ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Olympics. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 08-15-16, 03:01 pm


Karma: 100
Posts: 117/426
Since: 07-12-15

Last post: 262 days
Last view: 262 days
አልማዝ አያናና የሪዮ ኦሊምፒክ አዳዲስ ታሪኮች

አልማዝ አያና በሪዮ ኦሊምፒክ የ10 ሺህ ሜትርን ክብረ ወሰንን በ29:17.45 በሆነ ሰዓት በአስደናቂ ሁኔታ ከሰበረች በኋላ የማይታመኑ ታሪኮች እንዲከሰቱ አድርጋለች

የሪዮ ኦሊምፒክ የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር በታሪክ በኦሊምፒክ ከተካሄዱ ውድድሮች እጅግ ፈጣኑ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በዚህም ምክንያት የተለያዩ ከስተቶች ተፈጠረዋል

1. አልማዝ አያና የ10 ሺህ ሜትርን ሁለተኛ አጋማሽን ያጠናቀቀችው 14፡30፡64 በሆነ ሰዓት ነው፡፡ ይህም ሰዓት በ5 ሺህ ሜትር ውድድር የኦሊምፒክ ሪከርድ ሆኖ ከተመዘገበው ሰዓት በ 10 ሰኮንድ የፈጠነ ነወ፡፡

በአሁኑ ሰዓት የኦሊምፒክ 5 ሺህ ሜትር ርቀት ሪከርድ ተመዝግቦ የሚገኘው በሮማኒያዊቷ ገብሬላ አዛቦ ሲሆን ሰዓቱም 14፡40፡79 በሲዲኒ ኦሊምፒክ ነበር፡፡

2. ከዚህ ውድድር በፊት ርቀቱን ከ30 ደቂቃ በታች ሮጠው ያጠናቀቁትአትሌቶች ብዛት 5 ብቻ ነበሩ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አራቱ በርቀቱ ከ1ኛ እስከ 4ኛ የወጡት አትሌቶች ይገኙበታል፡፡

3. አልማዝ አያና በ10 ሺህ ሜትር ውድድር ላይ ስትሳተፍ ይህ ሁለተኛ ጊዜዋ ነው፡ ገባችበት ሰዓትም 30፡07፡00 ነበር፡፡

4. አልማዝ አያና ይህንን ውድድር ማሸነፏን ተከትሎ 8 አትሌቶችን ካቅማቸው በላይ በማስሮጥ የሀገራቸውን ብሄራዊ ክብረ ወሰን ሰብረዋል እነሱም ኢትዮጵያ፡ኬንያ፡ አሜሪካ፡ ቡሩንዲ፤ ግሪክ፤ ኪርግስታንና ኡዝቤኪስታን አትሌቶች ይገኙበታል፡፡

5. 18 ሴት አትሌቶች ደግሞ የራሳቸውን ፈጣን ሰዓት አስመዝግበዋል፡፡

6. በአልማዝ አያናና የመጨረሻ ደረጃን ይዛ ባጠናቀቀችው ሜክሲካዊቷ ሯጭ ማሪሶል ሮሜሮ መካከል ያለው የሰዓት ልዩነት ከ6 ደቂቃ በላይ ሲሆን በአልማዝ አያና ፍጥነት ሲገመት ከአምስት ዙር በላይ ነው፡፡

ምንጭ፡- ራነርስ ዎርልድ
Posted on 08-17-16, 01:21 pm


Karma: 100
Posts: 1/1
Since: 08-17-16

Last post: 1205 days
Last view: 1205 days
she registerd ambitious record
Posted on 08-18-16, 12:55 am


Karma: 90
Posts: 99/887
Since: 02-29-16

Last post: 129 days
Last view: 129 days
She is an amazing athlete never seen before
Posted on 08-18-16, 08:52 am


Karma: 100
Posts: 1/1
Since: 08-18-16

Last post: 1204 days
Last view: 1204 days
we are one
we are proud
Pages: 1