ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Surprising Things ገራሚ ነገሮች . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 03-20-19, 05:59 am
Administrator

Karma: 100
Posts: 127/163
Since: 02-10-19

Last post: 10 days
Last view: 9 days

ለመሆኑ ብዙ ተስፋ የተጣለባት ብላክ ቦክስ ምንድን ናት?
*************************************************************
ከሰሞኑ የብዙዎችን ልብ ከሰበረው አውሮፕላን አደጋ በኋላ በኢትዮጵያም ይሁን በመላው ዓለም የሚገኙ የተጎጂ ቤተሶቦች እና መላው ህዝብ አደጋው የተፈጠረበትን ትክክለኛ ምክንያት ለማውቅ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ በተለይም ደግሞ አደጋው ከተከሰተ ጥቂት ቀናት በኋላ በብዙ ፍለጋ የተገኘቸው ብላክ ቦክስ ወደ ፈረንሳይ ተልካ በአደጋው ወቅት የነበረውን አጠቃላይ ሁነት ለማሳየት የሚያስችሉ መረጃዎችን ልትሰጥ በምትችልበት ሁኔታ ላይ ናት የሚል መረጃ ከወጣ ጀምሮ የሁሉም ዓይን በመረጃ ሳጥኗ ላይ ያነጣጠረ ሆኗል፡፡ የትኛውንም አደጋ መቋቋም የሚያስችል አቅም አላት የምትባለው ይህች ብላክ ቦክስ አጠቃላይ መረጃዋ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ስለቴክኖሎጂዋ አፈጣጠር
እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1934 የዶክተር ዴቪድ ዋረን አባት በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸው ሲያልፍ ዴቪድ ገና የዘጠኝ አመት ልጅ ነበር፡፡ አባቱን ይዞ እንደወጣ ያልተመለሰው አውሮፕላን የተከሰከሰበት ምክንያት እንኳን ሳይታወቅ የዴቪድን ልብ እንደሰበረ ቀረ፡፡ ይህ ሁነት ሁሌም ቁጭት የሚፈጠጥርበት ዴቪድ በ1950 በበረራ ወቅት መረጃዎችን የምትመዘግብና የድምፅ ምልልሶችን የምትቀዳ መሳሪያ ለመፍጠር መነሻ ሆነው፡፡ የአዎስትራሊያ ዜጋ የሆነው ዴቪድ የዚችን መሳሪያ ፕሮቶታይፕ በ1956 ሲሰራ በመጀመሪያ "ARL Flight Memory Unit" የሚል መጠሪያ የሰጣት ቢሆንም ከአምስት አመት በኋላ በአሜሪካ እና እንግሊዝ አማካኝነት ወደ ሙሉ ምርት እንድትገባና እና አሁን የያዘችውን ስያሜም እንድታገኝ ሆኗል፡፡

የብላክ ቦክስ ገፅታ
የመረጃ ሳጥን ወይም ብላክ ቦክስ ሁለት አይነት ገፅታ ሲኖራት እነሱም flight data recorder (FDR) እና cockpit voice recorder (CVR) ይሰኛሉ፡፡ FDR የሚባለው በቋሚነት በየቦታው በተገጠሙለት ሴንሰሮች አማካኘነት ከኤሌክትሪክ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን እያንዳንዳቸውን ነገሮች ለምሳሌ የሞተር ኃይል እና ፍጥነትን ሲመዘግብ፤ CVR የተባለው ደግሞ በበረራው ወቅት የተሰሙ የፓይለቶችን እና የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ አካላትን አጠቃላይ ግንኙነቶችን የሚመዘግብ ነው፡፡ ብላክ ቦከስ ብዙዎች እንደሚያስቡት ጥቁር ቀለም ያላት ሳጥን ሳትሆን በአለም አቀፉ የኤሮስፔስ የቀለም አጠቃቀም መሰረት ከተፈጥሮአዊ ገፅታዎች ለመለየት የብርቱካናማ ቀለም እንዲኖራት ተደርጓል፡፡

የብላክ ቦክስ መሳሪያ ይዘት
የብላክ ቦክስ መሳሪያ አብዛኛውን ጊዜ በቲታንየም ወይም በማይዝግ ብረት የሚሸፈን ሲሆን 227 ኪ.ግ ክብደትም ይመዝናል፡፡ የትኛውንም አደጋ መቋቋም ይችላል የሚባለው የብላክ ቦክስ መሳሪያ ለአንድ ሰዓት የሚቆይ የ100 ዲግሪ ሴሊሺየስ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ መቋቋም ከመቻሉም በላይ ከፍተኛ እርጥበት እና በግፊት የተሞላ ጨዋማ ውሃ ውስጥ ሆኖ እንኳን የያዘውን መረጃ ሳያጣ ለ2 ዓመት መቆየት ይችላል።

መረጃ የማከማቸት አቅም
ብላክ ቦክስ በቀላሉ የማይጎዳ ከመሆኑም ባለፈ 3400 Gs የመረጃ ቋትም አለው። ይህም ማለት ከአዲስ አበባ ሳኦ ፖሎ ብራዚል የሚበር አውሮፕላን፤ ደርሶ አስኪመለስ ያለውን አጠቃላይ መረጃ ማለትም የአብራሪውን እንቅስቃሴ፣ የአውሮፕላኑን ፍጥነት፣ ከፍታውን፣ የነዳጅ ሁኔታ እና ሌሎች አንቅስቃሴዎቹን ይመዘግብለታል ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ CVR የተባለው የብላክ ቦክስ ገፅታ ለ25 ሰዓታት የሚቆይ የበረራ መረጃን ለማከማቸት ዲጂታል መቅጃዎችን የሚጠቀም ቢሆንም በራሱ ለመቅዳት ሲፈልግ ግን የሁለት ሰዓት የበረራ መረጃን ብቻ ይይዛል፡፡
Pages: 1