ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 2 guests | 1 bot
Pages: 1
Posted on 06-12-19, 06:19 pm


Karma: 100
Posts: 767/769
Since: 03-20-17

Last post: 168 days
Last view: 168 days
ህይወት የሚደምቀው በፍቅር እንጂ በብር አይደለም.....ገንዘብ በማንኛውም ሰአት ከሰራሽ ልታገኚው ትችያለሽ ፍቅር ግን ከፈጣሪ ነውና የሚገኘው አብዝተሽ አምላክሽን ለምኚ ወንድ ልጅ ከወደደሽ ራሱን ይሰጥሻል ይህ ማለት ደሞ አንቺ እንደፈለክሽ አንገት ሆነሽ ታዞሪዋለሽ ....ብዙ ሀብት ኖሮት ምንም ስብእና ወይም ላንቺ ክብር ከጎደለው ሰው ጋር አይደለም ትዳር ለአንድ ቀን አድሮ መለየት አትመኚ በማስመሰል እራሱን ደብቆ የሚመጣ አስመሳይ ወንድ ወጥመድ እንዳትገቢ ጥንቃቄ ይኑርሽ .... ብዙ ወንድ በማስመሰል የሚፈልገውን እስኪያገኝ የማይፈልገውን ያደርጋልና .... እንዲ አይነቱ ወንድ በኑሮ ህይወት እንደ እስስት ሲቀያየር ትመለከችዋለሽ .....
በውሳኔው የማይፀና አቋም የሌለው ሰው ላይ ብትወድቂ እድሜሽን በሙሉ ስትንከራተተቺ ትኖርያለሽና እንደዚ አይነቱን ወንድ ለማስተካከል ካልቻልሽ በትዳር እንዳትታሰሪ ጠንቃቃ ሁኚ......ደስታ የሚገኘው የውስጥ ፍላጎት በነፃነት መግለፆ ሲቻል ነውና ነፃነትሽን የሚነፍግ ፍላጎትሽን የማይጠብቅ ወንድ ገና ሲጀመር አትቅረቢው እንደዚ አይነት ወንድ ምን ጊዜም እራሱ የሚያወራውን እንጂ አንቺ የምታወሪውን አይሰማም ቢሰማም ቦታ ይሰጠውም እሱ የወደደው እንጂ አንቺ በመረጥሽው መንገድ አይጓዝም ና........
አንቺ ለምትናገሪው ለምታደርጊው ነገር ስህተት ቢመስለው እንኳን በቀስታ እንጂ ጮሆ ለሚናገር ወዳጅ አታበጂ ዛሬ ከጮኸብሽ ነገ ሊመታሽ እንጂ የሚያነሳው ምንም ምክንያት የለውምና........
ከሀብት ከቁሳቁስ ንጹህ ልብ ንጹህ ፍቅርን የሚሰጥሽ ወንድ ተመኚ ....
የወንድን ያለውን ሀብት ወይም ኪሱን ሳይሆን ይዞ የመጣውን ንጹህ ፍቅር ተመልከቺ እንደዚ አይነት ወንድ ትልቅ ዛፍ ሆኖ ሊጠልልሽ ፍሬ ሊሰጥሽ ይችላልና ምክንያቱም የሁሉ መሰረት ፍቅር ነውና ደስታ የሆነ ህይወት ከፈለክሽ ግን እህቴ ሁል ጊዜም አስተውይ ብር ሳይሆን ላንቺ ክብር ያለው ወንድን አግቢ !!!፡፡
Pages: 1