ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Politics - ፖለቲካ. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-25-16, 08:48 pm (rev. 1 by Tg on 07-25-16, 08:48 pm)


Karma: 100
Posts: 138/444
Since: 07-20-15

Last post: 38 days
Last view: 38 days
ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማሪያም የጎዳና ተዳዳሪዎችን ጎብኝተው ነበር ፤ በሞስኮ በኩል የኩባን የጦር አማካሪዎች በማግኘታቸው የወራሪውን የሶማሊያን ኃይል መመከት ችለዋል።
ከስሜነህ ጌታነህ@DireTube
-----------
አንድ ምስል ከእጄ ገባ ፤፤ ይህም ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማሪያም በ1970ዎቹ ግድም የጎዳና ተዳዳሪዎችን ሲጎበኙ፤፤
በአዲስ አበባ በአንዱ ስፍራ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ሄደው ጎብኝተዋል። ኮሎኔል መንግስቱ በ አውሮፓ አቆጣጠር 27 በግንቦት ወር በ 1941 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተወለዱ። አባታቸው ሃምሳ ዓለቃ ሃይለማሪአም ወልዴ እናታቸው ብዙነሽ ተሰማ ነበሩ።
ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለ ማርያም ከ1966 እስከ 1983 ዓ.ም. (1974 እስከ 1991 እ.ኤ.አ.) ለ17 ዓመታት የኢትዮጵያ መሪ ነበሩ። ወደ ስልጣን የወጡት በደርግ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን በመገልበጥ ሲሆን ተቃናቃሾኞቻቸው የነበሩትን የቅርብ ጓደኞቻቸውንና የደርጉን መሥራቾች በማስወገድ ብቸኛ የአብዮቱ መሪ ሆነው ከቆዩ በኋላ 1983 ከስልጣን ተወገዱ። በአሜሪካ ሲ አይ ኤ እርዳታ አገር ጥለው በመኮብለል ዚምባብዌ ሀራሬ ተሸሽገው ይኖራሉ።
ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም ወደ ርዕሰ ብሄርነት ሥልጣን ብቅ ሲሉ ገና የ37 ዓመት ወጣት የነበሩ ሲሆኑ በዘመቻ ቀይ ሽብር የብዙ ሺህ ወጣቶችን መጨፍጭፍ ከመጀመራቸው በፊት በሀረር የ3ኛ ክፍለ ጦር የመሳሪያ ግምጃ ቤት ውስጥ ይሰሩ ነበር።
በወቅቱ በክፍለ ጦሩ አዛዥ የነበሩት ጀነራል ሓይሌ ባይከዳኝ የሚባሉ ኮ/ መንግስቱን በባህሪያቸው በመጠርጠራቸው ከአጠገባቸው ዞር ለማድረግ ወደ ኦጋዲን አዛውረዋቸው እንደ ነበር ይነገራል። በእዚያም ጥቂት ጊዜ በኋላ ለትምህርት ወደ አሜሪካ ሜሪላንድ ለወታደራዊ ሳይንስ ትምህርት ተላኩ። ከትምህርት ሲመለሱም በ3ኛ ክፍለ ጦር የመሳሪያ ግምጃ ቤት ሃላፊ ሆነው ተሾሙ።
ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ሶማሊያ በሶቭየቶች ተደግፋ ሀገራችንን ድንገት ወረረች። በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩትን ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተርን ፈጣን ወታደራዊ እርዳታ ጠይቀው እርሳቸውም ደርግ ከራሺያ ጋር በጀመረው ወዳጅነት በመጠራጠራቸው የመግሥቱን ጥያቄ ሳይቀበሉ ቀሩ።
በእዚህም ምክንያት አማራጭ ያጣው ደርግና ኮሎኔል መንግሥቱ ሀገሪቱ በከፍተኛ ስጋት ላይ በመውደቋ የግድ ወደ ሞስኮ መሳሪያ ልመና ልኡካን ላኩ። በሌላ በኩል ሞስኮ ከሶማሊያ ጋር ጥቅምዋን በማወዳደር ለመንግስቱ መሳሪያ መስጠት ካስፈለገ በፊርማ ሶሻሊስት ካምፕ መግባቱን እንዲያረጋግጡ ስለ ጠየቀች ኮ/መንግሥቱ ይህን በማድረጋቸው በይፋ የሚመሩት አብዩት የሌኒኒስት ማርክሲስት መሆኑን በአዋጅ አሳወቁ።
ኮ/መንግሥቱ የቼ ጉቬራና የማኦ ሴቱንግ ሕይወት ታሪክ መጻህፍቶች ከማንበብ በስተቀር ስለ ሶሻሊዝም ከወሬ ባለፈ የሚያውቁት ጥልቅ እውቀት አልነበረም። ከስምምነቱም በሁዋላ በ2 ወር ጊዜ ውስጥ የብዙ ሚሊዮን ዶላር ታንክና የጦር መሣሪያ እርዳታ ማግኘት ብቻ ሳይሆን በሞስኮ በኩል የኩባን የጦር አማካሪዎች በማግኘታቸው የወራሪውን የሶማሊያን ኃይል መመከት ችለዋል።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አሜሪካ የጭንቅ ጊዜ ጥያቄ መላሽ ሆና ባለመገኘትዋ መንግስቱ በስልጣን እስከቆዩበት ዘመን ሁሉ በዋና ጠላትነት ፈረጁ። አንዳንድ ሚሲዮናዊያንንም ከአገር አባረሩ።


Pages: 1