ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Animals . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 09-08-18, 07:48 am


Karma: 90
Posts: 828/879
Since: 02-29-16

Last post: 66 days
Last view: 66 days
ሦስት ጭራ ያላቸው ባለ ባላ መሳይ ጭራ እንሽላሊቶችን ማግኘት የተለመደ ነገር ነው፡፡ የዚህ ምክንያቱም እንሽላሊቶች የተቆረጠ ጭራቸውን ለመተካት በሚደረገው ትክክለኛ ያልሆነ ሂደት ነው፡፡ እንደሚታወቀው እንሽላሊቶች ጭራቸው ቢቆረጥባቸውም መልሰው የመተካት ልዩ ችሎታ አላቸው፡፡ ጭራቸው በሚቆረጥባቸው ጊዜ የቆሰለው ቦታ ላይ ያሉ ሕዋሳት ለማደግ ይነቃቃሉ፤ ጭራው ሙሉ በሙሉ እስኪተካም ድረስ ዕድገት ይቀጥላል፡፡ ሆኖም አዲሱ ከዋነኛው ጋር ሲነፃፀር አጭር ነው፡፡ በአብዛኛው ሕዋሳት ለማደግ የሚነቃቁት በቁስሉ አንደኛ ወገን ብቻ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን ሕዋሳት በሁለት ወይም ከዛ በላይ ጭራ ያበቅላሉ፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ጭራው ጉዳት ቢደርስበትም ሙሉ ለሙሉ ለመቆረጥ የማያደርሰው ይሆናል፡፡ እንዲያም ሆኖ ግን ደግሞ የመጀመሪያው ዋነኛው ጭራ እያለ አንድ ወይም ሁለት ጭራዎች በተጨማሪ ሊበቅሉ ይችላሉ ማለት ነው፡፡

ባሲሊስክ (Basilisk) የሚባሉት እንሽላሊቶች ከፊት ይልቅ የኋላ እግራቸው የዳበረ በመሆኑ፤ መሬት ላይ ሲሮጡም የሚጠቀሙት የኋላ እግራቸውን ነው፡፡ ረጀሙን ጭራቸውን ደግሞ ሚዛናቸውን ለመጠበቅ ይጠቀሙበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ ውኃ ላይም በመሮጥ የታወቁ ናቸው፡፡ 400 ሜትር ድረስ በውኃ ላይ ሳይሰምጡ የመሮጥ ብቃት አላቸው፡፡ እነኚህ እንሽላሊቶች ትልቅ እግሮችና ቀለል ያለ አካል ስላላቸው የውኃ ላይ ሩጫ ይቀላቸዋል፡፡ በሩጫው በፍጥነት ከቀጠሉ አይሰምጡም በመኻል ቆም ካሉ ግን መስመጥ አይቀርላቸውም፡፡ በዋናም በኩል ጥሩ ዋናተኞች ናቸው፡፡

ማንይንገረው ሽንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004)

Pages: 1