ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Religion. | 1 guest
Pages: 1
Posted on 03-07-19, 09:34 pm (rev. 1 by Ye Arada Lij on 03-07-19, 09:51 pm)


Karma: 90
Posts: 868/887
Since: 02-29-16

Last post: 308 days
Last view: 308 days
እንኳን ለዐብይ ፆም በሰላም አደረሰን
☞ፆም ማለት ምን ማለት ነው?
☞የአብይ ስያሜዎች ስንት ናቸው
☞የአብይ ፆም ለምን ታላቁ ጾም ተበለ
☞የአብይ ጾም ስንት ክፍሎች አሉት
☞የአብይ ጾም ለስንት ሳምነታት ይጾማል
☞ስለ መጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ምን ያውቃሉ

1ኛ. ፆም ማለት ምን ማለት ነው?
ፆመ ፦ ተወ " ታቀበ"ታረመ ካለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ነው።
ፍቹም ምግብን መተው ' መከልከል' መጠበቅ ማለት ነው።
ፆም ማለት ሰውነት ከሚያስፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መከልከል መወሰን ማለት
ነው። ወይም ለሰውነት የሚያምረውን የሚያስጎመጀውን ነገር መተው ማለት
ነው ።
ፆም ከሃይማኖት ጋር ዝምድና ስላለው ሃይማኖት ባለበት ሁሉ ፆም አለ።
ፆም በብሉይ እና ኪዳን ከፍተኛ ቦታ አለው ።
ነብያት ከእግዚአብሄር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህል ውሃ በአፋቸው አይገባም
ነበር።//ዘፀ ፴፬÷፳፰//34*28//
በሐፂያት ብዛት የታዘዘውን የእግዚአብሔርን መዓት የሚመልሰው ሕዝቡ በፆም
ሲለምኑት ሲማልዱት ነበር። //ዮሐ ፪÷፯_፲// 2*7-20//
በሐዲስ ኪዳንም ፆም ሰው ሰራሽ ህግ ሳይሆን እራሱ መድኃኒታችን በመዋዕለ
ስጋዌው የስራ መጀመሪያ አድርጎ የሰራው ህግ ነው።//፬÷፪// 4*2//
ይህ ብቻ ሳይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር መንፈስ እርኩስ ሰይጣን እንኳን
በፆም እሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግሯል።// ማቴ ፲፯÷፳፩//
17*21/ሐ
ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ የታዘዙ ሐዋሪያትም ከመንፈስ ቅዱስ በየጊዜው
ትዕዛዝ እሚቀበሉበት በፆም እና በፆለት ላይ እንዳሉ ነበር።// የሐዋ
፲፫÷፪//13*2//
ለስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናት ቀሳውስት የሚሾሙት በፆምና
በፆለት ነበር።//የሐዋ፲፫÷፫//13*3//
ፆምስ በታወቀው እለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ መከልከል ነው።
ፆም ማለት፦ጥለላት ማባልዕትን ፈፅሞ መተው ሰውነትን ከመብልና ከመጠጥ
ከሌላውም ክፉ ነገር ሁሉ መጠበቅ ፣መገዛት፣ መቆጣጠር፣ በንስሐ ታጥቦ
በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ ይቅር በለኝ በማለት ቅድመ
እግዚአብሔር በመንበርከክ ምህረት በአምላክ ለመቀበል መዘጋጀት ነው።
ፆም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ፣ሀይለ ፍትወትን የምታደክም የበጎ ምግባር
ሁሉ መጀመሪያ ከእግዚአብሔር ፀጋን የምትሰጥ ፣የወንጌል ስራ መጀመሪያ፣
የፅሙዳን ክብራቸው፣ የደናግል እና የንፅህና ጌጣቸው
፣የንፅህና መገለጫ፣ የጸሎት ምክንያት እናት፣ የእንባ መገናኛ መፍለቂያ፣
አርምሞን የምታስተምር፣ ለበጎ ስራ ሁሉ የምትነቃቃ፣ ሰውነትን
በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትህትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ
መድኃኒት ነፍስ ናት።
ከህገ ልቦና ከነበሩ አበው አንስቶ በዘመነ ኦሪት እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ
በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ ቀደምት አበው ነቢያት፣ ነገስታት፣ካህናት በፆምና
በጸሎት ፅሙድ ሁነው እግዚአብሔር አምላካቸው ከክፉ ነገር እንዲሰውራቸው
በይቅርታ እንዲጎበኛቸው ሀይልንም እንዲያጎናፅፋቸው ተማፅነው ሀሳባቸውን
ፈፅሞላቸዋል።
በሀድስ ኪዳን ፆም ስለ ፅድቅ ተብሎ መከናወን ያለበት አብይ ተግባር ነው። //
ማቴ፭÷፮// 5*6//
ስጋዊ ጥቅምን ለማግኘት ተድላ ስጋን በመሻት ሳይሆን ዘላለማዊ መንግስት
ለመውረስ ስለ ፅድቅ ተብሎ የሚፈፀም ነው።
ፆም እንደምን ነው ቢሉ የስጋ ምግባር ነው።
ምፅዋት የገንዘብ ግብር እንደሆነች:አንድም ምፅዋት ስጋን መገበር ነው።
ምፅዋት ገንዘብ መገበር እንደሆነች። ~~~ስለዚህ የሚፆም ሰው በፈቃደ
ስጋው ላይ ድልን ይቀዳጃል።
በእምነት ሁኖ የለመነውን እግዚአብሔር ይሰጠዋል። ሰማያዊ የሆነውን
ምስጢር ለማየት ከአለማዊ ነገሮች ተለይቶ ይነጠቃል።
በአለም እየኖረ ከአለሙ ይለያል። ከአለም አይደለምና//
ዮሐ፲፭÷፲፱//15*19 //

