ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 03-16-19, 04:40 am
Administrator

Karma: 100
Posts: 113/163
Since: 02-10-19

Last post: 446 days
Last view: 396 days
ወንዶች የሚማርካችቸው ምንድነው ክፍል 20


እዩኤል እናቱ ውሃ ደፍታበት ከነቃ በኋላ በፍጥነት ከተኛበት ተነስቶ በእሩጫ ከቤቱ ሲወጣ እናትየው በድንጋጤ ባዶ እግሯን ተከትላው መሮጥ ጀመረች በፍጥነት ስለሆነ የሚሮጠው ብትጮህም ልትደርስበት አልቻለችም እዩኤል ለምን እንኳን እንዲህ እየሮጠ ወደ እሷ ጋር መሄድ እንደፈለገ አያውቀውም ተፈጥሮ እና ሰው ከጎዳት በላይ እሱ የጎዳት ገዝፎ ስለተሰማው ይቅርታ ሊጠይቃት?ወይስ በሌላ ሰው መደፈር እና መሰቃየትዋ ያውም አርግዛ ማሶረዷን ሁሉም ሲያውቅ እና ሲያንቋሽሻት ሲሰማ እረክሳበት የእውነትም መርከሷን ሊነግራት ከእሷ ጋር የጀመረው መንገድ የትም እንደማያደርሰው አሁን ስለተረዳው ትቼዋለው አንቺ ማለት እንደዚ ነሽ ብሎ ሊነግራት? ነው ፀፀቱ መድረሻ አሳጥቶት ቀድሞ ማስታወሻዋን መውሰዱን ባለመናገሩ እና ለእሷ ሚስጥር ባለመጠንቀቁ ከእንደሱ ያለ ዋልጌ እጅ በቸልተኛነት ወጥቶ የት እንደደረሰ ሲያስበው ከሁሉም የበለጠ የበደላት እሱ እንደሆነ ስለተሰማው ነው? ብቻ ያም ሆነ ይህ አሁን እየሮጠ ወደ ሚሊያርድ ቤት እየሄደ ነው መሀል መንገድ ላይ ሲደርስ ከኤፍራታ ጋር ፊት ለፊት ተገጣጠሙ ልቡ ያለው ሚሊያርድ ጋር ስለሆነ አልፏት ሊሄድ ሲል አየችው ፊቷ አልቅሳ ፍም መስሏል ወደ እሷ ጋር የተፈጠረውን ሰምቶ ሊያንቃት የመጣ ነው የመሰላት ፈርታዋለች ከዛ በላይ ግን ያደረገችው ነገር እና የሚሊያርድ ንግግር ሰላም ነስቷታል ‹‹እዩ ኤል›› እንደምንም ጠራችው ሲያያት አንዳች መጥፎ ነገር እንደተፈጠረ መገመት አላቃተውም ‹‹ምን አደረግሽ ነገርሻት?›› አላት ቀስ ብሎ:: …ማልቀስ ጀመረች ‹‹የእውነት እዩኤል አውቄ አይደለም የምታውቅ ነበር የመሰለኝ›› በሁለት እጆቹ ጭንቅላቱን ያዘ ‹‹እኔ እኔ …››መናገር አቃታት ለቅሶዋን ቀጠለች ‹‹ልረዳህ አስቤ ይቅርታ ልጠይቃት ነበር አመጣጤ ›› የዚህኔ አበደ ፀጉሩን እየነጨ ‹‹ማን እርጂኝ! ማን እርዱኝ አላችሁ?›› እንደ እብድ መጮህ ጀመረ ሁሉንም ነገር አበላሻችሁት ›› የለበሰውን ቲሸርት በሀይል ሲጎትተው ለሁለት ተገነጠለ ኤፍራታ በድንጋጤ ፈርታ መሸሽ ስትጀምር እየሮጡ ሲከተሉት የነበሩት እናቱ ደረሱ፡፡
