ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 1 guest | 3 bots
Pages: 1
Posted on 03-30-19, 12:59 pm
Administrator

Karma: 100
Posts: 148/163
Since: 02-10-19

Last post: 449 days
Last view: 399 days
ሴት ልጅ እንዳፈቀረችህ የምታቅበት መንገድ- በምታወሩበት ጊዜ እጇን ካጣመረች መጨናነቋን ወይም በሁኔታው ምቾት
እንዳልተሰማትአመላካች በመሆኑ እስትራቴጂህን ወይም ስልትህን በፍጥነት
መቀየር ይኖርብሃል፡፡ ሌላው ከዚሁ ከማጣመር ጎን የሚያያዘው የእግር ማጣመር
ነው፡፡ እግር ማጣመር ልክ እጅን የማታመር ያህል መጥፎ ሲሆን ይህን አጋጣሚ
የበለጠ መጥፎ የሚያደርገው ደግሞ አንድ ጊዜ እግሯን ካጣመረች እጇንም
የማጣመር ሁኔታ ከፍተኛ መሆኑ ነው፡፡ ይሁንና እግሯን አጣምራም ቢሆን
ጉልበቶቿ ወደ አንተ ከዞሩ ትንሽ ከመጨነቋ ውጪ ከአንተ ላይ ፍላጎት እንዳላት
ያመላክታል፡፡ ተቃራኒው ሆኖ ጉልበቷ በሌላ አቅጣጫ ከዞረ ግን ችግር ውስጥ ነህ
ማለት ነው፡፡
ወደኋላ መሸሽ ወይም መለጠጥ፡- ወንበር ላይ ከአንተ ራቅ ብላ ወይም ተለጥጣ
የምትቀመጥ ከመሆን በደንብ የሚስተዋል አንተን ያለመሻቷ መገለጫ ነው፡፡
ስለዚህ የእኔ ምክር የሚሆነው የዚህ አይነት አካላዊ እንቅስቃሴዎችን በምታይበት
አጋጣሚ ጨዋታውን ጥሎ መውጣት ብቻ ነው መፍትሄ የሚሆነው በእንደዚህ
አይነት አጋጣሚ ሴቷን የራሳቸው ማድረግ የሚችሉት ልምዱ ያላቸው ብቻ
ናቸው፡፡ የአካላዊ እንቅስቃሴ ማታለያዎች
አንድ ሴት አንተን እየተከታተለችህ መሆኑንና ያለመሆኑን ለማወቅ አንድ
የሚያስቅና የሚሰራ ማታለያ ልንገርህ፡፡ እሷ አንተን በምታይበት ሁኔታ ላይ ሆነህ
ሰዓትህን እያየህ በዝግታ ከ1-3 ቁጠርና ቀና ብለህ እያት፡፡ እሷም ሰዓቷን እያየች
ከሆነ አንተን ስታይህ እንደነበር እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡ ይህ ተፈጥሯዊ የሆነ
አንተን የሚወድ ሰው ባህሪ ነው፡፡ ልክ አንተ ሰዓትህን ማየት ስትጀምር እሷም
ምን እየጠበክ እንደሆነ በማሰብ ሰዓቷን ታያለች፡፡ ተጨማሪ የአካላዊ እንቅስቃሴ
መረጃዎች 1. ፀጉር ማፍተልተል
አብዛኛውን ጊዜ ፀጉሯን የምታስተካክል ወይም የምታፍተለትል ሴት የወንዶችን
አይን ለመማረክ የምትሞክረው ናት፡፡ ፀጉር ማፍተልተሏንም ሆነ መነካካቷን
በደቂቃ ውስጥ ሶስት ጊዜ የምታደርገው ከሆነ መያዝም ሆነ መታየትን
የምትፈልግ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡ ሌላው ደግሞ
ፀጉሯንየምትነካበት መንገድም የራሱ የሆነ መልዕክት እንዳለው መዘንጋት
የለብህም፡፡ ይህም ፀጉሯን በቀስታ የምትነካካ ከሆነ የፍቅር ጥበብ እንዳላት
ማወቅ የምትችል ሲሆን ከፈጠነች ደግሞ ማፈሯንና ትዕግስት አልባ መሆኗን
ማየት ትችላለህ፡፡
2. የብርጭቆ ጠርዝ ላይ እጅን ማሽከርከር
በሲግመንድ ፎርይድ ቲዎሪ መሰረት ይህ ምልክት ለወሲብ የመጋበዝ ያህል ነው፡፡
ይህ አባባል ታዲያ በብዙ ሴቶች ተደግፏል፡፡ ይህን ጊዜ ታዲያ የጣቶቿን
እንቅስቃሴ ልብ ማለት አለብህ፡፡ በዝግታ ጣቶቿን የምታሽከረክር ወይም
የምታንቀሳቅስ ከሆነ ጥልቅ የሆነ እርጋታን፣ እራስ መቆጣጠርንና ጥበቃን
አመላካች ስለሆነ ከጎኗ ልትቀመጥ ትችላለህ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ በጥፍሯ
ብርጭቆውን መምታት ከጀመረች ለነገሮች ትዕግስት ማጣቷንና መቸኮልን ወይም
በሌላ መልኩ በወንድ ጓደኛዋ መናደዷን አመላካች ነው፡፡

ይቀጥላል ....
Pages: 1