ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Singles & Dating . | 7 guests
Pages: 1
Posted on 03-14-19, 07:41 pm
Administrator

Karma: 100
Posts: 107/143
Since: 02-10-19

Last post: 1 hour
Last view: 1 hour
ወንዶች የሚማርካችቸው ምንድነው ክፍል 15


ሚሊያርድ እስር ቤት ሄዳ እዩኤልን ለመጠየቅ እየተዘጋጀች ነው እቴት ሰተት ብላ ወደ ክፍሏ ገብታ ‹‹ምንድ ነው ይሄ ሁሉ መኳኳል እስር ቤት ለመሄድ አይመስልም ›› ኮስተር ብላ ነው የምታያት ‹‹ውይ እቴት ደግሞ እስቲ አሁን ከሌላ ቀኑ ምንድነው የተለየ ያደረኩት ነገር ዝም ብለሽ አታካብጂ በቃ›› አይኗ ውስጥ ማፈሯ ይነበባል ‹‹ከዚ ልጅ ፍቅር ይዞሻል? እውነቱን ንገሪኝ? ›› ሚሊያርድ ድንግጥ አለች እቴት የበለጠ እየቀረበቻት ‹‹ይኸውልሽ እኔ እንደ እኩዮችሽ አፍቅረሽ ተፈቅረሽ የምትወጂውን ሰው አግብተሽ ስትኖሪ ማየት ህልሜ ነው ንገሪኝ ይሔንን ልጅ አፍቅረሽዋል?›› አይኖቿን ሰብራ አንድ ነገር መመለስ አቃታት ‹‹አውቄዋለው! የኔ ልጅ እራስሽን ጠብቂልኝ ዳግም ተሰብረሽ ማየት አልፈልግም ›› ብላ አቀፈቻት እቴት ሁሌም በወሳኝ ሰአት አጠገቧ ናት እንደ እናትም እንደጓደኛም እንደ እህትም …ሆና እየመከረች እና እየተቆጣች በተሳሳተ መንገድ እንዳትጓዝ ትመራታለች ሚሊያርድም እንደዛ ነው የተቀበለቻት እንደ ታላቅ ታከብራታለች እንደወላጅ ትፈራታለች ለእሷ ያላት ቦታ የተለየ ነው፡፡

