ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Military. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 03-21-19, 06:25 pm


Karma: 100
Posts: 751/769
Since: 03-20-17

Last post: 344 days
Last view: 344 days
አዲሱ የኢትዮጵያ የአየር መቃወሚያ ሚሳኤል!ራሽያዎች Pantsir-S1 ብለው የሰየሙት የአየር መቃወሚያ ሚሳኤል በቅርቡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ትርኢት ሲያሳይ መታየቱ ትኩረት ስቧል። የጦር መሳርያ አዋቂዎች እንደሚሉት ይህ ሚሳኤል የተገጠመው S-125 (SA-3) በተባለ ማስወንጨፊያ ላይ ነው። መሳርያው አውቶማቲክ ፀረ- አውሮፕላን መተኮሻ የተገጠመለት ሲሆን ከምድር ወደ አየር ተወንጫፊ እንደሆነ Defense Web ዘግቧል።

Pantsir- S1 በአንድ ደቂቃ ውስጥ 12 ኢላማዎችን ማጥቃት የሚችል ሲሆን እስከ 20 ኪሜ መምዘግዘግ እንደሚችል ተገልፁዋል።

አፍሪካ ውስጥ መሳርያው ያላት ሌላ ሀገር ኢኳቶሪያል ጊኒ ነች።

ነገር ግን መሣሪያው መቼ እንደተገዛ፣ ምን ያህል ብዛት እንዳለ እንዲሁም ወጪው ምን ያህል እንደሆነ አልተገለፀም።

የራሺያው S-400 እና የአሜሪካው THAAD የአየር መቃወሚያ መሳርያዎች በአለም ላይ እጅግ ዘመናዊዎቹ ሲሆኑ ዋጋቸውም በብዙ መቶ ሚልዮን ዶላር ይገመታል ተብሎ ይታሰባል።

P.S: ያው ሀገራት የጦር መሳርያዎቻቸውን በይፋ የሚያሳዩት (ይህ መሳርያ በETV እንደታየው) አቅማቸውን ለማሳየት (to project power) ነው ይባላል። ስለዚህ ይህን ፅሁፍ ተከትሎ የሀገር ሚስጥር ነው ምናምን የሚል ሀሳብ ካለ ይቅር።
Pages: 1