ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Government. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-29-16, 01:58 pm (rev. 1 by Ye Arada Lij on 07-31-16, 10:16 pm)


Karma: 90
Posts: 79/879
Since: 02-29-16

Last post: 34 days
Last view: 34 days
‘‘የኢትዮጵያ ነገሥታት ቁጥር…ከዘመነ አጼ ዘርዐ ያዕቆብ ጀምሮ ሲዘረዘር’’

………………………………………
ሐገራችን ኢትዮጵያ ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ ጠላትን የሚያንቀጠቅጡ አራስ ነብር የሆኑ ነገሥታቶች እንደነበሯት የሚታወቅ ነው። ይሁንና ቅድመ ክርስቶስ ልደትም ይሁን እስከ አጼ ዘርዐ ያዕቆብ ድረስ፥ የነበሩትን ገዥዎች ስማቸውንና ቁጥራቸውን ለማወቅ ብንፈልግ፥ ጥንታዊ መዛግብቶቻችንን ማገላበጥ ግድ ይለናል።
በዚህም ረገድ፥ ዘመን ጠገብ ማስረጃዎች ያሉን ሕዝቦች ስንሆን ፥ከነዚህም ውስጥ ልንጠቅስ ብንሞክር …በአለቃ ታዬ የተጻፈው፥ ክብረ ነገስትና ሌሎች የታሪክ መጽሐፍት የተጻፉትን መመልከት በይበልጥ ሁሉን ግልጽ ያደርግልናል።
እኔ ግን አሁን የምዘረዝርላችሁ የኢትዮጵያ ነገሥታት…ከ1426 ዓ.ም ጀምሮ ከነገሱት ከአጼ ዘርዐ ያዕቆብ ወዲህ ያሉትን ሲሆን መነሻዬም ቆየት ብለው ከተጻፉት መጽሐፍት አንዱ ከሆነውና በጥራዙ ደጎስ ካለው ከዓለም ታሪክ መጽሐፍ ይሆናል።
የነገሥታቱ ስመ መንግስት ወይም የስራ ስም በቅንፍ የተቀመጠ ሲሆን ዝርዝራቸውን እንዲህ አስቀምጨዋለሁ።
አጼ ዘርዐ ያዕቆብ (ቆስጠንጢኖስ).........ከ1426 ¬- 1460
አጼ በእደ ማርያም .......................... ከ1460- 1470
አጼ እስክንድር .............................. ከ1470 -1486
አጼ ዐምደ ጽዮን ............................ ከ1486- 1487
አጼ ናዖድ(አንበሳ ዘጸር) ................... ከ1487- 1500
አጼ ልብነ ድንግል (ወናግ ሰገድ) ........ ከ1500- 1533
አጼ ገላውዴዎስ (አጽናፍ ሰገድ) …..... ከ1533- 1551
አጼ ሚናስ (አድማስ ሰገድ) ................ከ1551- 1555
አጼ ሰርጸ ድንግል (መለክ ሰገድ) ........ ከ1555- 1588
አጼ ያዕቆብ .................................. ከ1588 -1595
አጼ ዘድንግል አቤቶ ልሳነ ክርስቶስ……...ከ1595- 1597
አጼ ሱስንዮስ (ስልጣን ሰገድ) ............ ከ1597 -1624
አጼ ፋሲል ዓለም ሰገድ .................... ከ1624- 1660
አጼ ዮሐንስ 1ኛ( አእላፍ ሰገድ) …...... ከ1660- 1674
አጼ ኢያሱ 1ኛ (አድያም ሰገድ) .......... ከ1674 -1690
አጼ ተክለ ሃይማኖት (ሉል ሰገድ)........ ከ1698 -1700
አጼ ቴዎፍሎስ (አጽራር ሰገድ) ........... ከ1700- 1703
አጼ ዮስጦስ .................................. ከ1703- 1708
አጼ ዳዊት 2ኛ (አደባር ሰገድ) ............ ከ1708- 1713
አጼ በከፋ (መሲሕ ሰገድ) ................. ከ1713 -1723
አጼ ኢያሱ 2ኛ (ብርሃን ሰገድ) ........... ከ1723- 1747
አጼ ኢዮአስ .................................. ከ1747- 1763
አጼ ዮሐንስ 2ኛ (ዘዋሕድ እዴሁ) ....... ከ1763
አጼ ተክለ (ሃይማኖት አድማስ ሰገድ)… ከ1763- 1770
ሰሎሞን ....................................... ከ1770- 1772
ተክለ ጊዮርጊስ 1ኛ (ፍጻሜ መንግስት).. ከ1772- 1777
ራስ ዓሊ( ትልቁ) ........................... ከ1777- 1781
ራስ ዓሊጋዝ ................................. ከ1781- 1786
ራስ ዐስራትና ራስ ወልደ ገብርኤል……... ከ1786- 1792
ራስ ጉግሳ .................................... ከ1792- 1818
ራስ ይማም ...................................ከ1818 -1820
ራስ ማርዬ ................................... ከ1820- 1823
ራስ ዶሪ ...................................... ከ1823
ራስ ዐሊ (ትንሹ)……………........ ከ1823- 1845
አጼ ቴዎድሮስ 2ኛ( አባ ታጠቅ) ........ ከ1845- 1860
አጼ ተክለ ጊዮርጊስ 2ኛ ................... ከ1860- 1863
አጼ ዮሐንስ 3ኛ( አባ በዝብዝ) .......... ከ1864- 1881
አጼ ምኒልክ 2ኛ (አባ ዳኘው)............ ከ1881- 1906
ልጅ ኢያሱ 3ኛ ............................. ከ1906- 1909
ንግስት ዘውዲቱ ............................ ከ1909- 1922
አጼ ኃይለ ስላሴ ቀዳማዊ ................. ከ1922- 1967
ፕሬዚዳንት መንግሰቱ ኃይለ ማርያም.... ከ1967- 1983
ፕሬዝዳንት መለስ ዜናዊ ………….. ከ1983¬- 2004 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ...ከ2004 ዓ.ም...
እነዚህ ዋና ዋናዎቹ ነገሥታት ወይንም አገሪቷን ያስተዳደሩ መሪዎች ሲሆኑ፤ እነዚህ እያሉ በአንዳንድ ወቅት የሸዋ መሳፍንትና ንጉሶች እንደነበሩ ይታወቃል።
Posted on 09-27-16, 02:41 pm


Karma: 100
Posts: 58/610
Since: 08-27-16

Last post: 49 days
Last view: 7 days
አባቶቻችን፡እና፡እኔም፡በመመስከር፡የተደረገ።

በቴዎድሮስ፡
ቀረ፡በየቦታው፡መንገስ።
በዮሐንስ፡
ጠነከረ፡ኦርቶዶክስ
በምኒልክ፡
ኢትዮጵያን፡አስከበርክ።
በኢያሱ፡
ዳቦ፡ነው፡ትራሱ።
በዘውዲቱ፡
ተደፋ፡ሌማቱ።
በተፈሪ፡
ጠፋ፡ፍርፋሪ።
በመንግስቱ፡
ታጨደ፡ወጣቱ።
በመለሰ፡
ዲያቢሎስ፡ነገሰ።
በሃይለማሪያም፡
ተከዳች፡እመቤታችን፡ማርያም።
Pages: 1