2ኛ.
ዐቢይ ጾምም ቤተክርስቲያናችን እንድንጾም ካወጀችልን ጾም አንዱ ነው፡፡
ዐቢይ ጾምየተለያዩ ስሞች አሉት፡፡ አንደኛ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም በመሆኑ እንዲሁም ዐቢይ
እግዚአብሔር ወዓቢይ ኀይሉ ዓቢይ እግዚአብሔር ወብዙኃ አኰቴቱ የተባለ
ጌታ የጾመው ስለሆነ፣ /መዝ.47፥1፣ መዝ.146፥5/፡፡ ሁለተኛ ሁዳዴ ጾም
ይባላል፡፡ ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት
ሥራ ሁዳድ ስለሚባል ሲሆን ከአጽዋማት ሁሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ኃያሉ
አምላካችን ስለጾመው ነው፡፡፣ /አሞ.7፥1/፡፡ ሦስተኛ በዓተ ጾም ይባላል፡፡
የጾም መግቢያ፣ መባቻ ወይም ጾሙ የሚሰፍርበት በዓት ማለት ነው፡፡ አራተኛ
ጾመ አርባ ይባላል፡፡ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው 40 /ዓርባ/ ቀን
ስለሆነ፣ /ማቴ.4፥1/ አምስተኛ ጾመ ኢየሱስይባላል፡፡ ጾሞ፣ ጹሙ ብሎ
ስላዘዘን፣ ስድስተኛ ጾመ ሙሴ ይባላል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በዘወረደ ሰኞ ዕዝል
ከመዝ ይቤ ሙሴ እስመ ለዓለም፣ ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት እያለ በጾመ
ድጓ ስለ ዘመረ ነው፡፡
ዐቢይ ጾምጌታ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው የአርባ ቀን ጾም ነው፡፡ ማቴ.4፥1
ምእመናን ጌታቸው ያደረገውን ምሳሌ ተከትለው ይጾሙታል፡፡ ዐቢይ ጾም
ስምንት ሳምንታት /55 ቀኖች/ አሉት፡፡ ሰባት ቅዳሜ ስምንት እሑድ ይገኛሉ፡፡
አሥራ አምስት ቀን ማለት ነው፡፡ ከጥሉላት እንጂ ከእህል ውኃ ስለማይጦሙ
የጦሙ ወራት አርባ ቀን ብቻ ይሆናል፡፡

