ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Health - ጤና. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 05-02-19, 03:33 pm


Karma: 100
Posts: 758/769
Since: 03-20-17

Last post: 409 days
Last view: 409 days
"ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ሆስፒታሌ የምርመራ መሳሪያ ስለሌለ ታካሚዎቼን ወደ ኬንያ እልካቸዋለው"
.
እንደኔ ወደህ ፣ መርጠህ አሊያም ደግሞ ፈርዶብህ ተገደህ የዳር ድንበር ሃኪም ብትሆን ማዶ ማዶዉን ስትመለከት የሚነሳብህን ራስ ምታትና ጨጓራ ለማስታገስ እነ Paracetamol, Omeperazole ን በየቀኑ እየተመገብክ ትኖራለህ፡፡
.
ማዶ ያለዉ የኬንያዉ ሆስፒታል ከኢትዮጲያዉ 2 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ አንዳንዴ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁ "ዉጭ ሀገር" ልሂድ ብለህ ወይ ደግሞ የሆስፒታልህ ላብራቶሪ Hemoglobin መስራት አቅቶት (CBC, OFT are just dream!) sample ይዘህ እዚያ ለምነህ ልታሰራ ትሄዳለህ፡፡ አሊያ ደግሞ የኦፕራሲዮን ክፍሉ በ አዉቶክሌቭ ወይም በሆነ ነገር ብልሽት functional ሳይሆን ይቀርና ኦፕሬሽን (Emergency C/S) የሚያስፈልጋትን ሚስኪን እናት ይዘህ ማዶ ያለዉ "የዉጭ ሃገሩ GP" C/S እንዲሰራ ለመማጸን ተሯርጠህ ትሄዳለህ።
.
ሆስፒታል ስትገባ ጥበቃዉ ፣ ጽዳቱ ፣ ጥራቱ ፣ የላቦራቶርና ሌሎችም የህክምና ዕቃዎች ፣ ጥራታቸዉ….፡፡ ነጭ ለባሽ ሁሉ "Docta" እየተባለ ነዉ የሚጠራዉ። ነርሱ ፣ ላቦራቶሪ ቴክኒሺያኑ እንዴት አንደሚያብጠለጥሉህ…GPዉን ብዙ ግዜ በስልክ ካልሆነ በአካል አታገኘዉም።
.
እድለኛ ሆነህ "I am a docta, don’t waste my time" ብሎ ስልኩን ካልዘጋብህና ካገኘሀዉ አንተ በርሱ ፊት ምንም ነህ! ሰባ እና ሰማንያ ሺህ ብር (የኬንያ ሽሊንግ አላልኩም…ብር) እየተከፈለዉ በሙያዉ ተከብሮና ተፈርቶ በሚኖር ሰዉ ፊት አንተ ማለት….የበረሃዉ ፀሐይ ያጠወለገህ ፣ ከነበረሃ አበል ስድስት ሺህ ምናምን እየተከፈለህ የምትኖር ደሃ ፣ Duty በጀት ስለሌለ ወይም…በወር ሦስት ወይም አራት ቀን አድረህ ከ750 ብር-1300 ብር (Honestly) ብቻ የምታገኝ ፣ አንዳንዴ ጥይት በጆሮህ እያለፈ ወይም በ ፊልም ብቻ የምታዉቀዉ ድምጹ ብቻ ነብስ የሚያስወጣ ከባድ መሳርያ እየተተኮሰብህ በእግዚአብሄር ምህረት ብቻ በሕይወት እየኖርክ ሕዝብ የምታገለግል ፣ የፈረደብህ ዕለት ቦምብ ፈንድቶ አስር ሆነህ ሀምሳ ቁስለኛ ለመርዳት ስትሯሯጥ ደም እየፈሰሰብህ Risk allowance 0 ብር ከ00 ሳንቲም የሚከፈልህ ፣ ልማር ልደግ ብትል ሌላ ሶስትና አራት የድህነትና የባሰ ባርነት ዓመታት ፍንትዉ ብለዉ የሚታዩህ …ወዘተ ሰዉ ነህ፡፡
.
ከፊትህ ያለዉ የዉጭ ሀገሩ GP ብትሆን ይሄኔ "100 day doctors strike" ብለህ ለመብትህ ወተሃል፡፡ ከዉጭ ሀገሩ GP ጋር በዚያ እንግሊዘኛዉ መከራ እያህ አዉርተህ ፣ ስለ ህክምና ምናምን ካወራህ ደግሞ የማያዉቀዉን ሳይንስ አስተምረሄዉ ወደ እናት ሀገርህና መቼም ጥሎህ ወደማይሄደዉ ዉዱ ጓደኛህ ድህነት ስትመለስ በሁለት ኪሎ ሜትር ያለዉ አስር እጥፍ ልዩነት ጆሮህ ዉስጥ እያቃጨለብህ የፈጋህለትን የDegreeህን ወረቀት ጨብጠህ ሀገርህን የምትሰናበትበት ቀን ይናፍቅሃል፡፡
.
ሐኪም በመሆንህ የተሸወድክና የተረገምክ ከመሰለህ ጓዴ እኔ ልንገርህ የተሸወደች ሀገር ዉስጥ ሐኪም ሆንክ እንጂ አንተ አልተሸወድክም!! ቀንበር ተጭኖብህ ለሕዝብህ ስትፈጋ እንደነ ቀይ ቀበሮና ዋሊያ አይቤክስ ሌላዉ አለም ማይሆንልህ ሆነህ አይደለም ቸልተኞች ቀንበር ጭነዉ ስለሚያርሱብህ ነዉ፡፡
.
BREAK THE SILENCE AND LIBERATE THE HEALTH SYSTEM
ዶ/ር አየነው ከሞያሌ ሆስፒታል

Pages: 1