ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 1 guest | 4 bots
Pages: 1
Posted on 03-28-19, 05:59 am
Administrator

Karma: 100
Posts: 147/163
Since: 02-10-19

Last post: 449 days
Last view: 399 days
ሴት ልጅ እንዳፈቀረችህ የምታቅበት መንገድየቅርብ ጊዜ የስነ ልቦና ጥናታዊ ሪፖርቶች… ሴት ልጅ ለአንተ ልዩ ፍቅርና
መውደድ እንዳላትና እንደሌላት አዕምሮዋን በአካላዊ እንቅስቃሴዎቿ በኩል
በቀላሉ እንድታነብ ያስችሉሃል!!
አካላዊ እንቅስቃሴዎች ዋነኛዎቹ የመግባቢያ መንገዶች ናቸው፡፡ እነዚህ
እንቅስቃሴዎች ግልፅ አካላዊ እንቅስቃሴና ዝግ አካላዊ እንቅስቃሴ ይባላሉ፡፡
አካላዊ እንቅስቃሴዎች በራሳቸው ቋንቋ በመሆን ከንግግርም በላይ በሆነ መልኩ
መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡ እንዲህ አይነት ተግባቦት በአብዛኛው በተቃራ ፆታ
ግንኙነት ውስጥ በተለይም በሴቶች ላይ ይስተዋላሉ፡፡ ግልፅ አካላዊ እንቅስቃሴ
አንድ ጊዜ ከሴት ጋር አይን ለአይን ከተገጣጠምክ ፊቷን ካዞረች በኋላ ያላትንም
እንቅስቃሴዎች አስተውል፡፡ አይናች በመጋጨቱ አፍረት ወይም መጨናነቅ ነገር
ከታየበት ተመችተሃታል ወይም ወዳሃለች ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ፀጉሯን
እንደማፍተልተል፣ ልብሷን ወይም ጌጣጌጧን ማስተካከል ወይም ደግሞ እጇ ላይ
ባለው ነገር መጫወት ከጀመረች እነዚህ ግልፅ የሆኑ ማረጋገጫዎችህ ናቸው፡፡
- ውስጥ እጇን አንብብላት፡- በአጋጣሚዎች እና አንድ ላይ በምትሆኑባቸው
ሁኔታዎች ውስጥ እጇን ብትመለከት እሷም አሳልፋ ውስጥ እጇንና የእጇን አንጓ
እንድትነካ ከፈቀደችልህ ሌላው ያንተ እሷን የመመቸት የአዕምሮ ፍቃድ ማሳያ
አንዱ መንገድ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ ‹‹ከፈለከኝ ያንተው ነኝ›› እንደማለት ነው፡፡
- ማጎንበስ፡- በምታጎነብስበት ጊዜ ትከሻዋን ወደ አንተ በመስበቅ ካጎነበሰች
ዕድል በእጅህ ገብታለች ማለት ነው፡፡
- እግሮቿን ከፍታ በምትቀመጥባቸው አጋጣሚዎች ካሉ አንተ ጋር በመሆኗ ምቾት
ተሰምቷታል ማለት ነው፡፡
- አንድ ሴት አንድን ሰው በምታይበት ጊዜ የአይን ብሌኗ ከሰፋ ያንን ሰው
እንደምትወደው በተቃራኒው ደግሞ የአይን ብሌኗን ካጠበበች ለዛ ሰው ጥሩ
ስሜት እንደሌላት አንድ መገለጫ ነው፡፡ አይን ለአይን በምትጋጩበት ጊዜ
ፈገግታን ከቸረችህ ወደ እሷ ሂድና አነጋግራት፡፡ ሌላው እንደ መልካም ነገር
መገለጫ የሚወሰደው አንተ በምታወራበት ጊዜ ለረባ ባልረባው ፈገግ የምትል
ወይም ሳቅ የምታበዛ ከሆነ በእርግጠኝነት በደንብ ተመችተሃታል ይሄ ደግሞ
የበለጠ የተሻለ ነው፡፡

ይቀጥላል.....
Pages: 1