ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Family. | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 02-08-19, 10:30 pm


Karma: 100
Posts: 742/769
Since: 03-20-17

Last post: 242 days
Last view: 242 days
እርሶ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?

ልጄ 11 ዓመቱ ነው፤ በትዳሬ ፍፁም ደስተኛ ስላልነበርኩኝ ከ4 ዓመት ከ6 ወሩ ጀምሮ ብቻዬን የሚያስፈልገውን ነገር ሁላ እያረኩ አሳደኩት።

በወቅቱ ከእናቱ ጋር ተስማምተን መኖር ግን አልቻልንም ነበር። በመሃላችን ያለው አለመስማማትና ግጭት እየባሰ ሲመጣም ከ6 ዓመት በፊት የመጨረሻውን መለያየት ፈፀምን። ልጃችንንም በፍ/ቤት ውሳኔ እኔው ጋር እንዲያድግ ሆነ።

እኔም ጊዜዬን ለሱ ሰጥቼ 'ምንም ሳይጎልበት አሳደኩት። እሱ አብሮኝ እስካለ ድረስ ከብዙ ነገር ተቆጥቤ እያሳደኩት በረፍት ቀኑም እናቱን እየጠየቀ ኖርን፡፡

ከሁለት ወር በፊት ግን አንድ ነገር ተፈጠረ። በልጃችን ባህሪ ዙሪያ ለመነጋገር እርሱም ባለበት ከእናቱ ጋር ቁጭ ብለን አወራን! እሱም እኛን ጥሩ ልጅ በመሆን እንደሚያስደስተን ቃል ከገባ በኃላ "እናንተም አብራችሁ በመሆን እኔን ለማስደሰት ቃል ግቡልኝ።" በማለት ያልጠበቅነውን ጥያቄ አቀረበ። በኔ በኩል ሊሆን እንደማይችል ቁርጡን ነገርኩት፡፡ እርሱ ግን አብረን ከእናቱ ጋር የማንሆን ከሆነ፤ አንድ ነገር እንድፈቅድለት ጠየቀኝ። እሱም እናቱ ጋር መሆንን አልከለከልኩትም።

በሌላ ጎን ደሞ ወደፍቅር የተቀየረ ህይወት አለኝ። ልጄ ወደእናቱ ከሄደ በኃላ ለፍቅረኛዬ ያለኝ ቦታ ጨመረ፡፡ ፍቅረኛዬ ስላለፈው ህይወቴ ሁሉንም ታውቃለች።ልጄ ከእናቱ ጋር እንድታረቅ እንደሚፈልግ ግን አታውቅም። ልጄ ደሞ ስለፍቅረኛዬ ምንም አያውቅም።አንድ ቀን ልጄ "አባቴ ብታገባ ይከፋኛል። እቀየምሃለሁ። " ቃል በቃል አለኝ።

"እህት ወንድም እንዲወለድልህ አትፈልግም? " ብዬም ጠየኩት"እፈልጋለሁ። ግን ከእናቴ። " የሚል ቁርጥ ያለ መልስ ሰጠኝ።"ታርቀን ከምታገኘው ጭቅጭቅና ስድብ ይልቅ፥ ተራርቀን ያለው ሰላም ይሻላል። " ብዬ አስረድቼው ነበረ።

ከነበረብኝ ጉዳት አኳያ እንኳን ታርቆ ወደኃላ መመለስ ሳስበው ያመኛል ።

ለ6አመት ብቻየን ካለ እናት ያሳደግኩት ልጄ ፍላጎት ለማሟላት ስል የራሴን የፍቅር ህይወት መተው በድጋሜ መስዋዕት መክፈልና ልጄ እንዳይከፋብኝ ወይስ ከፍቅረኛዬ ጋር ቀጥዬ ፈጣሪ ከረዳኝ ልጄን ማሳመን?

እርሶ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?
Pages: 1