------------------

1. እርሾ መለት ምን ማለት ነው
- እርሾ መለት መነሻ መጀመሪያ ማለት ነው
2. እርሾ የምናገኝበት መንገድ ፪ ነው
እነርሱም:- ሀ. በፋብሪካ
ለ. በቤት ውስጥ የሚሰሩ ናቸው
3. በፋብሪካ የሚሰሩ እርሾዎች
ሀ. ለተለያዩ ዳቦዎች
ለ. ለኬኮች
ሐ. ለፓስቲዎች ወዘተ እንገለገልባቸዋለን

- በቤት ውስጥ የሚሰሩ እርሾዎችን ግን ለሁሉም መጠቀም እንችላለን ሆኖም ግን የጤፍ እንጀራችንን ለመጋገር ጣዕሙ የጤፍ እርሾ ስለሚመቸን ካላጣን በስተቀር ምንም ጊዜ በጤፍ እርሾ ማቡካትን እንመርጣለን

- ዳቦም ስንጋግር በጣም ጥቂት የዳቦ እርሾና የጤፍ እርሾ ጥላይ ጨምረን ነው የምንጋግረው ይህ በዚህ እንዳለ አሰራሩን እናያለን

አሰራሩ
-----
- ለዳቦና ለእንጀራ የምንጠቀምበትን ዱቄት ሁሉ በተናጠል በመጠቀም እርሾ መፍጠር እንችላለን
ለምሳሌ:- 1/4 ኪሎ የጤፍ ዱቄት በጣም ለሰስ ባለ ውሃ ላላ አድርጎ ማቡካት ክ3 ቀን ጀምሮ ኩፍታውን በመጠበቅ ኩፍ ሲል እንደ እርሾ መጠቀም ትችላላችሁ::

- በተሰጠው ምሳሌ መሰረት ከማንኛውም የዱቄት አይነት እርሾ መስራት ትችላላችሁ

ማሳሰቢያ:- ሀ. ሁሉም ዱቄቶች በእኩል ቀን ኩፍ ሊሉ አይችሉም
ለ. የእርሾ ጣዕም አመራረጥ እንደተመጋቢው ነው

- ውድ ተከታዮቻችን ማሻሸያ፣ማስተካከያ፣እንዲሁም ሀሳብና የምትጠይቁት ጥያቄ ካለ ከስር መጻፍ ትችላላችሁየጤፍ እርሾ

የጤፍ እርሾ

.
.
.
.
Pages: 1