ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 03-22-19, 03:21 am
Administrator

Karma: 100
Posts: 134/163
Since: 02-10-19

Last post: 243 days
Last view: 193 days
እንደማፈቅራት ምን ብዬ ልንገራት ክፍል 4

አልጋ ልብስ
-----------
አልጋ ልብሱ ደማቅ አረንጓዴ ነበር፡፡ እዚያች ክፍል ውስጥ የደረሰብኝን ስቃይ የምናውቀው እኔ፤ ሶስት ወንዶች እና ያ አረንጓዴ አልጋ ልብስ ነን፡፡ ያ አረንጓዴ አልጋ ልብስ በደሜ ተጨማልቋል፡፡
ያ አረንጓዴ አልጋ ልብስ በሶስት ወንዶች የዘር ፍሬ ላብ ረጥቧል፡ ፡ ያ አረንጓዴ አልጋ ልብስ በእንባዬ ርሷል። እነዚያን አውሬዎች ብከሳቸው ኖሮ አንደኛ ምስክር አድርጌ የምጠራው ያንን ባለውለታዬን አረንጓዴ አልጋ ልብስ ነበር፡፡

በመደፈሩ መካከል ወይም አንዱ ደፋሪዬ ወጥቶ ሌላው እስኪተካ ድረስ ሰውነቴን እሸፍንበት ነበር፡፡ አለም በጨከነብኝ ጊዜ እርቃኔን ሸፍኜበታለሁ፡፡ መደፈሬን ለማንም አልተናገርኩም፡፡
እንዲህ አይነት ነገር ለማን ይወራል? ያን ቀን ተደብቄ ነበር እዚያ ፓርቲ ላይ የተገኘሁት፡፡ አድሬና አምሽቼ ስመጣ እናቴ በጣም ተቆጣችኝ፡፡

እያነከስኩ መምጣቴ እንዳይታወቅብኝ ተጠንቅቄ ወደ መኝታ ቤቴ ገብቼ ተኛሁ፡፡
ለሳምንት ያህል ሽንት ቤትመጠቀምና ሽንቴን መሽናት ለኔ ስቃይ ነበር፡፡ ለእናቴ አልነገርኳትም፡፡ የቤቱ ብቸኛ ልጅ ስለሆንኩ ሌላ የምነግረው ሰው አልነበረም፡፡ ለትምህርት ቤት ሴት ጓደኞቼ እንዲህ ሆንኩ ብዬ መናገሩ ደግሞ የድንጋይ ያህል ከበደኝ፡፡
ለመደፈሬ እራሴንም ጥፋተኛ አደርጋለሁ፡፡ እዚያ ፓርቲ መሄድ አልነበረብኝም፡፡ የሰጡኝንም መጠጥ መጠጣት አልነበረብኝም፡፡
Pages: 1