ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Religion. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-07-16, 02:50 pm (rev. 2 by Ye Arada Lij on 07-07-16, 02:52 pm)


Karma: 90
Posts: 64/879
Since: 02-29-16

Last post: 69 days
Last view: 69 days
የፓስተሩንና የኦርቶዶክሱ ፍጥጫ ~

ፖስተር፦ሰላም ላንተ ይሁን ወንድሜ

ኦርቶዶክሱ፦አሜን ለሁላችንም ይሁን እንዴት ነህ ፓስተር ሰሞኑን ጠፍተሃል

ፓስተር፦ጠፋሁ አይደል አገልግሎት ላይ ስለነበርኩ እኮ ነው ክብር ለጌታ ይሁን ሀሌሉያ

ኦርቶዶክሱ፦አይ ፓስተር አገልግሎት ነው ያልከኝ?የሆነው ሆነና ወደ ዛሬው የመወያያ ርዕሳችን ብንገባ ምን ይመስልሃል

ፓስተር፦ደስ ይለኛል

ኦርቶዶክሱ፦ጥሩ ደስ ያለህን ሀሳብ ማንሳት ትችላለህ

ፓስተር፦ "እናንተ ኦርቶዶክሶች ግን ማርያም ማርያም
ማለትን ታበዛላችሁ ቆይ ግን "ምናችሁ ስለሆነች ነው እንዲህ የምታሞጋግሷት??"

ኦርቶዶክሱ፦ "እናታችን ስለሆነች።"ነዋ

ፓስተር፦ "ማነው እናታችሁ ያደረጋት?"

ኦርቶዶክሱ፦ "ልጇ ጌታችን መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነዋ።"

ፓስተር፦ "ደሞ መቼ?"

ኦርቶዶክሱ፦ "በእለተ አርብ በቀራንዮ መስቀል ላይ ሆኖ ።"

ፓስተር፦ "ደፋሮች ናችሁ!"

ኦርቶዶክሱ፦ "እንደት?"

ፓስተር፦ "ጌታ ለዮሐንስ እናትህ እችውት አለው እንጅ
መቼ ኦርቶዶክሶች እናታችሁ እችውት አላችሁ?"

ኦርቶዶክሱ፦"ዮሐንስ እናት አልነበረችውም እንዴ ? ለምን
እናትህ እችውት አለው?"

ፓስተር፦"በእርግጥ እናት አለው ግን እናቱንም እናቱ
እንድትሆንለት ለሱ ብቻ ሰጠው።"

ኦርቶዶክሱ፦"ታድያ ለምን "እናትህ" አለው ? በወላጅ
እናትህ ላይ እናቴንም ጨምረልሃለው ለምን አላለም?"

ፓስተር፦ "በዛን ሰኣት ወላጅ እናቱ አብራው
አልነበረችማ።"

ኦርቶዶክሱ፦ "አይ ፓስተር ታስቃለህ በጣም! ለመሆኑ 10ቱ
ትእዛዛት ለማን ተሰጡ??"

ፓስተር፦ "ለሙሴ ነዋ!"

ኦርቶዶክሶ፦ታድያ ለሙሴ ብቻ ከተሰጠ ለምን እኛም
ትእዛዛቱን እንድንጠብቃቸው ተደረገ??"

ፓስተር፦ "የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ስለሆኑ እኛም
እንጠብቃቸዋለን!"

ኦርቶዶክሱ፦ "መልካም ለሙሴ የተሰጡት 10ቱ ትእዛዛት
ለሙሴ ብቻ ተሰተው እንዳሉ እኛ ደሞ አይ የእግዚአብሔር
ትእዛዛት ናቸው ብለን ጠበቅናቸው፤ ለመሆኑ ኢየሱስ ክርስቶስ
እግዚአብሔር አይደለምን???"

ፓስተር፦ "እግዚአብሔርማ ነው ከፈለክ ጥቅስ ልስጥህ።"

ኦርቶዶክሱ፦ "አይ ጥቅሱን እንኳ ተወው እኔምኮ አምንበታለሁ! ያውም ሃያል አምላክ ነው!!"

