ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Religion. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 06-02-16, 12:36 pm (rev. 1 by Melat on 04-24-17, 04:33 am)


Karma: 100
Posts: 92/426
Since: 07-12-15

Last post: 69 days
Last view: 69 days
~ በዘመኑ ሁሉ ፍጹም ሰላምን እግዚአብሔር ይሰጣት ዘንድ ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንማልዳለን፤
~ ዕውቀትን እሱን መፍራትንም እግዚአብሔር ይሰጣቸው ዘንድ ስለመኳንንትና ስልጣን ስላላቸው እንማልዳለን፤
~ ስለ ዓለሙ ሁሉ እግዚአብሔር ማሰብን ያስቀድም ዘንድ እያንዳንዱም የሚያስፈልገውን ያማረውን የሚሻለውንም ያስብ ዘንድ ስለ ዓለሙ ሁሉ እንማልዳለን፤
~ እግዚአብሔር ይቅርታ ባለው ቀኝ መርቶ በፍቅር እና በደኅንነት ወደ ማደሪያቸው ይመልሳቸው ዘንድ በባህር እና በየብስ ስለሚሄዱ ሰዎች እንማልዳለን፤
~ እግዚአብሔር የዕለት የዕለት እንጀራቸውን ይሰጣቸው ዘንድ ስለተራቡና ስለተጠሙ ሰዎች እንማልዳለን፤
~ እግዚአብሔር ፈፅሞ ያረጋጋቸው ዘንድ ስላዘኑ እና ስለተከዙ ሰዎች እንማልዳለን፤
~ እግዚአብሔር ከእስራታቸው ይፈታቸው ዘንድ ስለታሰሩ ሰዎች እንማልዳለን፤
~ እግዚአብሔር በሰላም ወደሃገራቸው ይመልሳቸው ዘንድ ስለተማረኩ ሰዎች እንማልዳለን፤
~ እግዚአብሔር ትዕግስትን በጎ ትምህርትንም ይሰጣቸው ዘንድ የድካማቸውንም ፍጹም ዋጋ ይሰጣቸው ዘንድ ስለተሰደዱ ሰዎች እንማልዳለን፤
~ እግዚአብሔር ፈጥኖ ያድናቸው ዘንድ ይቅርታውንና ቸርነቱንም ይልክላቸው ዘንድ ስለታመሙትና ስለድውያኑ እንማልዳለን፤
~ ከቅድስት ቤተክርስቲያን ወገን ስለሞቱ ሰዎች እግዚአብሔር የእረፍት ቦታ ይሰጣቸው ዘንድ እንማልዳለን፤
~ እግዚአብሔር እንዳይቀየማቸው ከመዓትም ተመልሶ ፍጹም ዕረፍትን ይሰጣቸው ዘንድ ስለበደሉ አባቶቻችን እና ወንድሞቻችን እንማልዳለን፤
~ በሚያስፈልግበት ቦታ እግዚአብሔር ዝናቡን ያዘንብ ዘንድ ስለ ዝናብ እንማልዳለን፤
~ የወንዙን ውሃ ምላልን ብለን እግዚአብሔር እነሱን እስከ ልካቸውና እስከወሰናቸው ይመላ ዘንድ ስለወንዝ እንማልዳለን፤
~ ለዘር እና ለመከር ሊሆን እግዚአብሔር ለምድር ፍሬዋን ይሰጣት ዘንድ ስለ ምድር ፍሬ እንማልዳለን፤
~ በጸሎት የምንለምንና የምንማልድ ሁላችንንም በሰላም በመንፈስ ይጠብቀን ፍቅርንም ይስጠን ዓይነ ልቡናችንን ያብራልን ፈቃዱም ሆኖ ጸሎታችንን ይቀበል ዘንድ ቀርበን እግዚአብሔርን እንለምነው!
ዐውቀን በሃብቱ እናድግ ዘንድ በእርሱም ስም እንመካ ዘንድ...በነቢያት በሐዋርያትም መሰረት ላይ እንታነጽ ዘንድ እንግዲህ በመንፈስ ቅዱስ እንነሳ!!! ቀርበን አምላካችን እግዚአብሔርን እንለምነው ወዶ ጸሎታችንን ይቀበል ዘንድ።
አሜን+++

Posted on 06-03-16, 06:07 am


Karma: 100
Posts: 114/365
Since: 07-14-15

Last post: 247 days
Last view: 247 days
Amen Amen
Posted on 09-01-16, 03:26 pm


Karma: 100
Posts: 10/610
Since: 08-27-16

Last post: 84 days
Last view: 2 days
የሁላችንም፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንደዚህ፡ሲል፡ቃል፡ኪዳን፡ገብቶአል።
ትንቢተ፡ኤርምያስ፡ምእራፍ፡31ቁጥር፡32

ሕጌን፡በልቡናቸው፡አኖራለሁ፥በልባቸውም፡እጽፈዋለሁ።እኔም፡አምላክ፡እሆናቸዋለሁ፤እነርሱም፡ሕዝብ፡
ይሆኑኛል። እያንዳንዱ፡ሰው፡ባልንጀራውን፥እያንዳንዱም፡ወንድሙን፣እግዚአብሔርን፡እወቅ፡ብሎ፡
አያስተምርም፤ከታናሹ፡ጀምሮ፡እስከ፡ታላቁ፣ድረስ፡ሁሉ፡ያውቁኛልና፥ይላል፡እግዚአብሔር። በደላቸውን፡
እምራቸዋለሁና፥ኀጢአታቸውንም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አላስብምና።

Pages: 1