ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 1 guest | 2 bots
Pages: 1
Posted on 03-18-19, 05:19 am
Administrator

Karma: 100
Posts: 121/163
Since: 02-10-19

Last post: 446 days
Last view: 396 days
ወንዶች የሚማርካችቸው ምንድነው ክፍል 28

ወርደው ወደ ህንፃው ገቡ በፎቶ ያየችውን ሰው በጭንቅላቷ መዝግባ ምስሉን እያመላለሰች የስራ አስኪያጁ ቢሮ ጋር ስትደርስ እጇ እግሯ ሁሉ በላብ ተጠመቀ ‹‹ሚሊ ደና ነሽ›› ሳሮን ተጨንቃለች ‹‹ወይም እዩኤልን ልጥራው›› ‹‹አይ ሳሪ አስፈላጊ አይደለም እኔ እራሴ እወጣዋለው›› ቢሮውን አንኳኳች ‹‹ይግቡ›› የሴት ድምፅ ‹‹አቶ ሰለሞንን ማግኘት ፈልጌ ነበር›› እንድትገባ ተፈቅዶላት ስትገባ የሚስደነግጥ ውበት ያለው እጅግ ሰፊቢሮ ወስጥ በጣም ግርማ ሞገስ ያለው ጎልማሳ ቀይ መልከመልካም የተረጋጋ ሰው ወንበሩ ላይ ተቀምጧል በትህትና ‹‹ተቀመጪ እባክሽ›› አላት ኩር አድርጋ ስታየው እሱም በደንብ ተመለከታት ‹‹ከዚ በፊት ተገናኝተናል ልበል ››አላት በጥርጣሬ ነው የሚመለከታት በአሉታ አንገቷን ወዘወዘች ‹‹ተገናኝተን አናውቅም አደይ ናት አንተ ጋር የላከችኝ ›› አለችው ፊቱ በሰከንዶች ልዩነት ለውጥ አመጣ ሲቀላ ይታያል‹‹አደይ አደይ የቷ! ›› አይኖቹን ግን ከሷ ላይ መንቀል አልቻለም ‹‹አደይ ፍቅረኛህ የነበረችው ፣አደይ የእናንተ ቤት ሰራተኛ የነበረች …››ፊቱ በድንጋጤ እየገረጣ ከተቀመጠበት በቀስታ ተነሳ እና ‹‹አሁን የት ናት? በሂወት አለች? አንቺ ምኗ ነሽ ቁርጥ እሷን ነው የምትመስይው ›› እየተጠጋት መጣ ‹‹አንተንስ አልመስልም ›› ባለበት ቆመ እያወቁ እንዳለወቁ እያስመሰሉ እንደመኖር ደግሞ የሚያም ነገር የለም ‹‹ልጇ ነኝ ወልዳ ለብቻዋ ያሳደገችኝ ልጇ ልጅ እንዳለህ እንድታውቅ ያህል ነው እኔ ካንተ ምንም አልፈልግም ለማንኛውም ሚሊያርድ እባላለው አባዬ ›› ብላ እጇን ስትዘረጋለት ሳብ አድርጎ አቀፋት እና ‹‹እናትሽን ለአመታት ስፈልጋት ነበር ማርገዟን ፈፅሞ አላውቅም ነበር በመጨረሻ ቤተሰቦቼ በግድ አጋቡኝ እስካሁን እናትሽ በልቤ ውስጥ ናት ለደቂቃዎች ካወሩ በኋላ ስትወጣ ድንደ ፀሀይ ደምቃ እየተፍለቀለቀች በደስታ እየዘለለች ነበር ሳሮንን ልክ ስታገኛት ‹‹አባቴን አገኘውት ሳሪ››ብላ እያለቀሰች ስታቅፋት ከኋላዋ ነበር እሱም እንደ ጨዋ ሳሮንን ሰላም ካለት በኋላ በሙሉ መስሪያቤቱ እያዞረ ለሁሉም ሰራቶቹ ‹‹የበኩር ልጄ እቺ ናት›› እያለ አስተዋወቃት አብረው ምሳ በሉ ከእህት ወንድሞቿ ጋር እሁድ ለመተዋወቅ ቀጠሮ ይዘው ተለያዩ፡፡

የእራስን ነገር መጠበቅ እና መንከባከብ የባለቤቱ ሀላፊነት ነው የእራስህን ነገር መጠበቅ ካልቻልክ እና ከጣልከው ሌላ ያነሳዋል ፈጣሪ ስለፈጠራቸው ብቻ የሚያኖራቸው እጅግ ብዙ በርካታ ሰዎች ወይም ፍጥረታት እንዳሉ አውቃለው እናም ከልጅነት የነበረ እና አርፍዶ የመጣ በልብ እኩል ይዳኛል ብሎ ማሰብ ይከብደኛል ምንም ምክንያት ይኑረው ፍቅርስ ይህንን አመዛዝኖ ለመዳኘት እና ለማፍቀር ይቻለዋል? እቴት ዘመኗን ሙሉ ለልጇ ሰው ቤት የኖረች ከልጇ ጋር ሁሉን የተጋራች ሴት ናት መከልከል የተፈጠረው የሰው ልጅ በቃኝን እንዲያውቅ ምኞት ደግሞ ሰው ብዙ እንዲያልም እና ነገን እየናፈቀ እንዲኖር ያለበቃኝ እንዲያልም በህልሙ ውስጥ እንዲኖር ለዚህች አለም እሱ ከሚያስፈልገው በላይ እንዲሰራ ይመስላል ደስ የሚል ንፁህ አየር ይነፍሳል እቤት ስትደርስ ለእቴት እና ለፍላጎት ከአባቷ ጋር ያሳለፈችውን ሁሉ እንዴት እንደምትነግራቸው እያሰበች ለብቻዋ ትስቃለች እዩኤል ይሄንን ሲሰማ እንዴት ንግዲ እንደሚደሰት እያሰበች ልቧ በደስታ ዝልል ዝልል ትላለች እዩኤል ደወለ ‹‹ሚሊ የት ናችሁ አንቺና ሳሮን አልተቻላችሁም›› ከድምፁ ፍልቅልቅ እያለ ነው ‹‹እዩ አባቴን እኮ አገኘውት ›› ድምፅዋ በደስታ ይርገበገባል ‹‹ምን ኸረ ሀይቅ ጋር ነን ቶሎ ኑ በናታችሁ በቃ አፍጥኑት ›› ስልኩን እንደዘጋቸው አዙረው ወደ ሀይቅ በረሩ ልክ ስትደርስ እቅፉ ውስጥ ገባች ለዘልአለም እንደዚ መሆን ፈለገች ፀሀይ እያዘቀዘቀች ነው ሀይቁ ላይ ስታርፍ የሚገርም እይታን ፈጠረ ከአድማስ ማዶ ጀንበር ደና ሁኑ ስትል ነገ አዲስ ቀን ልሙጥ ወረቀት ሁሉም ሰው የየራሱን ታሪክ የሚፅፍበት ቀን ሆነ በአዲስ ቀን ሁላችንም የየራሳችን ታሪክ እንፃፍ፡፡
።።።።።።።
።።።ተፈፀመ።።።
Pages: 1