ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Animals . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 09-08-18, 07:49 am


Karma: 90
Posts: 829/879
Since: 02-29-16

Last post: 66 days
Last view: 66 days
በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኙ ዊዝሎች (Weasels) ደም የጠማቸው ገዳዮች በሚል ዝናቸው የናኘ ነው፡፡ አነስተኛ ሥጋ በል እንስሳት ቢሆኑም፤ ይኬን በመጠን ማነሳቸውን ከሚገባው በላይ በጥንካሬ፣ ድፍረትና ፍጥነታቸው ያካክሱታል፡፡ የሥነ ሕይወት ተመራማሪዎች እንደሚያምኑት እኒህ እንስሳት ከመግደል ለሚያገኙት ደስታ ብቻ ሲሉም ይገላሉ፡፡ በአንድ ቦታ ተሰባስበው የሚገኙ አይጦችን በሙሉ በመግደል ይታወቃሉ፡፡ በዚህም ፀባያቸው ምክንያት ብዙውን ጊዜ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመሰደድ ይገደዳሉ፡፡ በአካባቢያቸው የሚገኙትን ታዳኞቻቸውን በብዛት ስለሚገኙ፤ የሚበሉትን ያጡና አካባቢ መቀየር ግድ ይላቸዋል፡፡ በዊዝል ጎጆ ውስጥ የሞቱ አይጦችን ማግኘት የተለመደ ነው፡፡

የዊዝልን ዱካ ሲከተል የነበረ አንድ የሥነ ሕይወት ተመራማሪ በመንገዱ ላይ 11 የጥንቸሎችን ሬሳ መመልከቱ ተዘግቧል፡፡ ዊዝሎች ብዙውን ጊዜ ማረድ ከመጀመራቸው በፊት ትንሽ ደም ብቻ ይጠጣሉ፡፡ ትልቆቹ ዊዝል ከግማሽ ኪሎ ግራም ያነሰ ይመዝናሉ፡፡ ድፍረትና ቆራጥነታቸው ግን አስደናቂ ነው፡፡ በብዙ መጠን የሚበልጣቸውን እንስሳ ለማጥቃት ወደኋላ አይሉም፡፡ ብዙውን ጊዜም አሸናፊ ናቸው፤ ቢያንስ እየሞከሩ ይሞታሉ፡፡ እንስሶቹ የአይጥ አደገኛ ጠላቶች ናቸው፡፡ ለምሳሌ በኒውዮርክ ውስጥ 300 ሺሕ ዊዝሎች አሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ እነዚህም በየዓመቱ ለ60 ሚሊዮን አይጦች መውደም ምክንያት ናቸው፡፡

ማንይንገረው ሸንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004 ዓ.ም.)

Pages: 1