ፓስተር፦ "እና?"

ኦርቶዶክሱ፦ "እናማ ለሙሴ 10ቱን ትእዛዛት የሰጠው
እግዚአብሔር ነው ብለን አምነን እኛም ትእዛዛቱን
ከተቀበልን ታድያ ድንግል ማርያምን ለዮሐንስ የሰጠው
ኢየሱስ ክርስቶስም እግዚአብሔር ነው ብለን ለምንድ ነው
ድንግል ማርያምን ለዮሐንስ ብቻ ተሰጠች የምንለው?"

ፓስተር፦ "የፈለከውን ጠይቀኝ እኔ ድንግል ማርያምን
ኢየሱስ ሰቶኛል ብዬ እናቴ አልላትም! "

ኦርቶዶክሱ፦ "መብትህ ነው እሽ የጌታዬ እናትስ
አትላትም??"

ፓስተር፦ "አልላትም"

ኦርቶዶክሱ፦ "ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስንም ጌታዬ
አትለውም ማለት ነዋ!"

ፓስተር ፦ "ለምንድ ነው ማልለው እሱማ ጌታዬ ነው"
አልክደውም "ኢየሱስ ጌታ ነው!"

ኦርቶዶክሱ፦"እሽ ከ10ቱ ትእዛዛት አንዱ እናትህንና
አባትህን አክብር የሚል ነው! ታድያ አንተ የራስህን እናት ሰው
ቢያከብርልህ እንደምትደሰት ሁሉ ጌታችንም እናቱን
ስታከብርለት እንደሚደሰትብህ አታውቅምን?"

ፓስተር፦ "ስለወለደችው አከብራታለሁ"

ኦርቶዶክሱ፦ "ምን ብለህ ታከብራታለህ?"

ፓስተር፦ ዝም

ኦርቶዶክሱ፦ "አንድ አባት ለልጁ የምጣፍጥ ምግብ
አዘጋጄለትና በመሶብ አድርጎ አቀረበለት፤ ልጁም እንጀራውን
እስክጠግብ በልቶት መሶቧን ወረወራት ። አባቱ "ልጄ ለምን
ወረወርካት?" ብሎ ጠየቀው። ልጁም "ምን ታረግልኛለች?
እንጀራንስ በላው" አለ። አባቱም "ልጄ ነገ ምናልባት እንጀራ
ባይርብህም ግን ችግር ልደርስብህ ይችላል በዛን ጊዜ ይህችን መሶብ ይዜህ ለምስክርነት ከዝህች መሶብ የበላው ሰው ነበርኩ ዛሬ ግን ቸግሮኝ ለልመና ወጣው ትላለህ መሶቧን
ሳትይዝ ብትወጣ ግን ማጅራት መቺ ዱርዬ ነህ ብለው
ይደበድቡሃል ልጄ ስለዝህም መሶቧ ታስፈልግሃለች" አለው።
ልጁም "አይ አባቴ አታስፈልገኝም" ብሎ መለሰለት። ያን ጊዜ
አባቱም "ልጄ በስሜ ትጠራ ይሆናል ነገር ግን የኔ ልጅ
አይደለህም ያበላችህን ቀኜን ክደሃታልና እኔ በዝህች መሶብ
ከብሬ አንተ ግን እሷን ካድካት" አለው።

ፓስተር፦ ምን ለማለት ፈልገህ ነው?

