ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Marriage & Divorce . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 07-06-16, 03:26 pm (rev. 1 by Tg on 12-01-16, 05:37 pm)


Karma: 100
Posts: 131/444
Since: 07-20-15

Last post: 69 days
Last view: 69 days
ልብ የሚነካ የፍቅር ታሪክ
አንድ በጣሙን ደሃ የሆነ ሰው ከሚስቱ ጋር ይኖር ነበር፡፡ አንድ ቀን
ሚስቱ ጸጉሯን የምታበጥርበት ማበጠሪያ እንዲገዛላት ጠየቀችው፡፡ ባል
በጣም አዘነ፡፡
በኪሱ አንዳችም ገንዘብ ስለሌለው እያዘነ እንደማይችል ገለጸላት፡፡
ሌላው ይቅርና በቅርቡ ማሰሪያው ለተበጠሰበት የእጅ ሰዓቱ እንኳ
ማሰሪያ መግዛት ስላልቻለ በኪሱ ይዞት እንደሚዞር ማሰሪያው
የተበጠሰውን ሰዓት እያሳየ እንደማይችል ገለጸላት፡፡
ሚስትም ነገሩን ተወችው፡፡ ባል ወደ ሥራ ሲሄድ በአንድ የሰዓት
መሸጫ በኩል ሲያልፍ ወደ መሸጫው ገብቶ ማሰሪያው የተበጠሰውን
ሰዓት ሸጠ፡፡ ሌላ ሱቅ ገባ፡፡ ለሚስቱ በጣም የሚያምር ማበጠሪያ
ገዛ፡፡ ምሽት ላይ... ከ...ስራ ወደ ቤት ሲመለስ ዋንኛ ዕቅዱ ለሚስቱ
እንዴት ያንን የሚያምር ማበጠሪያ እንደሚሰጣት ነበር፡፡
ሚስቱን ሲያያት ግን ደነገጠ፡፡ ያ የሚያምረው ዘንፋላ ጸጉሯ በአጭሩ
ተቆርጧል፡፡ ባለማመን እንደተዋጠ የገዛላትን ማበጠሪያ ከቦርሳው
አውጥቶ ወደ እሷ ቀረብ ሲል አይኗ በእንባ እንደረጠበ በእጆቿ መሃል
የያዘችውን ነገር ተመለከተ - የሰዓት ማሰሪያ፡፡
ሰዓቱን ሸጦ ማበጠሪያ እንደገዛላት ሁሉ፣ ለካንስ እሷም ያን ዘንፋላ
ጸጉሯን አስቆርጣ ሸጣ የሰዓት ማሰሪያ ገዝታለት ነበር… ሁለቱም ፍቅር
በልባቸው እየነደደ በእንባ ታጠቡ…
Posted on 07-07-16, 02:53 pm


Karma: 90
Posts: 65/879
Since: 02-29-16

Last post: 66 days
Last view: 66 days
I like it nice story....read mine
Posted on 07-20-16, 11:26 pm


Karma: 100
Posts: 1/1
Since: 07-20-16

Last post: 1036 days
Last view: 1036 days
Knight
Posted on 07-21-16, 07:54 am


Karma: 100
Posts: 133/365
Since: 07-14-15

Last post: 244 days
Last view: 244 days
Like it Tg'ye
Posted on 07-23-16, 12:37 am


Karma: 100
Posts: 1/1
Since: 07-23-16

Last post: 1033 days
Last view: 1033 days
Nice story
Posted on 08-18-16, 10:19 am


Karma: 100
Posts: 1/3
Since: 08-18-16

Last post: 1003 days
Last view: 946 days
ilike it nice
Posted on 02-10-17, 11:53 am


Karma: 100
Posts: 4/5
Since: 09-20-16

Last post: 827 days
Last view: 812 days
i know this story when i was a childhood
Pages: 1