ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 03-31-19, 03:21 pm
Administrator

Karma: 100
Posts: 150/163
Since: 02-10-19

Last post: 449 days
Last view: 399 days
ስምንት የአማላይ ሴቶች ባህሪና እነሱን መልሶ ማማለያ ምስጢር ክፍል 2

ሴት ልጅ ምንም ጊዜ ቢሆን የመደነቅና የመወደድ ስሜቷ አይረካም፡፡ ሁሌም ቢሆን የነገሮች ማዕከል ሆና መገኘት ትፈልጋለች፡፡ ታዲያ እሳቷ ሴት ሁሌም ቢሆን ተውባ ተሽቀርቅራና በወንዶች ተከባ መገኘት የምትፈልግ ናት፡፡ በህይወቷ የምትፈልገው ነገር ሁሉ በነፃነት ማውራት፣ ጮክ ብሎ መሳቅ፣ ፍቅር በመስራት መደሰት በአካባቢው ውስጥ ገኖ መታየትን ነው፡፡ ይህችን ሴት ለማግኘት ታዲያ ይህን ስሜቷን ማወቅ ይኖርብሃል፡፡ ስሜቷ መፈለግ ስለሆነ የተለየች ሆና እንዲሰማት ማድረግ ይገባሃል፡፡ ግን ደግሞ እንቅስቃሴህ በዚህ ብቻ ሳይገታ ሁሌም ይህን ጉዳይ ሁሉም ሰው የሚነግራትና የምታየው ስለሆነ ያለአንተ አብረሃት መኖር እሷ ጎልታ እንደማትታይ እንዲሰማትና ሁሌም አንተን እንድትሻ የማድረግ ከባድ የቤት ስራ አለብህ፡፡ መሳሳት የሌለብህ እሳቷ ሴት ሁሌም ቢሆን በወንዶች መከበብ ፀጋ የታደለች ነች፡፡ የቤት ስራህን ለመጀመርም መጀመሪያ አንተ እንደሌሎች ወንዶች ሁሉንም ነገር በፀጋ መቀበል የለብህም የራስህ አቋም ካለህ የሷ እሳትነት አንተን የማይሞቅህ እንዲመስላት ማድረግ ከቻልክ በእርግጠኝነት ከመሞቅ አልፎ እንደምታቃጥል ልታሳይህ ትጥራለች፡፡ ያኔ ታዲያ ለሷ ማማር ያንተ ከጎኗ መሆን እንደሚያስፈልግ ታሳያታለህ፡፡
Pages: 1