ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 1 guest | 3 bots
Pages: 1
Posted on 03-24-19, 04:13 am
Administrator

Karma: 100
Posts: 140/163
Since: 02-10-19

Last post: 449 days
Last view: 399 days
ሴትን የማማለል ጥበብ ክፍል 2

ባሌ የምግብ ጠረጴዛው ላይ የተቀመጠ ወረቀት ተመስጦ ያገላብጣል:: አይኖቼ ዋናው በር አጠገብ የተቀመጡት ሁለት ሻንጣዎች ላይ አረፉ...ብዙም አልተገረምኩም:: ላለፉት ሶስት አራት ወራት እኛ ካለንበት ከተማ ወደ 150 ኪሎ ሜትር ገደማ የሚርቅ አገር ለስራ ቢያንስ በየሁለት ሳምንቱ እየተላከ መስራት ጀምሯል:: ከእኛ ጋር የሚያሳልፈው አንድም የእረፍት ቀን ስለሌለው መጀመሪያ ላይ በጣም እነጫነጭ ነበር...ሁዋላ ግን ጭራሽ ለመድኩትና እንደውም ከኩርፊያውም: ከንትርኩም: ከመገፋፋቱም እንደእረፍት እየወሰድኩት ደስ ደስ ይለኝ ጀምሯል::

ዛሬ ግን እንደወትሮው ልብሱን እንዳዘጋጅለትም ሆነ የሚወደውን የሀበሻ ምግብ እንድሰንቅለት ቀድሞ አልነገረኝም:: ደግሞስ ሁለት ትልልቅ ሻንጣ ምን ያደርግለታል? "ቁጭ በያ!" አለ ፊት ለፊቱ ያለውን ወንበር እያመለከተኝ::
"ምንድነው ሻንጣው?" አልኩ ፊቴን ከስክሼ...ከቆምኩበት ሳልነቃነቅ:: አደን ላይ እንደተገናኙ አውሬዎች ተፋጠጥን:: "መጀመሪያ ቁጭ በይና በጥሞና እንነጋገር" አለኝ በመለማመጥ ድምፅ:: ውስጤን የማላውቀው ስሜት ሲነዝረኝ ተሰማኝ...ቁጣ አልለው ንዴት: ሽብር አልለው ፍርሀት...ብቻ ድብልቅልቅ ያለ::

ወንበሩን ሳብኩና ጫፉ ላይ ተንጠላጥዬ ተቀመጥኩ...በድንገት ለመሮጥ የተዘጋጀሁ ይመስል:: "እናት..." አለ ንግግሩን ሲጀምር:: እናት ብሎ ከጠራኝ ኧረ በሙሉ ስሜ እንኩዋን ከጠራኝ ወራት አልፈዋል...ሽብር አናወዘኝ:: "እናት...ጥሩ ሰው ነሽ: ደግ ልብ አለሽ:: ለልጆችሽ ሙዋች ነሽ...በራሴው ልጆች አንቺን የመሰለ እናት ስላደላቸው እ-ቀ-ና-ባ-ቸ-ዋ-ለ-ሁ" አለና ጉሮሮውን ሲቃ ሲተናነቀው የኔ እንባ ቀድሞ መዥጎድጎድ ጀመረ...ገባኝ: በጣም ገባኝ...አንድም ቃል አልተነፈስኩም::
ንግግሩን ቀጠለ:: "እኔ ላንቺ የምገባ ሰው አይደለሁም..." አቁዋረጥኩት "ምን ማለት ነው?" አንባረቅሁበት "ዲስኩርህን አቁምና በቀጥታ ለማለት የፈለከውን ተ-ና-ገ-ር" እንባ ተናነቀኝ:: "ይኸውልሽ...ዋነኛው ችግርሽ መደማመጥ የሚባል ነገር አታውቂም..." አለና በብሽቀት ሲያገላብጥ የነበረውን ወረቀት ወደኔ አሽቀነጠረው::

የመጀመሪያው ገፅ ላይ የተፃፉት የህግ ቃላት ብዙም አልገቡኝም:: የሱ ስም ከላይ: የኔ ስም ከታች...እንደካሳሽና ተከሳሽ አይነት ነገር...ከስሩ ደግሞ የልጆቻችን ስም እና የተወለዱበት ቀን...ከዛ ደግሞ የቤታችን አድራሻ...ቀጥሎ የመኪኖቻችን አይነትና የተሰሩበት አመተምህረት...ባንካችን ውስጥ ያለው ገንዘብ መጠን...ያለብን እዳ...ግራ በተጋባ መንፈስ ባሌን ቀና ብዬ አየሁት: እሱም አፍጥጦ እየጠበቀኝ ነበርና አይን ለአይን ተገጣጠምን:: "ምንድነው ይሄ?" ብዬ አንሾካሸኩ...ጥያቄው ለሱ ይሁን ለኔ አላውቅም...እሱም አልመለሰልኝም::

ሁለተኛው ገፅ 1ኛ 2ኛ እያለ ንብረት ያከፋፍል ጀመር:: ሰበብ የማይሻው እንባዬ እንደጉድ እየተዥጎደጎደ ደረቴን አራሰው...አይኖቼን እየጨመቅሁ ማንበቤን ቀጠልኩ...ይህ የልጆቼ ህይወት ወሳኝ ጉዳይ ነው: የራሴም ህይወት ጉዳይ ነው: የማልቀሻና የመቅለስለሻ ጊዜ አይደለም...እንባዬ ግን አሻፈረኝ አለ::
ማንበቤን አላቁዋረጥኩም....ቀናም ብዬ ወደባሌ አላየሁም...ቤቱ: መኪኖቹ: የሱ ደሞዝ: የባንክ ገንዘባችን እንደቅርጫ ስጋ ተሸንሽኖዋል...ያልጣመኝ ነገር አለ: ግን አሁን ዋናው ጉዳዬ እሱ አይደለም...ማነብነቤን ቀጠልኩ...ሶስተኛ: አራተኛ: አምስተኛ ገፅ...የልጆቼን ስም ሳይ ልቤ ቀጥ አለች...አዎን ሁሉም ገደል ይግባ: አባታቸውን ጨምሮ ...ግን...ግን...ከልጆቼ ከአንዳቸውም ከተነጠልኩ ሁሉም ነገር አለቀ...እሱም እኔም እናውቀዋለን::

የቻልኩትን ያህል አየር ስቤ ማንበቤን ቀጠልኩ...ሲተናነቀኝ የነበረውን ሲቃ በጭራሽ ልቆጣጠረው አልቻልኩም...ሰውነቴን እያንዘፈዘፈ ፈነቀለኝ...አዎን...መርዶ የተረዳሁ ይመስል ጮኬ ማልቀስ ጀመርኩ...ለነገሩ ይህ ሁሉ ዱብ እዳ መርዶም አይደል::

ይቀጥላል
Pages: 1