ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Ethiopian News & Events አዲስ ዜና. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 06-22-19, 04:44 pm


Karma: 100
Posts: 769/769
Since: 03-20-17

Last post: 24 days
Last view: 24 days
በአማራ ክልል የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተደረገ
*****************
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉን የጠቅላይ ሚንስትር ፕሬስ ሴክሬተሪ ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን አስታወቁ፡፡
በክልልሉ ዛሬ በተደራጀ ሁኔታ በመንግስት መዋቅር ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መሞከሩን አቶ ንጉሱ ገልፀዋል፡፡
በክልሉ መፈንቅለ መንግስት በማካሄድ የመሪ ድርጅቱ አዴፓ እና የአማራ ክልል ህዝብ ያገኘውን ነፃነትና ሰላም ለመንጠቅ እንዲሁም በህዝቡና በመንግስት ላይ ጥቃት ለመፈፀም የተደራጀ እንቅስቃሴ መደረጉንም ነው አቶ ንጉሱ የገለፁት፡፡
የተደረገውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የፌደራል መንግስት የፀጥታ መዋቅር ክልሉን በተለይም ባህርዳር ከተማና አካባቢውን በቁጥጥር ስር አውሎ በተግባሩ የተሳተፉት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ትእዛዝ መሰጠቱም ተገልጿል፡፡
ህብረተሰቡም አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ ጥሪም ቀርቧል፡፡

Posted on 06-22-19, 04:51 pm


Karma: 90
Posts: 880/883
Since: 02-29-16

Last post: 5 days
Last view: 5 days
ሰምተን መጣን እኮ ዘይገርም ዘይገርም ነው
Pages: 1