3ኛ.
የአቢይ ጾም ሦስቱ ክፍሎች
1. ዘወረደ (ጾመ ሕርቃል)፤ ይህም ጾሙ ከሚገባበት
ሰኞ ጀምሮ እስከ እሑድ ያረስ ያለው 7 ቀን ነው።
2. የጌታ ጾም፤ ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣዕና
ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለው 40 ቀን ነው።
3. ሕማማት፤ ይህም ጌታችን በአልዓዛር ቤት ለማዕድ
ከተቀመጠበት የሆሳዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሥዑር
ቅዳሜ ያለው መከራን የተቀበለበት 8 ቀን ሕማማት
ነው።
ይህም 7+40+8 = 55 ቀን ማለት ነው።

4ኛ.
የአብይ ጾም ሳምንታት 8 ናቸው፤
ዘወረደ
ቅድስት
ምኩራብ
መጻጉዕ
ደብረዘይት
ገብርሔር
ኒቆዲሞስ
ሆሣዕ

ሰለ ተትርጉማቸው ከታች ከተለጠፈው ሰንጠረዥ ተመልከት

5ኛ. ለምን አብይ / ታላቅ
ተባለ
አብይ ፆም መባሉ ትልቅና ታላቅ ፆም መሆኑን
ለማሳወቅ ነው። ይህ ፆም ታላቅ
መባሉም ለ55 ቀናት ያህል መፆሙና
ከሌሎቹ አፅዋማት ጋር ሲነፃፀር በቁጥር
መብለጡ ብቻ ሳይሆን ጌታችን አምላካችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ
ቆሮንቶስ መፆም ሳይገባው ለእኛ አርአያና
ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የፆመው ፆምም
በመሆኑ ነው

6ኛኛ.
የመጀመሪያ የአቢይ ጾም መግቢያ እሁድ ዘወረደ ይባላል ደግሞም
ጾመ ሕርቃል ይባላል፡፡ ስያሜውም፤ በ 614 ዓ . ም ኪርዮስ የተባለ
የፋርስ ንጉሥ ኢየሩሳሌምን በመውረር ጥቃት አደረሰ፡፡ በዚህ
ወቅት በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ በሠራችው ቤተመቅደስ
ውስጥ ሲገባ ንግሥቷ በክብር አስቀምጣው የነበረው የጌታችን
የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንደ ፀሐይ ሲያበራ
አገኘው፡፡ ቢነካው አቃጠለው ዲያቆናቱን አሸክሞ ሌላውን ንዋየ
ቅድሳት ዘርፎ 60 ሺ የሚደርሱትን አቁስሎ ገድሎ 3 ሺ የሚሆኑትን
ማርኮ ከተማዋንም አቃጥሎ ወደ ፋርስ ባቢሎን ይመለሳል፡፡
በዚህ ጊዜ ከጦርነቱ ያመለጡ በየዋሻው በየጉራንጉሩ ገብተው
የተሸሸጉ ተሰብስበው ከ 14 ዓመት በኋላ በ 628 ጩኸታቸውንና
የደረሰባቸውን በደል ለክርስቲየኑ የሮም ንጉሥ ሕርቃል
ይነግሩታል፡፡ እርሱም ሐዋርያት ሰውን የገደለ እድሜውን በሙሉ
ይጹም ስላሉ እንዴት ላድርገው አላቸው እኛ የአንተን እድሜ
ተከፋፍለን እንጾማለን ብለው አንድ አንድ ሳምንት ደርሷቸው
ጾሙን በሚገባ ጾመውታል፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ
መስቀልና የተማረኩ ክርስቲያኖችን ለመመለስ ሕርቃል ጦር መዝዞ
በኪርዮስ ላይ ተነሳበት ድል ለሕርቃል ሆነና መስቀሉን ያለበትን
አጥቶ ሲቸገር መስቀሉን ሲቀብርና ዲያቆናቱን ሲያስገድል
በመስኮት ሆና ያየችው ከኢየሩሳሌም የተማረከች አንዲት ብላቴና
አሳይታው አውጥቶ በልብሰ መንግሥቱ ጠቅልሎ ወደ
ቁስጥንጥንያ ተመለሰ፡፡ የተማረኩት በሙሉ ነጻ ወጡ ይህን
ለማሰብ ለማስታወስ በተጨማሪ በኃጢአት ላይ ድል እንድናገኝ
መንፈሳዊ ጦር በውስጣችን እንዲበዛልን መስቀልህ ከምርኮ
እንደተመለሰ እኛንም ከኃጢአት ምርኮ መልሰን ለሕርቃል ድል
መንሳትንና በጠላቶቹ ላይ ኃይልን እንደሰጠኸው ለእኛም
በኃጢአት ላይ ድል መንሳት መንፈሳዊ ኃይልን ስጠን እያልን
እንጾመዋለን፡፡ በጌታ ጾም ላይ እንዲጾም የሆነበት ምክንያት ጾሙ
የጌታ ጾም በሚጾምበት ወቅት ላይ ስለተጾመ ቤተክርስቲያናችን
አብራ ደንግጋዋለች፡፡እዚህ ላይ በዚያን ጊዜ ለሕርቃል ሕዝቡ
ሱባኤ ይዞለታል፡፡ ዛሬም እኛ ለቤተክርስቲያን ያደረግነውን በማሰብ
እግዚአብሔር አምላክ ለሕርቃል የሰጠውን በጠላቶቹ ላይ ድል
መንሳትን ለእኛም እንዲሰጠን የምንጠይቅበት ስለሆነ
የመጀመሪያውን ሳምንት በሕርቃል ሰይመን ጾሙን እንጾማለን፡፡
የእኛ ጠላት የጨለማ ገዥ የሆነው ዲያቢሎስ ነውና እሱን ደግሞ
በጾም እንደምናሸንፈው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
አስተምሮናል፡፡አንድም ዘወረደ ማለት

