ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Animals . | 1 guest
Pages: 1
Posted on 09-08-18, 07:40 am


Karma: 90
Posts: 824/879
Since: 02-29-16

Last post: 66 days
Last view: 66 days
በምድር ላይ የሚገኙ ትልቅ ወፎች ሰጎኖች ናቸው፡፡ ከ2.5 ሜትር በላይ ርዝመትና 135 ኪሎ ግራም ያህል ክብደት ሲኖራቸው መብረር ከማይችሉት አዕዋፍ ይመደባሉ፡፡ የሚኖሩትም ከ50-70 ዓመታት እንደሚሆን ይገመታል፡፡ ሰጎኖች ጠንካራ ቅልጥም ሲኖራቸው በፍጥነት ለመሮጥና ከጠላቶቻቸው ለማምለጥ ይረዳቸዋል፡፡ በዓመት ከ30-50 እንቁላል ይጥላሉ፡፡ እንቁላላቸው 1.5 ኪሎ ግራም ያህል ክብደት ያለው ሲሆን በምድር ላይ ያለ ትልቁ ነጠላ ህዋስ ነው፡፡ የመጠኑም ትልቅነት የትንሿን ወፍ (እዝዝ ወፍ) 4,600 ያህል እንቁላል በውስጡ ሊይዝ የሚችል ነው፡፡ የእንቁላላቸውም ቅርፊት በጣም ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ እስከ 130 ኪ.ግ የሚመዝን አካል ቢቀመጥበት እንኳን ላይሰበር ይችላል፡፡ ከርቀት ጠላት መምጣቱን ለማየት መሬት ላይ ተቀምጠው አንገታቸውን በማስገግ በጥንቃቄ እየተመለከቱ አደጋው መቃረቡን ካወቁ ለመሸሽ ይዘጋጃሉ፡፡

ዕድሜ

በቀቀንና ሌሎች የተለያዩ የንስር ዓይነት ወፎች ከ100-300 ዓመት ዕድሜ እንደሚኖሩ ይገመታል፡፡ ጥንብ አንሳ - 118፣ በቀቀን - 120 እና ወርቃማ ንስር - 104 ቢገመቱም እነዚህ ግምቶች ከብዙ ዓመት በፊት ይኖሩ ለነበሩ ወፎች ነው የሚሠራው፡፡ በዘመናዊው የወፎች ፓርክ ግን 75 ዓመት የሞላው እንኳን አልተዘገበም፡፡ ንስር ጉጉቶች (Eagle Owl) - 68፣ ጀርባ ጥቁር አሳ አዳኝ ወፍ (Black Backed Gull) - 63፣ ኮንዶር (Condor) - 52፣ በቀቀን 54፣ ጭልፊት - 55፣ ነጭ ሻሎ - 51፣ ወማይ (Starling) - 17፣ ካናሪ (Canary) 22፣ የእንግሊዝ ስፓሮው (English Sparrow) 23 እና ባለ ቀይ ጉትዬ ካርዲናል (Red Crested Cardinal) 30 ይገመታሉ፡፡ በአጠቃላይም ወፎች ከአጥቢዎች የተሻለ ዕድሜ እንዳላቸው ይጠቀሳል፡፡

Pages: 1