ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Education - ትምህርት. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 06-10-19, 07:58 pm


Karma: 100
Posts: 764/769
Since: 03-20-17

Last post: 350 days
Last view: 350 days
#ሳይኮሎጂ_ፈተና
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ የ 3ኛ አመት የሳይኮሎጂ ተመራቂ ጓደኛሞች ነገ Final ፈተና እያላቸዉ ማታ ሲጠጡና ሲጨፍሩ አመሹ ፡፡ እናም ወደ ተከራዩበት ቤት ሲመለሱ ለማጥናት ጊዜ ስላልነበራቸዉ ወዲያዉ ተኝተዉ ጠዋት በመነሳት ወደ መፈተኛ ክፍሉ ይሯሯጣሉ ፡፡
በዚህ ጊዜ ሳያጠና መፈተኑ የጨነቀዉ አንድ ተማሪ አሪፍ ሀሳብ ያቀርባል ፡፡
"ለምን ግን ሳናጠና ከምንፈተን ፥ አስተማሪያችንን ትናንት ማታ ወደ ግቢ ላይብረሪ ስንመጣ የምንመጣበት ታክሲ ጎማ ፈንድቶ እሱ እስኪስተካከል ጠበቅን ከዛም ደግሞ በመንገድ ላይ አንዱ ጓደኛችን ታሞ እሱን ሆስፒታል ወሰድን ግቢ እንደገባንም ስለደከመን ሳናጠና አደርን አንለዉም " የሚል ሃሳብ አቀረበ ፡፡ በዚህ ጊዜ ሁለቱም በሀሳቡ በደስታ ተስማምተዉ ለአስተማሪዉ ሊነግሩት ወደ ቢሮዉ በፍጥነት አመሩ ፡፡ የሳይኮሎጂዉ ፕሮፌሰርም ባጋጠማቸዉ ነገር እጅግ በጣም አዝኖ ለነሱ ብቻ ሌላ ፈተና አዉጥቶ በነጋታዉ ሊፈትናቸዉ ተስማሙ ፡፡
3ቱ ጓደኞችም በብልጠታቸዉ እጅግ በጣም ተደስተዉ ቀጥታ ወደ ኬኔዴ ላይብረሪ ገብተዉ ማጥናት ጀመሩ ፡፡ በዛን ቀን ደግሞም ማታዉን ጨምረዉ ወጥረዉ ሲያጠኑ ካማሹ በኅላ በነጋታዉ ለፈተና ቀረቡ ፡፡ አስተማሪዉም ሌላ አንድ ፈታኝ አስተማሪ ጨምሮ 3ቱን ተመራቂ ተማሪዎች ሰፊ ክፍል ካስገባቸዉ በኀላ አራርቆ አስቀምጦ የፈተና ወረቀ ሰጣቸዉ ፡፡
3ቱም ጎደኞች ያለፈዉ ቀን እጅግ በጣም አጥንተዉ ስለነበር በተጨማሪ ትናንት ከተፈተኑት ጓደኞቻቸዉ ስለ ፈተዉ ብዙ መረጃ ይዘዉ ገብተዉ ስለነበር ፈተናዉን እንደሚሰቅሉት ያላንዳች ጥርጣሬና በሙሉ መተማመን ነበር የገቡት ፡፡
የሳይኮሎጂ ፕሮፌሰሩም የፈተና ወረቀቱን ሰጣቸዉና በሉ ስሩ ተማሪዋቼ አለ ፡፡ 3ቱም ተማሪዋች ፈተናቸዉን ገልብጠዉ ስማቸዉንና ID ቁጥራቸዉን ከፃፉ በኀላ ጥያቄዉን ማንበብ ጀመሩ ፡፡ ጥያቄዋቹ እንዲህ የሚሉ ነበሩ ?
1. የፈነዳዉ የታክሲ ጎማ የትኛዉ ነበር ?
ሀ.የፊት ቀኝ ለ.የፊት ግራ
ሐ. የኀላ ቀኝ መ.የኀላ ግራ
2.ጎማዉ የፈነዳዉ የት አካባቢና ስንት ሰአት ነዉ?___________________
3. ጎማዉ የተቀየረዉ የት ጎሚስታ ቤት ነዉ?
________________
4.የታመመዉን ጓደኛችሁን የት ሆስፒታል ወሰዳችሁት?
_______________
መልካም ፈተና !

Pages: 1