«ዘወረደ » ማለት « የወረደ» ማለት ነው፡፡ አምላክ ሰው ሆነ፤
ሰው አምላክ ሆነ ማለት ነው። ይህም ጌታችን መድሃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት
መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር፤
ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን
የሚያመላክት፣ የሚታወስበት፣ የሚነገርበት የዐቢይ ጾም አንደኛው
ሳምንት ነው፡፡ዮሐ.3-13፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም
በገባዉ ቃልኪዳን መሰረት “ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ
እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ” እንዳለ ሐዋርያዉ
ቅዱስ ጳዉሎስ የጠፋዉን አዳም ፍለጋ ከአባቱ እሪና ሳይጎድል
ሳይለይ ከሰማይ መዉረዱን የምናዘክርበት በዓል ነዉ። ይህ ጾም
የጾም መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት የምንጾመው ጾም ሲሆን
ሕርቃል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ እግዚአብሔር አምላክ
ለአዳም “ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ
በመልዕልተ መስቀል ተሰቅየ አድንኃለሁ” ብሎ ለአዳም ቃል
ገባለት ፡፡ ዘፍ. ፫ ፥ ፲፭ ይህ ኪዳነ አዳም ይባላል ፡፡ የቃል ኪዳን
ሁሉ መሠረት ነው ፡፡ ሁለቱን ኪዳናት (ብሉይ ወሐዲስ) በፅኑዕ
ተስፋ ያስተሳሰረ የረጅም ዘመናት የድኅነት ሰንሰለት ነው ፡፡
ዘወረደ እርቀ አዳም ፤ ተስፋ አበው ፤ ትንቢተ ነቢያት ፤ ሱባኤ
ካህናት መፈፀሙ ፤ ኪዳነ አዳም መሲህ መወለዱ የሚነገርበት
የፍቅር አዋጅ ነው ፡፡
ዘወረደ ማለት?
ምስጢረ ሥጋዌ ትምህርት ነው
፡ ዘወረደ ስንል አምላክ መጣ ፤
ረደ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ ፤
ፍጹም ተዋሕዶ ሰው ሆነ ማለታችን ነው ፡፡
ወረደ በአምላክ ትህትና ክብረ አዳም የሚነገርበት ነው ፡፡
ምላክ ሰው በመሆኑ ሰው አምላክ ሆነ ፤ ከበረ ፤ ገነነ ፤ ነገሠ ፡፡
ያው አምላክ ክርስቶስ በቅድስት ሞቱ ሟቹን አዳም ዘላለማዊ
ሕያው አደረገው ፡፡
አምላክ ወልደ አምላክ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ሞቶ ለአዳም
ያለውን ታላቅ ፍቅር ገለጸ ፡፡
ተጣላውን አዳምን በፈቃዱ ታረቀው ፡፡
ላቶቹ ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን ፥ ይልቁንም
ከታረቅን በኃላ በሕይወቱ እንድናለን ፡፡ ሮሜ. 5 ፥ ፲ ፡፡ በዚህም
ትህትናን ፍቅርን አስተማረን ፡፡