ኦርቶዶክሱ፦ "አባት የተባለው አብ ነው ፤ እንጀራ የተባለው
ወልድ ነው፤ መሶብ የተባለችው ድንግል ማርያም ናት። 'አብ
አንድ ልጁን አሳልፎ እስክሰጥ አለሙን እንድሁ ወዶአልና'
ተብሎ እንደተፃፈ! ወልድም 'የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ'
እንዳለ! ስለድንግል ማርያም 'ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን
ይላታል በውስጧ ሰው ተወልዷልና' እንደተባለ። አንተም አብ
በልጁ እንድትድንበት ብሰጥህ ዳንኩኝ በቃ ብለህ ለመዳንህ
ምክንያትየሆነችውን ድንግልን ካድካት። ርሃብ ባያጋጥምህ
እንኳን ለሌላ ችግር ትጠቅምሃለች የተባለው አንተ ሰው ነህ
በምትሰራው ኃጢአት ሁሉ ስለእናትህ ብለህ ማረኝ ብትለው
ጌታ ይምርሃል እናቱንም አንቺ ታስፈልግኛለሽ አማላጄ
ብትላት ሁሉ ሙሉ ይሆንልሃል። አንተ ግን ይህን ሁሉ
አልቀበል አልክ። አባት ልጁን በስሜ ትጠራለህ ግን ልጄ
አይደለህም እንዳለ አንተም ዛሬ በኢየሱስ ስም ትጠራለህ
ነገር ግን የሱ ልጅ አይደለህም አባትህን አንተም ታውቀዋለህ
ማን እንደሆነ! ያለ መሶብ እንጀራ እንዳሌለ ሁሉ ያለ ድንግል
ማርያምም ክርስቶስ የለም።

ፓስተር፦ "ጌታ ምስክሬ ግራ ገብቶኛል"

ኦርቶዶክሱ፦ "ለምን ግራ ይገባሃል?"

ፓስተር፦ "የጌታዬ እናት እንዳልላት ጌታ ጌታዬ ነው
ብፅዕት ብላት ደግሞ የሚቆጣኝ ሌላ ጌታ አለኝ"

ኦርቶዶክሱ፦"ለሁለት ጌቶች ነው እንዳ የምትገዛው?"

ፓስተር፦ "አይ ለ1 ጌታ ብቻ ነው የምገዛው"

ኦርቶዶክሱ፦ "ጌታህ ማነው? የሚቆጣህስ ሌላኛው ጌታ
ማን ይባላል??"

ፓስተር፦ "እሱ ሚስጥር ነው አይነገርም"
.......................................................................
"እመቤቴ ሆይ ! የናቁሽ ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ
ይሰግዱልሻል፤ የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮንም ይሉሻል"!!!!

ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የሲኦል ደጆች አይችሏትም
ቤተክርስቲያን አ.ት.ታ.ደ.ስ.ም!

ፀልዩ በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር! የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ሚስጢር)

ቤተክርስቲያን....
መሰረቷ ጉልላቷ እርሱ ነው
ሙሽራዋ መስቀል ላይ የሞተው
ዛሬም ነገም ያው ነው ለዘላለም
አትንገሩን አዲስ ጌታ የለም!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን-ይቆየን።
Posted on 09-12-16, 06:47 am (rev. 1 by Man on 09-12-16, 06:48 am)
Red Paragoomba


Karma: 100
Posts: 26/50
Since: 08-22-16

Last post: 965 days
Last view: 950 days
(የኔ ሃሳብ) ፥ አምላክ ይክበር ይመስገን። የድንግል አማላጅነት አይለየን።
_________________________
አመሰግናለሁ።
Posted on 02-04-17, 05:52 pm


Karma: 100
Posts: 1/1
Since: 02-04-17

Last post: 840 days
Last view: 839 days
" አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም። ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 4:1)

(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 1)
----------
23፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።

24፤ ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤ እጮኛውንም ወሰደ፤

25፤ የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።


(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 12)
----------
46፤ ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር።

47፤ አንዱም። እነሆ፥ እናትህና ወንድሞችህ ሊነጋገሩህ ፈልገው በውጭ ቆመዋል አለው።

48፤ እርሱ ግን ለነገረው መልሶ። እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው? አለው።

49፤ እጁንም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ። እነሆ እናቴና ወንድሞቼ፤

50፤ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ እኅቴም እናቴም ነውና አለ።
" የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 10:3)

Pages: 1