ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 1 guest | 2 bots
Pages: 1
Posted on 03-25-19, 08:00 pm
Administrator

Karma: 100
Posts: 145/163
Since: 02-10-19

Last post: 449 days
Last view: 399 days
ሴትን የማማለል ጥበብ ክፍል 6

.....ግራ ግብት ብሎኝ ተገትሬ ቀረሁ...ባል እንዴት ይሸኛል? ደህና ሁን ወይስ መልካም እድል ተብሎ? ይጨበጣል: ይታቀፋል ወይስ ይሳማል? ወዳጅ ነው ጠላት? ውስጤ ከሚተራመሰው ሙግት ባሌ ተመለሰና ገላገለኝ::
የደም ስሮቹ ግንባሩ ላይ ተግተርትረዋል...ስንብቱ ለሱም ቀላል አልሆነም:: እንዴት ይሆናል? በዚች አለም ላይ አለኝ የሚለውን ነገር ሁሉ ተሰናብቶ: ቁልፉን አስረክቦ ለመጨረሻ ጊዜ በሩን አቁዋርጦ ሊወጣ ነው::

"በ-ቃ...መ-ሄ-ዴ...ነ-ው" አለ በተሰባበረ ድምፅ: አንጀቴ ተላወሰ: ቅር ልለው ግን በፍፁም አልፈለኩም: ኧረ በጭራሽ:: ኩራቴ የት ሄዶ: ሌላ ሴት ጋ ለመሄድ የተነሳን ወንድ ከምለምን ሞቴን እመርጣለሁ: አዎን ለምወዳቸው ልጆቼ ስል እንኩዋን የማላደርገው አንድ ነገር::

"ም-ን...እ-ን-ደ-ም-ል-ህ...አ-ላ-ው-ቅ-ም....መ-ል-ካ-ም...እ-ድ-ል?
ያባራው እንባዬ መዥጎድጎድ ሲጀምር እሱም ግራ ተጋብቶ ቆመ::

"እ-ና-ት-ዬ...ይ-ቅ-ር-ታ" ምንም አልመለስኩለትም:: እያመነታ ወደበሩ ተራመደና ሻንጣዎቹን እያነሳ ዞር ብሎ አየኝ: ከቆምኩበት አልተነቃነቅሁም:: "በ-ሩ-ን...ቆ-ል-ፊ-ው"

ሲቃ እየተናነቀኝ ወደበሩ ሄድኩ: አንድም ቃል አልተናገርኩም... ምን ልናገር እችላለሁ? ስልኩ የወደቀበት እንዲታየው የውጪውን መብራት አበራሁለትና በሩን ዘጋሁት: ቆለፍኩት: ተደግፌው ወደመሬት ተንሸራተትኩና ጮኬ አለቀስኩ: ለትዳሬ: ለራሴ: ለባሌ: ለልጆቼ...አዎን ለልጆቼ ተንሰቅስቄ አለቀስኩ:: ለምን ያህል ጊዜ እንደቆየሁ አላውቅም: እዛው በሩ ስር እንደተቀመጥኩት ቤቴን መቃኘት ጀመርኩ: ግድግዳው ላይ የተሰቀሉት ፎቶዎቻችን ላይ አፈጠጥኩ: ከዛም አይኔ እዛ ወረቀት ላይ አረፈ::

ተነስቼ ወደጠረጴዛው አመራሁና አገላበጥኩት: እንደተነጋገርነው የባንኩን ድርድር ለውጦታል:: ግን ያ ድርድር አሁን ፋይዳ የለውም: አሁን ባለሙሉ መብትዋ እኔ ነኝ:: ግን ደግሞ መልሼ አሰብኩ: እንኩዋን ብር እሱም ሄዷል:: ብእር ከቦርሳዬ አወጣሁና እያንዳንዱ ገፅ ላይ ፊርማዬን አኖርኩ::
በአንድ ፊርማ የገባሁበትን ትዳር በአምስት ፊርማ ተሰናበትኩት:: የመጨረሻው ፊርማዬ ላይ ማህተም ይመስል እንባዬ ተንጠባጠበበት::

ልጆቼን ቃኘሁና በራቸውን ክፍት ትቼ ወደራሴው መኝታ ቤት ገባሁ:: ቅድም ለግብዣው እየለካሁ ያሽቀነጠርኩዋቸው ልብሶች አልጋው ላይ ተከምረዋል:: በቁሜ ዘፍ ብዬ በጀርባዬ ተዘረጋሁባቸውና ጣራው ላይ አፈጠጥኩ:: ቅድም ልብሶቼን ስለካ የነበረኝ ህይወቴና የአሁኑ ህይወቴ አራምባ ቆቦነት አስገርሞኝ "ተ-ፈ-ፀ-መ" ብዬ አንሾካሸኩ:: ከቃሉ ጋር የሆነ እንግዳ ስሜት ተናነቀኝ:: "በ-ቃ...ተ-ፈ-ፀ-መ" አልኩኝ ደገምኩና ከፍ ባለ ድምፅ:: የሚተናነቀኝ ስሜት ፈንቅሎኝ ሊወጣ ታገለኝ::

"ማበዴ ነው እንዴ?" እራሴን ጠየኩ....በዚች ቀውጢ ሰአት እንዲህ አይነት ስሜት...አፌን አፍኜ ያዝኩት:: ግን አልቻልኩትም...አሸነፈኝ...አልጋዬ ላይ እንደተዘረርኩ ለቀቅሁት:: "ቂቂቂቂቂቂ.....ካካካካካካካካ" ሳቄ ቤቱን አናጋው
Pages: 1