በዚህ በመጀመርያው ሳምንት ከመዝሙረ ዳዊት ላይ የሚሰበከው ምስባክ፦
በግዕዝ፦
እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ
አሚን ወሰናይት ቅድሜሁ
ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ
በአማርኛ፦ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ።
ምስጋናና ውበት በፊቱ ነው፥
ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው። (መዝ.፺፭(፺፮)፡፭
በዚህ በመጀመርያው ሳምንት የሚነበበው የወንጌል ክፍል፦
ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ
ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን
ስትጦም፥
በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን
ተቀባ ፊትህንም
ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። ብልና ዝገት
በሚያጠፉት ሌቦችም
ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤
ነገር ግን ብልም
ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ
በሰማይ መዝገብ
ሰብስቡ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። የሰውነት
መብራት ዓይን ናት።
ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤ ዓይንህ
ግን ታማሚ
ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን
ጨለማ ከሆነ፥
ጨለማውስ እንዴት ይበረታ! ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም
የለም፤ ወይም
አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል
ሁለተኛውንምይንቃል፤
ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ
ነፍሳችሁ
በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት
አትጨነቁ፤ ነፍስ
ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን? ማቴ.፮፡፲፮-፳፭

ጾም ስጋችንን ለነፍሳችን የምናስገዛበት ከፈጣሪ
ጋር የምንገናኝበት የጽድቅ መንገድ ለስጋ ጤንነትም ቢሆን
አስፈላጊያችን የሆነ አንዱና ዋነኛዉ የጽድቅ እቃ ጦራችን ነዉ፡፡
ሆኖም የጾም ወቅት ሲመጣ አቀበት የሚወጡ ይመስል
የሚፈሩትና የሚያማርሩት ሳይሆን እንኳን መጣልን ተብሎ በጉጉት
የሚናፈቅ መሆን አለበት፡፡ስለሆነም ማንኛዉም ሰዉ ጾሙን ሲጀምር
የሚከተሉትን ጉዳዮች በደንብ ሊያጤናቸዉ ይገባል፡፡
የዲያብሎስን ሥራ ሊያፈርስየተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅም
በፆም ድል ማድረግን ለእኛ አስተምሮናል። እኛምበዚህ በአብይ
ፆም የለመነውና የጠየቅነው ነገር ሁሉ ከኃጢአት
በስተቀርእንዲከናወንልን ፆምን ገንዘባችን እናድርግ። በፆም
የተጠቀሙ ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳንእናቶች እንዳሉን
እናስተውል። በተለይ አሁን በቤተ ክርስቲያን ላይ
እየደረሰበሚታየው አስቸጋሪ ፈተና እያንዳንዳችን ልባዊ ፆም
በመፆም ልዑል
እግዚአብሔር የፀሎታችንን ምላሽ እንዲሰጠን እንማፀን።
ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን
አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ(source)
ማኅበረ ቅዱሳን 2004 ዓ.ም ፆሙን አስመልክቶ ካቀረበው ዲያቆን ንጋቱ አበበ ፆሙን አስመ
ካቀረበው የተወሰደ
Pages: 1