ሄሎ ሀበሻ ምርጥ የሀበሻ መዝናኛ ሰፈር፣
ይህ ዌብ ሳይት ሀበሻን ከመላው አለም በማገናኘት የሚያወያይ
የሚያዝናና ዌብ ሳይት ወይም መድረክ ነው፥፥
ተሳተፉ ፣ ኮመንት አድርጉ ፣ የራሳችሁን ፃፉ
0 users browsing Animals . | 1 guest | 1 bot
Pages: 1
Posted on 09-08-18, 07:36 am


Karma: 90
Posts: 823/879
Since: 02-29-16

Last post: 66 days
Last view: 66 days
እንደ በግ፣ ፍየል፣ ቀጭኔ፣ ዲር፣ አንቴሎፕ (Antelope) እና ላም ያሉ እንስሳት የዋጡትን ምግብ መልሰው በማመንዠክ ይታወቃሉ፡፡ ይኼም የሚሆነው ጨጓራቸው አራት ክፍል ስላለው ነው፡፡ የመጀመሪያው ምግቡ በአፍ አኘክ አኘክ ተደርጎ በመጀመሪያ የሚደርስበትና እንደ ማጠራቀሚያ የሚያገለግለው ሲሆን፤ ሩሜን (Rumen) ይባላል፡፡ ከዛም በቀስታ ወደ ሁለተኛው ክፍል ሬዝተኩለም (Reticulum) ይገባል፡፡ እዛም ምግቡ ወደ ትንንሽ ጥቅል ይለወጣል፡፡ ይኸው ምግብ እንስሳው በሚያርፍበት ጊዜ ወደ አፍ እንደገና ይምጣና ይመነዥካል፡፡ በዚህን ጊዜ እንደመጀመሪያው በግርድፍ ሳይሆን በደንብ ደቆና ከምራቅ (ኢንዛይም) ጋር ተዋህዶ ወደ ሦስተኛው ክፍል ኦማሰም (Omasum) ይላካል፡፡ እዚያም ምግቡ ይፈጫል፡፡ በመጨረሻም አራተኛው ክፍል አቦማሰም (Abomasum) ከአንጀት ክፍላቸው ጋር በመሆን የአፈጫጭ ሒደቱን ያጠናቅቀዋል፡፡

አንገታሞቹ

ቀጭኔ ዕድሜ ለረጅም አንገቱ በምድር ላይ ያለ በጣም ቁመታም አጥቢ ለመባል በቅቷል፡፡ አንዳንድ ቁመታቸው 6 ሜትር የሚደርሱ ቀጭኔዎች ሊገኙ ቢችሉም፤ በአማካይ 3 ሜትር ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገመታል፡፡ ቀጭኔ አሁን በምድር ርየለው ቁመታም ቢሆንም ቅሉ ከምድር ገፅ የጠፋው የአውራሪስ ዝርያ (Baludiherium) ግን በቁመት ይበልጠው ነበር፡፡ ረጅሙ ቀደምት የአውራሪስ ዝርያ ቁመቱ እስከ 7.5 ሜትር ይገመታል፡፡ ለቀጭኔ ረጅምነት ትልቁን አስተዋጽኦ ያደረገው አንገቱ በውስጡ ያሉት አጥንቶች ሰባት ብቻ ናቸው፡፡ ይኼ ደግሞ ረጅም አንገት ከሌላቸው ሌሎች አጥቢዎች ጋር የአጥንቱን ብዛት እኩል ያደርገዋል፡፡

በተለምዶ ቀጭኔ ድምፅ አልባ ትባላለች፡፡ ቀጭኔዎች አዳኞች በሚያድኗቸውና በሚያቆስሏቸው ጊዜ ድምፅ አያወጡም፡፡ አጥኚዎች ግን የድምፅ ማውጫ ክፍላቸው በደንብ የተሟላ ዕድገት ባይኖረውም፤ ቀጭኔዎች ድምፅ ማውጣት እንደሚችሉ አረጋግጠዋል፡፡ በእርግጥ ይህ ክፍልም ከትላልቆቹ ይልቅ በታዳጊዎቹ ላይ የተሻለ ዕድገት ያሳያል፡፡ በዚህም ምክንያት ታዳጊዎች የተሻለ ድምፅ ያወጣሉ፡፡

ማንይንገረው ሸንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004 ዓ.ም.)Pages: 1