እቴት ያዘጋጀችላትን ምግብ ይዛ የእስረኛ መጠየቂያ ሰአት ከመጀመሩ ደረሰች እዩኤል ተጠርቶ እስኪመጣ ድረስ ደቂቃዎች አለፉ በእስረኛ መጠየቂያው አዳራሽ ውስጥ በርካታ እስረኞች እና ታሳሪዎች እየተጠያየቁ ነው አብዛኛው እስረኛ ወጣት ነው አንዳንዶቹ ያለቅሳሉ ፣ሌሎቹ ተቀራርበው ሚስጥራቸውን ሌላው እንዳይሰማ በሚመስል ሁኔታ ያወራሉ፣የተቀሩት ግን እስር ቤትን እንደቤታቸው ቆጥረውት ይመስል ተዝናንተው ነው ተቀምጠው የሚያወሩት እነዚ ለማዳ! ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ እዩኤል ልክ ሲያያት ከመደንገጡ ብዛት ለመመለስ ቃጣው፣ልክ ስታየው በቀናት ውስጥ እንዴት እንደገረጣ አስተውላ ልቧ አዘነ፣ የልብ ምቱ ፈጠነ እንዲህ አድርጎት አያውቅም ፣አይኖቿ አይኖቹን ተርበውታል፣አጠገቧ እንደምንም ተጎትቶ መጣ ናፍቆት ቢሰማውም የጥፋተኝነት ስሜት እያንገላታው ነው፣ ወደ እሱ የሚገፋትን ስሜት መቆጣጠር ስላልቻለች አቀፈችው፣ መልሶ አላቀፋትም ‹‹አዝናለው›› ብሎ እንባው ወረደ ለእሷ የሚሰማው ስሜት እውነት ነው ግን ሊነግራት ልክ ሲፈልግ አንዳች ሀይል መጥቶ ይተናነቀዋል፣ አንደበቱን ሳግ ያፍነዋል፣ ወይም አንድ ነገር ይፈጠራል ‹‹ለምንድነው ሁል ጊዜም አዝናለው እና ይቅርታ የምትለኝ?›› አለችው ዝም አለ ‹‹እዩኤል ምን አድርገህ ነው ቆይ የታሰርከው?›› ‹‹ከሰው ጋር ተጣልቼ ›› ደፍሮ አይኗን አያት ታሳሳለች ስላሳለፈቸው አስቸጋሪ የሂወት መንገድ አሰበ ወንድሟ እንደዛ አይነት በደል በድሏት እንኳን ወንድሜ ብላ ማስታወሻዋ ላይ የፃፈችውን እያስታወሰ ዝም ብሎ እያያት ‹‹አንቺ ግን እንዴት ነሽ?›› አላት ‹‹እንዴ! እኔ ምን እሆናለው አንተ ነህ እንጂ እስር ቤት ያለኸው?›› ‹‹አይ ማለቴ የጠፋብሽን ደብተር አገኘሽው ወይ?›› ‹‹ውይ ከየት አገኘዋለው ብለህ ነው››ቀለል አድርጋ ‹‹በጣም ቀና ሰው ነሽ ማለቴ ጥሩ አሳቢ ነሽ ›› ‹‹ማለት አልገባኝም እንዴት አልክ?›› ‹እ እ እ ማ ለ ቴ የዛን ቀን ›› ተንተባተበ ማስታወሻዋን እያነበበ ስለሷ የተሰማውን ነበር የነገራት ‹‹እ የአደጋው ቀን ማለትህ ነው ይሄ ጥሩ አሳቢ መሆን እኮ አይደለም ሁሉም ሰው ማድረግ ያለበት ነገር ነው የኔ ቤተብ ብትሆንስ? ብሎ ለአንዲት ሰከንድ ማሰብ ብቻ ነው የሚጠበቅብህ በቃ የዋህነትም ክፍትም በተፈጥሮ አይሰጥም ቢሰጥ እንኳን ተፈጥሮ ለፈጠረው ታማኝ አየደለም›› ‹‹አንዴት ማለት አልገባኝም›› ‹‹እስቲ የትኛው ፍጡር ነው ለፈጠረው ታምኖ የኖረው ሰው እንኳን ማሰብ የሚችለው በየ ቀኑ በየ ሰአታት በየ ደቂቃ የፈጠረውን ይክዳል ትእዛዛቱን ያፈርሳል እና አንዱ በአንዱ ላይ ተፅእኖው ከባድ ነው ስለዚህ ታማኝ ልሁን እንኳን ብትል አትችልም በዚህ አለም ላይ ለብቻህ መቆም አትችልም ያለ ድጋፍ የቆመ ማንም የለም›› በመደነቅ አጨበጨበላት ‹‹አንቺ እስከ ዛሬ ድረስ የት ነበረሽ?›› ሰዎች ዞረው ሲያዩዋቸው ‹‹አንተ አቁም እንጂ ድጋሚ እንዳልመጣ ልታደርገኝ ነው እንዴ?›› ‹‹ስታስቢው እኔ እድሜ ልኬን እዚህ የምኖር ይመስልሻል እንዴ?›› ‹‹አዎ ይመስለኛል››አለችው እያሾፈች ‹‹ ለነገሩ ልክ ነሽ ይገባኛል!›› ‹የእስረኛ መጠየቂያ ሰአት አልቋል›› ተባለ ‹‹ያመጣሁልህ ምግብ አለ ›› ‹‹ይሄን ያህል መቸገር አልነበረብሽም መተሽ መጠየቅሽ ለኔ ከበቂ በላይ ነበር ›› ‹‹አታካብደው እና መቼ ነው የምትወጣው?›› ‹‹ምንም አልታወቀም አንድ የሚሰማኝን ስላንቺ ልንገርሸ?›› ‹‹እሺ ደስ ይለኛል›› ‹‹መጠየቂያ ሰአት አልቋል›› ተደገመ‹‹ከዚ በላይ ባውቅሽ ደስ ይለኛል ይሄ ለእኔ የሚገባኝ ሰው አይደለውም በርገጥ ግን አመሰግናለው›› ብሎ ምግቡን ሲቀበላት ‹‹እኔስ ስላንተ የሚሰማኝን መናገር እችላለው››በአንገቱ ንቅናቄ አዎንታውን መለሰላት‹‹የእስረኛ መጠየቂያ ሰአት አልቋል›› ተሰለሰ ‹‹እወድሀለው›› ብላ ከንፈሩን ሳመችው ባለበት ደርቆ ቀረ እሷ ግን ወታ ሄደች፡፡ እሱ ምንም ቢሰማው ግድ የላትም ለረዥም ግዜ ስትመኘው የነበረውን ነገር በመጨረሻ አደረገችው፡፡ እዩኤል ልቡ ድው ድው ድው እያለ ወደ ውስጥ ሲገባ ስትስመው የተሰማውን ስሜት አይነት ከዚ ቀደም ተሰምቶት አያውቅም ስሜቱ ሁሉ ተዘበራረቀበት ርብሽብሽ የሚያደርግ አንዳች የሚገርም ስሜት፡፡ ለሰአታት ደጋግሞ ስለ እሷ እና ስላደረገችው ነገር እያሰበ እያሰላሰለ ናፈቀችው እንዴት ደፍራ እንደሳመችው እያሰበ ድፍረቷ አስደነቀው፡፡

