ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Personal Blog የመጣጥፍ ቦታ. | 1 guest | 2 bots
Pages: 1
Posted on 06-03-16, 11:27 pm


Karma: 90
Posts: 44/879
Since: 02-29-16

Last post: 64 days
Last view: 64 days
"ችግርን ማስቸገር"
(ይበልጣል ስዩም☞ ይሳኮር)
"ስኬት ማለት ውድቀት ሲገጥም የጉጉት ስሜትን ሳያጡ መጓዝ ማለት ነው"
ዊንስተን ቸርችል
ኦፕራ 1954 በሚሲሲፒ ከተማ ተወለደች።ገና ከጨቅላነቷ አነስታ ፈተና የተጋረጠባት ኦፕራ ዝቅተኛ ገቢ ካላት እናቷ ከጎኗ ሳትኖር ፍቅርን ተርባ የሴት አያቷ ጋር አደገች። ከአያቷ ጋር በነበረችበት ሰአት በብዙ የህይወት እንቅፋቶች ተመታለች። እናቷ ገና እንደተወለደች ጥላት በመሄዷም የእናት ፍቅር ተርባ ድሆች በብዛት በሚኖሩበት አካባቢ መኖር እጣ ፈንታዋ ሆነ። በቦታው ካሉ ሰዎች በላይ ድህነታቸው ስር የሰደደ ነበር። በልተው የማያደሩበት
ቀናትም የተበራካቱ ነበሩ። በምትለብሰውም ልብስ የተነሳ እኩዮቿ ይሳለቁባት ነበር።
ድህነት ከሚያሳድረው ተፅእኖ በላይ ግን ከዘጠኝ አመቷ ጀምሮ ይደርስባት የነበረው ተደጋጋሚ ወሲባዊ ጥቃት እጅግ የከፋ ነበር። አስገራሚ የነበረው ደግሞ ወሲባዊ ጥቃት ሲደርባት የነበረው በአጎቷ፣ በአጎቷ ልጆች እና በቤተሰቧ የቅርብ ጓደኞች መሆናቸው ነበር!! በዚህም የተነሳ ገና በጨቅላነቷ ባልጠነከረ ገላዋ በ14 አመቷ አርግዛ ትወልዳለች። ልጁ ግን በተወለደ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሞተ።
ይህን ሁሉ የህይወት ስንክሳር ቢገጥማትም የነገዋን እና ጠንካራዋን አፕራ ለመፍጠር ምኞቷ ነበር። ታዲያ በዛው አመት እናቷ የተሰተካከለ ኑሮ እንድትኖር አባቷ ወዳለበት ቴንሲ ከተማ ትለካታለች ከጊዜም በኋላ ትኖርበት በነበረው አካባቢ ባለው ቴንሲ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት እድል ታገኛለች። በዩኒቨርስቲውም ኮሚዩኒኬሽን ( ተግባቦትን) ማጥናት ጀመረች። ከዛ በፊት ትማርባቸው በነበሩት ትምህርት ቤቶችና ኮሌጆች እና በክልል የሬዲዮ ጣቢያዎች ላይ መሳተፏ የትምህርት ክህሎቷን እንድታሳድግና የትምህርት ዘርፏን እንድትመርጠው አድርጓታል።
እንደዛም ሁኖ ነገሮች አልጋ በአልጋ አልነበሩም ዜና አንባቢ ሁና መስራት ብትፈለግም አትመጥኝም ተብላ ተመልሳ ታውቃለች የኋላ የኋላ ግን ባልቲሞር በሚገኝ ጣቢያ ዜና አንባቢ ሁና መስራት ጀመረች። ባጭር ጊዜ ውስጥም People are Talking የሚባል ቶክ ሾው በአቅራቢነት መስራት ጀመረች።1983 ወደ ቺካጎ ተመልሳ ዝቅተኛ ተመልካች
የነበረውን AM chikago የተሰኘውን ቶክ ሾው ላይ መስራት ጀመረች በጥቂት ወራት ውስጥ ግን በዛ ጊዜ በተመልካች ብዛት አንደኝነቱን ተቆጣጥሮ የነበረውን phil Donahue ቶክ ሾው መብለጥ ቻለች በዚም የተነሳ የቶክ ሾው ስሙ ወደ ኦፕራ ሾው ተቀየረ።
ይህቺ ሴት ከብዙ ስቃይና እንግልት በኋላ በጥረቷ ሂወትን ማሸነፍ ችላለች። በመከራ ውስጥ ተስፋ ላለመቁረጥ መታገል ለስኬት መጓጓት ከባድ ቢሆንም በድል ተወጥታዋለች። በወቅቱ ለሴት ልጅ እና ለጥቁሮች ያለውን መጥፎ አመለካት በጥረቷ መታገል የቻለች ጠነካራ ሴት ናት። ለችግሮች እጅ ከመስጠት ይልቅ ነገሮችን በእችላለው ስሜት ዛሬ ያለችበት ቦታ ላይ ደርሳለች። በአለም ተፅእኖ መፍጠር ከቻሉ ሴቶችም ግንባር ቀደሟ ነች። በጥበቡ ኢንዱስትሪም ይህ ነው የማይባል አስተዋፆ አበርክታለች። በአሁን ሰአት 2.9 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ሀብት
መካበት የቻለች ዝነኛ ሰው መሆን ችላለች። "ችግርን ማስቸገር የስኬት ሁነኛ ቁልፍ ነው!!"
Pages: 1