ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Doctor's Help. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-16-16, 06:37 pm


Karma: 90
Posts: 67/887
Since: 02-29-16

Last post: 206 days
Last view: 206 days
"ከአንበሳና-ከዝሆን-ማን-ያሸንፋል?”-ቢለው፤-“ከሁሉም-አሳ-ሙልጭልጭ-ነው”-አለው
ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ሰው በጠና ታመመና አልጋ ላይ ዋለ፡፡ በየጊዜው እየሄደ ዶክተሮች ያነጋግራል፡፡
1ኛው ሐኪም - “አይዞህ ቀላል ነው፡፡ ለክፉ አይሰጥህም” አለው፡፡
ህመምተኛው - “ዕውን ሐኪም በዚህ ተፅናንቼ ልቀመጥ?”
1ኛው ሐኪም - “እርግጡን ነው የነገርኩህ”
ህመምተኛው - “እንዳፍዎ ያድርግልኝ!”
ግን አያርፍም ህመምተኛው - ወደ ሁለተኛው ዶክተር ይሄዳል፡፡
ሁለተኛው ሐኪም - “ምንም ችግር የለብህም፤ አሁን የያዘህ በሽታ በረዥም ጊዜ የሚድን ስለሆነ ብቻ ነው አልጋ መያዝ ያስፈለገህ”
ህመምተኛው - “ቃልዎትን አምኜ ዝም ብዬ ልተኛ ሐኪም?”
ሁለተኛው ሀኪም - “እቺን ታክል አትጠራጠር!”
ህመምተኛው - “እንዳፍዎ ያድርግልኝ!”
ወደ ሶስተኛው ሀኪም በሚቀጥለው ቀን ይሄዳል፡፡
ሶስተኛው ሐኪም - ከሁሉም የተለየ ነገር ነው የነገረው፡፡
“ወዳጄ የያዘህ በሽታ ፈፅሞ ጊዜ የሚሰጥ አይደለም፡፡ እንዲያውም ሀያ አራት ሰዓት ለመቆየት መቻልህን እጠራጠራለሁ፡፡ ስለዚህ ምንም አላደርግልህም”
ህመምተኛው አመስግኖ ሄደ፡፡
ሁኔታው ሶስተኛው ሐኪም እንዳለው ሳይሆን ቀረ፡፡ ሰውየው ከቀን ቀን እየተሻለው መጣና በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ካልጋው ተላቆ ቆሞ መሄድ ቻለ፡፡ በእርግጥ ግን ህመሙ ብዙ ስጋውን ስለበላው በአፅሙ የሚሄድ ይመስላል፡፡
አንድ ቀን መንገድ ላይ ሶስተኛውን ሐኪም አገኘው፡፡ ሐኪሙ በጭራሽ ያየውን ማመን አልቻለምና፤
“የወዲያኛውን ዓለም አይተህ ተመልሰህ መጥተህ መሆን አለበት፡፡ ለዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ ከዚህ ቀደም ተለይተውን ወደ ሰማይ ቤት የሄዱት ወዳጆቻችን እንዴት ናቸው ባክህ?”
ህመምተኛውም - “እጅግ በጣም ተመችቷቸው፣ ደልቷቸው ነው የሚኖሩት፡፡ ዘለዓለማዊውን ውሃ ጠጥተውና የዓለም ችግር ሁሉ ረስተው፤ በጣም ተመችቷቸው ይኖራሉ፡፡ በነገራችን ላይ እኔ ከዛ ለቅቄ እየመጣሁ ሳለሁ ምድር ላይ ባሉ ዶክተሮች ላይ ፍርድ ለመስጠት እየተዘጋጁ ነበር፡፡ ያስቀመጡት ምክንያት ህመምተኛ ሰዎች በተፈጥሮአዊ መንገድ እንዳይሞቱ ጥበብ እየተጠቀሙ በህይወት እንዲቆዩ በማድረጋቸው ነው፡፡ አንተንም ከሌሎቹ ጋር እንደሚቀጡህ ሲያስቡ ነበር፡፡ እኔ ግን እሱን ተዉት፤ ምክንያቱም እሱ አባይ ጠንቋይ እንጂ ዶክተር አይደለም አልኳቸው!”
* * *
ውሸተኛ ዐባይ ጠንቋዮች እየበዙ፣ ዕውነተኛ ዶክተሮች እየሳሱ ከመጡ አገራችን አደጋ ላይ ናት! ዐባይ መምህራን እየበዙ ዕውነተኛ መምህራን ከተመናመኑ የትምህርት ነገር አዲዮስ! የሚባል ይሆናል! ዐባይ ጠበቆችና ዐባይ ዳኞች ከተበራከቱና ዕውነተኛ ዳኞችና ሀቀኛ ጠበቆች ከጠፉ “O! Justice thy has flown to beasts!!” (ፍትሕ ሆይ! ወደ አራዊት በረርሽን!) እንዳለው ሼክስፒር ይሆናል፡፡ ግልፅነትና ተጠያቂነት ለአፍ አመል ብቻ እየተስፋፉ በተግባር ግን ሁሉ ድብቅ፣ ሁሉ የአዋቂ አጥፊ እየሆነ የሚገኝ ከሆነ፤ የለበጣ ዲሞክራሲ እንጂ ሌላ የለም፤ ሃሳዊ መብት እንጂ ለዕድገት የቆመ ሀቀኛ ሥርዓት አይኖርም፡፡ የካብነው እየተናደ፣ አደግን ያልነው ቁልቁል እየሔደ፤ በየቀኑ በችግር ማጥ ውስጥ መላሸቃችን አሳዛኝ ነው! የግል ት/ቤቶች ዕውቅናና ፈቃድ አስቂኝ ደረጃ ላይ ደርሷል! የት/ቤቶች ተቋማት ዕድሳት ዘወትር በማስጠንቀቂያና በማስፈራሪያ የሚታለፍ የመስፈራሪቾ (Scare-crow) ሂደት ሆኗል፡፡
Pages: 1