ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 1 guest | 4 bots
Pages: 1
Posted on 03-24-19, 08:46 am
Administrator

Karma: 100
Posts: 142/163
Since: 02-10-19

Last post: 449 days
Last view: 399 days
ሴትን የማማለል ጥበብ ክፍል 4

"ተግባባን ወይይይ?" አልኩ በድጋሚ ድምፄን ከፍ አድርጌና አጎንብሼ ፊቴን ወደሱ ፊት በጣም እያስጠጋሁ:: ብዙም አተኩሮ ሊያየኝ አልቻለም: ወንበሩን ወደሁዋላው አንሸራትቶ ራቀኝ::

"ተናገር እንጂ" "አይ አንቺ...ልብሽን እኮ አውቀዋለሁ:: እንኩዋን ሰው...." ፈገግ ለማለት ሞከረ:: "አሂሂሂሂ..." እኔም የብሽቀት ሳቄን ብልጭ አደረኩ::

"ልቤንማ አውቀኸው ነው የምትጨማለቅብኝ...አሁን ግን እስኪ ወንድነትህን ልለካው...እስቲ አንድ ልጅ ከኔ ለመንጠቅ ሞክር...በላ ሞክረኝ" የተናገርኩትን ለማስረገጥ በሌባ ጣቴ ጠረጴዛውን እየደጋገምኩ ተመተምኩት:: "ይገባኛል...በንዴት ብዙ ነገር ልትይ ትችያለሽ...እኔ ግን ለልጆቹም ቢሆን የሚሻለው....." አቁዋረጥኩት::
"ኖ-ኖ-ኖ-ኖ...ወዴት ወዴት...አንተን ብሎ ለልጆቹ አሳቢ:: እንደልብህ ለመንዘላዘል እንዲመችህ ነው እንጂ...አሁን የተባልከው ወንድ ከሆንክ አንዳቸውን ለመውሰድ ሞክር እስኪ ነው" ድንፋታዬን ቀጠልኩ...የሚጋልበኝን እንግዳ ስሜት ወደድኩት...እልህ: በቀል: አልጠቃም ባይነት... ምንም ሳይመልስልኝ ተፋጥጠን ቆየንና "እሺ ልክ ነሽ...ማንኛቸውንም አልወስድም" ከት ብዬ በንቀት ሳቅሁበት::
"በሞከርከኝ ኖሮ...አንተ ሽንታም!" ወንበሬ ላይ በኩራት ተመቻችቼ ተቀመጥኩ...አዎን ድል መታሁ:: እኔ እሱ ላይ: እሱ ወረቀቱ ላይ አፍጥጠን በዝምታ ተቀመጥን:: እንደዛ እወደው: ከመውደድም አልፌ አመልከው የነበረውን ሰው ለአይኔ ተፀየፍኩት:: "ጥዝ...ጥዝ...ጥዝ" የሚል ድምፅ በጣም በስሱ የወረሰንን ፀጥታ አቁዋርጦ ተሰማኝ...የአንዳችን የእጅ ስልክ መሆን አለበት...ግን ደግሞ የኔን ስልክ ድምፁን አላጠፋሁትም::
በአይኔ ፈለኩ...የማንኛችንም ስልክ በአካባቢው የለም:: የባሌ እጅ ግን በድንገት ሲንቀሳቀስ አየሁትና ወዲያው ድምፁ ፀጥ አለ::
ጠረጴዛው ቢከልለኝም እጁ ወንበሩ
መደገፊያ ላይ ወደተሰቀለው ጃኬት ኪስ እንደገባ ገምቻለሁ:: ቶሎ አይኔን ከባሌ ላይ አንስቼ ከጀርባው ያለው ግድግዳ ላይ አፈጠጥኩ...አላየሁም: አልሰማሁም ለማለት አይነት::
ወዲያው ባሌ ተነሳ:: ያን የፍቺ ወረቀት ወደእኔ እየገፋ "ተረጋግተሽ አንብቢውና ይስተካከሉ የምትያቸውን ነገሮች ነገ አስተካክያቸው ሁለታችንም እንፈርምበታለን" አለ እያመነታ:: የኔ ልብ ግን እዛ ስልክ ላይ ተንገዋሎ ቀርቷል...አሁን እንዳይሄድ መያዝ አለብኝ::
"አስተካክያቸው? ማን: አንተ?" አልኩ በለሰለሰ ድምፅ...ያ ሁሉ ማጉዋራት በፍጥነት ሲቀየር ገርሞት አፈጠጠብኝ:: "እእእ...አ-ዎ-ን...ጠበቃዬ ለማስተካከል እንዲመቸን ብሎ ኢሜይል አድርጎልኛል" "ባንክ ያለንን ገንዘብ ግማሽ እስከተካፈልን ድረስ በሌላው ሁሉ እስማማለሁ...ልጆቼን እንደሁ ሰጥተኸኛል" ቀጠልኩ በዛው በለሰለሰ ድምፅ "ቅድም ስለጮህኩብህ ይቅርታ...የልጆቼን ነገር ታውቀዋለህ" የባሰውን ግራ ተጋባ::
ከደቂቃት በፊት ልገለው ስዝት የነበርኩ ሴትዮ ከመቅፅበት ወደ ይቅርታ ጥየቃ ስገባ ጆሮውን አላመነም...ግን ደግሞ ወንድ አይደል...ሰተት ብሎ ወደወጥመዴ ገባልኝ:: "እና-ና-ና.....አሁኑኑ ላስተካክለው?" አለ ፈራ ተባ እያለ:: "አዎን...የባንኩን ብቻ አስተካክለው...ታዲያ ለኔም ቀሪ ኮፒ ስለምፈልግ እባክህ ፕሪንት አድርግልኝ" ጨዋነትና ትህትና የተሞላበት መልሴን ሰጠሁ "እስከዛ ልጆቼን አይቼ ልምጣ" ብዬ ወደመኝታ ቤታቸው አመራሁ...እሱም ኮምፒውተሩ ወዳለበት ክፍል ተጣደፈ::

ይቀጥላል........
Pages: 1