ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Ethiopian News & Events አዲስ ዜና. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 04-20-19, 08:23 pm (rev. 1 by ጮሌው on 04-20-19, 08:24 pm)


Karma: 100
Posts: 756/769
Since: 03-20-17

Last post: 242 days
Last view: 242 days
ሸኮናው እንዳይቀር
በበግ እና በሰንጋ በሬ የሚታወቀው የአማራ ክልል ዛሬ ደግሞ አስገራሚ ዜና ተስምቱዋል።
ይህ ሰንጋ በሬ 98,000 ብር የመጨረሻ መሸጫው የሆነ በአገሪቱ ሪከርዱን የሰበረ ሲሆን ከጎጃም የደለበው በግ ደግሞ 15,000 ብር እንደተሸጠ ተሰምቱዋል።
በብግ አቅርቦት የአገሪቱን 56% የሚሸፍነው አማራ ክልል በዚህ አመት የደለቡ በሬወች እና በጎች ለየት ያሉ ሆነዋል።
በተለይ በጎቹ የላታቸው መጠን እስከ አምስት ኪሎ የደረሱ እንዳሉ ነው የተሰማው።
ይህን በሬ 98,000 ብር የገዛው ሰው ግን እግዚዮ ነው በቃ በሬ መቶ ሺ ብር ገባ??
ቅርጥፍጥፍ አርገው ሊበሉት ነው ማለት ነው? ሸኮናው የለ ቆዳው ወዳጀ በሬው በትንሹ የተጣራ 200 ኪሎ ስጋ ቢኖረው በትንሹ አንዱ ኪሎ ስጋ 490 ብር መሆኑ ነው።
እውነት ለመናገር እኔ ከበሬው ይልቅ በጉ በስማም ያስጎመጃል ወይኔ ብዙ ቬጋን ባልሆን ኖሮ ይሄን የበግ ስጋ ባሳየሁት ነበር።
ግሩም ነው ወዳጀ በሬ መቶ ሺ ብር ገባ እያየነው በዚህ ፍጥነቱ ምናልባት በቀጣይ አስር አመት አንድ ሚሊዮን መግባቱ ነው ።
ያኔ እንተያያለን አንድ ሚሊዮን ገዝተሽ በእኛ ሰፈር ስጋ እበላለሁ ያልሽ ሁሉ ጦርነት ነው ምንከፍተው እንዴ አልበዛም እንዴ ጎበዝ ድሆች የትን ይኑሩ ።


Pages: 1