ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Ethiopian News & Events አዲስ ዜና. | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 03-13-19, 07:19 am


Karma: 90
Posts: 875/879
Since: 02-29-16

Last post: 6 days
Last view: 6 days
‹‹እኛ ወታደራዊ ምርኮኞች ነን የፈለጋችሁትን አድርጉ››

አቶ በረከት ስምዖን

ከጥረት ኮርፖሬት ድርጅቶች ጋር በተያያዘ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ታስረው በሚገኙት አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ ላይ፣ ተጨማሪ ምርመራ ለሦስተኛ ጊዜ ተፈቀደ፡፡

የተጠርጣሪዎቹን ጉዳይ በመመርመር ላይ የሚገኘው የክልሉ የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ በተፈቀደለት 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ውስጥ በአገር ውስጥና ውጭ አገር ከሚኖሩ ሦስት ሰዎች፣ የምስክርነት ቃል መቀበሉን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ በተጨማሪም በርካታና የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎችን መሰብሰቡንም አክሏል፡፡

የተቋማቱን የኦዲት ሥራ አለማጠናቀቁን ዓቃቤ ሕግ አስረድቶ፣ የኦዲት ምርመራውን ለማጠናቀቅ በሥራ ላይ ያሉ ከ20 በላይ ባለሙያዎችን እያነጋገረ ቢሆንም፣ የተወሰኑት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ተጨማሪ ባለሙያዎች መፈለግና ማጠናቀቅ ስላለበት ተጨማሪ 14 ቀናት ስለሚያስፈልገው እንዲፈቀድለት ጉዳዩን ለሚከታተለው የባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ጥያቄውን አቅርቧል፡፡

ለመጀመርያ ጊዜ በሁለት ጠበቆች ተወክለው የቀረቡት አቶ በረከትና አቶ ታደሰ ባቀረቡት መቃወሚያ እንደተናገሩት፣ ጉዳዩ ውስብስብ ሳይሆን ግልጽ ነው፡፡ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ቀደም ብሎ በዋለው ችሎት 14 ቀናት ያስፈቀደው ምርመራቸውን አጠናቀው ለመቅረብ በመሆኑ፣ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሊፈቀድለት እንደማይገባ ተከራክረዋል፡፡ ክርክራቸው ታልፎ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የሚፈቀድ ከሆነም ከአምስት ቀናት ያልበለጠ እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡

በተጨማሪም የተጠረጠሩበት ጉዳይ ዋስትና ስለማይከለክል የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸውም ጠይቀዋል፡፡የዋስትናን ጉዳይ በሚመለከት ቀደም ባሉት ችሎቶች በተጠርጣሪዎቹ ተጠይቆ ብይን የተሰጠበት በመሆኑ፣ በይግባኝ መጠየቅ ከሚቻል በስተቀር በተያዘው መዝገብ እንደማይቻል በመግለጽ ፍርድ ቤቱ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ በተጨማሪ የምርመራ ቀኑ ላይ መዝገቡን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት በአዳር ለማክሰኞ መጋቢት 3 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱ በነጋታው ሲሰየም፣ አቶ በረከትና አቶ ታደሰ የቀረቡት ያለ ጠበቃ ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ጠበቆቹ የቀሩት ዛቻና ማስፈራሪያ ስለደረሰባቸው መሆኑን ሊገልጹ ሲሞክሩ ፍርድ ቤቱ አስቁሟቸው፣ ቅሬታቸውን በጽሑፍ በጽሕፈት ቤት በኩል እንዲያቀርቡ በመንገር የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ከጠየቀው 14 ቀናት ውስጥ ስምንት ቀናት በመፍቀድ፣ ለመጋቢት 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

እነ አቶ በረከት ቅሬታቸውን በጽሑፍ እንዲያቀርቡ የተነገራቸው ቢሆንም፣ ‹‹እኛ ወታደራዊ ምርኮኞች ነን የፈለጋችሁትን አድርጉ›› በማለት እየተናገሩ ከችሎት ወጥተዋል፡፡
Pages: 1