ወዲያው ለብቻው ማውራት ጀመረ ‹‹እባክህ ከሆነው በላይ ህይወቴን ከባድ አታድርግብኝ በቃ ይበቃኛል!!!››ብላ በሀይል የምታንባርቅበት ይመስለዋል በልመና የተጀመረው ንግግር ከምኔው ወደ ጩኸት እንደተሸጋገረ አይገባውም እና ይደነግጣልል ‹‹እኔ እድለ ቢሷ ቀድሞውንስ እንዴት አስቤው ነው ሆኖልኝ የማያውቀውን ያውም እንዳንተ ያለ ወንድ በሂወቴ ሲገባ የእኔ ነው ብዬ አምኜ መቀበሌ… አንተም! እዩኤል አንተም እኔን ከዳኸኝ?›› እያለቀሰች እንዲህ ብላ ትዝብቷን የምትነግረውም ይመስለዋል ደግሞ ቆየት ትልና ‹‹እና አልበቃህም አሁንስ አላበቃም ጨዋታህ የስንት ተስፋ ቢስ ሴቶችን ሂወት ነው እንዲህ ያጨለምከው?›› ላለማልቀስ እንባዋን ዋጥ ለማድረግ እና እራስዋን ለመቆጣጠር ብትፈልግም ጥረቷ ሁሉ ከንቱ እየሆነ እንባዋ ገንፍሎ ከቁጥጥሯ ውጪ በሆነ መንገድ እየወረደ የምታወራው ይመስለዋል ‹‹ለማላስታውሰው ጊዜ ልቤ ዳግም ተሰባበረ አሁን ግን እንክትክቱ ነው የወጣው መቼም ይቅር አልልህም! ምን አረኩህ? ምን በደልኩህ? ምን አጠፋው? ከወደቅኩበት ተነሳው ስል!፣የተሰበረ ውስጤን ትጠግንልኛለህ ስል!፣ሁሉም ነገር እንዳዲስ ይጀመራል ብዬ ሳስብ! ለምን ግን ለምን በሂወቴ መጣህ ልትገለኝ ነው የፈለከው? ይኸው ሞቻለው እጅህ ላይ ይኸው!›› እጇን ዘርግታ እየሰጠችው እንባዋ ፊቷን እያጠበው የምታወራው ይመስዋል እሱም በበኩሉ ብቻውን መልስ ይሆናታል ብሎ ያሰበውን ነገር ይናገራል፡፡ ብቻውን ሲለፈልፍ ልጄ አበደ ብለው የእዩኤል እናት ጩኸታቸውን ያቀልጡታል የእዩኤል እናት ምንም መረጋጋት ስላልቻሉ ኤፍራታ በፍጥነት አንቡላንስ ጠርታ እዩኤልን ወደ ሀኪም ቤት ወሰደችው፡፡
ሚሊያርድ በቀጥታ የሄደችው ወደ ፍቅር ሀይቅ ነበር መንገድ ለመንገድ እንባዋን እያዘራች መንገዱን እንኳን በትክክል ማየት ተስኗት ያለማሰተዋል ትራመዳለች በተደጋገሚ የመኪና ክላክስ እየሰማች አትሰማም የሂወት ማብቂያ የሌለው ውጥንቅጥ ያሰለቻት ይህቺ ነፍስ ለመኖር አንድ እንኳን ምክንያት አጣች ‹‹ ምን አደረኩት? ኸረ እኔ ሰውን ሁሉ ምን አደረኩ? ሰው ሁሉ ለምን እንዲህ ክፉ ሆነብኝ? አሁን እስቲ ካልጠፋ ሴት በሂወት ተስፋ በቆረጠች ሴት እንዲህ ያለ በደል ማድረስ ለምን?...›› ማንም መልስ ባይሰጣትም ደጋግማ ትጠይቃለች ለብቻዋ መንገድ ላይ እንደ እብድ ታወራለች ‹‹አንተስ ፈጣሪ የት ነህ? በአንዲት በምታንህ ሴት ማብቂያ የሌለው በደል ሲፈፀም የታል መልስህ? ዘገየህ እኮ…ኸረረረረረረረ ወይኔ !!›› ጩኸቷን አቀለጠችው በአከባቢዋ የነበሩት ሰዎች ደንግጠው መሸሽ ጀመሩ ተስፋ የሰው ሁሉ የመኖር ምክንያት ነገን አለማወቅ! እውነት! እውነትን መሸከም የከበዳት አንዲት ነፍስ ሀይቅ ውስጥ ተወርውራ ገባች ጭው እያለባት ወደታች መስመጥ ጀመረች ፡፡

..............ይቀጥላል........✍️
Pages: 1