ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Just For Laughs - አስቂኝ ነገሮች . | 1 guest | 2 bots
Pages: 1
Posted on 09-22-18, 06:56 am


Karma: 100
Posts: 735/760
Since: 03-20-17

Last post: 15 days
Last view: 15 hours
ሰላም ጓዶች እንዴት ናችሁ? ፒስ ነው? እኔ እነዛ ዥልጦች ያን ቦንብ ካፈነዱ ጀምሮ የተገፈፈው ቀልቤ እስካሁን አልተመለሰልኝም።
ዶህ'' ስል እኛ ለአብይ ክብር የተተኮሰ መሰሎን ጮክ ብለን ይደገም ይደገም ሁለ ብለን ነበር እኮ!!!
ከዛ ህዝቡ ወደኛ መምጣት ጀመራ።አሁንም አልገባኝም--- ምንድነው ወደ ታላቁ ሩጫ ተቀየረ እንዴ ብዮ እየሾፈኩ ስጠይቅ. ...ቦንብ ነው ቦንብ ፈነዳ ምናምን የሚል ወሬ ጆሮዮ ጠብ አለች። ወንድሜ....አበባ ብቂላ መች ይሮጣል ከፈጥነቴ ብዛት ቤቴን ሁሉ አልፌ ነው የቆምኩት።
አሯሯጤ እማ ሌላ ቦንብ ያዛ የወያኔ ሽፍታ እየተከታተለኝ ያለ ነው የሚመስለው።
ወይኔ....ያን ከመሰለ ደስታ በሽብር ያቋረጣ ሰው እግዜር የጁን ይስጠው; እኛን እንደስደነገጠን እድሜ ልኩን ስደነግጥ ይኑር..
የሰውን ልጅ በቦንብ ለማቡነን እንዳሰባ አመዱ ቡን ይበል...
አሜባ ይጫወትበት....
ቤቱ ለልማት ተፈልጎ ያላ ካሳ ይፈረስ...
ፌዴራሎች ከበው ያናጋግሩት...
ጥፍሩን ሞጃሌ ይጫወትበት...
እንደ ኮማንድፖስት ብን ብሎ ይጥፋ.....
ምን ልበላቸው ሌላ????
ብቻ...አብይን በክፉ ያዩ አይኖች ትራኮማ ይያዛቸው
ከድያብሎስ ጋር ይደመር ከኛ ይቀነስ
አተት ኮተት ከቤቱ አይጥፋ።
ሆሆሆሆሆ ገና ሳንደመር ኢትዮጵያውያን የነበርነውን ሰዎች ኢትዮጵያ ልያደርጉን????
Pages: 1