‹‹ ‹‹ ‹‹ ‹‹

ዮናስን ደጋግመው ከእዩኤል ጋር በምን ምንያት እንደተጣሉ ቢጠይቁትም ለመናገረ ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ ሰለዚህ ማስታወሻ ቤተሰቦቻቸው ቢሰሙ ነገሩን የበለጠ ማክረር መስሎ ተሰማው በእሱ ምክንያት እየተፈጠረ ያለው ነገር እና የእዩኤል ይህን ያህል ቀን መታሰር አላስደሰተውም በተደጋጋሚ የእዩኤል ቤተሰቦች ጉዳዩን በሽምግልና እንዲያዝ እና የሚፈልጉትን ያህል ካሳ የዮናስን የክምና ወጪ ጨምሮ እንደሚክሱ ተናግረው ሳይሳካላቸው ቀርቶ ዛሬ በብዙ ልመና እና ደጅ መጥናት በሀሳባቸው ተስማምተው ሽምግልናውን ተቀበሉ ፖሊስ ጣቢያም ሄደው ክሱን አነሱለት፡፡ የዮናስ እናት ከስራ ልጇ እስኪድን ለማስታመም ፍቃድ ስለወሰደች ቀን ቀን አብራው ትውላለች አብራው ስትሆን እረጅም ሰአት በዝምታ ተውጦ ሲተክዝ ስለምታየው ከጊዜ ወደ ጊዜ የጓደኛው እንደዚ ማድረግ እየጎዳው በሀሳብ ውስድ እንደሚያደርገው እየተሰማት በእጅጉ ትጨነቃለች በመሀል አንድ ሀሳብ መጣላት ልብ ወለድ የመሰላትን ግን ምንነቱን በርግጥም በትክክል ያላረጋገጠችውን ከልጇ ክፍል ያገኘችውን ያንን አፃፃፉ የሚያምረውን አጀንዳ ደብተር ልጇ ልብ ወለድ መፃፍ እደምትሞክር በመገመት ልታነብለት ይዛው መጣች..........

...........ይቀጥላል........✍️
Pages: 1